Sunday, 10 December 2023 20:29

“ሆኖ መገኘት” የተሰኘ መለወጥ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

 በሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የህይወት ፍልስፍና መነሻነት የተሰናዳውና ስለ መለወጥና ለመለወጥ ስለ ሚያስፈልጉ ዘርፈ ብዙ ቁርጠኝነቶች የሚያትተው “ሆኖ መገኘት” መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት እውቅናናፈቃድ ባለው በሆቴል ማኔጅመንት ከፍተኛ ብቃትባለውና በስትራቴጂ ልማት ብሎም በተቋማዊአመራር ከፍተኛ ልምድ ባዳበረው እንዲሁም በሀይሌሆቴሎችና ሪዞርቶች አመራር ብቃቱ አንቱታንባተረፈው መልካሙ መኮንን እና በተቋማዊ ልማትእንዲሁም በዘላቂ የትምህርት ዘርፍ ባለራዕይ መሪበሆነው ፋሲል መንግስቴ የተሰናዳው ይሄው መፅሀፍመለወጥ ለሚፈልጉ ባለ ሀሳቦች እጅጉን ጠቃሚእንደሚሆን ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴበመፅሀፉ ጀርባ በሰጠው የጀርባ ማስታወሻ ገልጿል፡፡ “ምንም እንኳ የመጽሀፉ መነሻ ሀሳብ ከእኔ የህይወትፍልስፍና የተቀዳ ቢሆንም እኔ ግን እንደሌላ ሰውሆኜ ነው ያነበብኩት እኔ በግል ህይወቴ የምኖራቸውየህይወት መርሆዎችና ፍልስፍናዎች በተለያዩ ቢዝነሶች ውስጥ ሊተገበር የሚችል የፍልስፍናመፅሀፍ እንደመነሻ ሀሳብ ሆነው መቅረባቸው ታላቅ የደስታ ስሜት ጭሮብኛል……፡፡ ይህ የደስታስሜት የሚመነጨው ከተራ ግብዝነት አይደለምይልቁንም እንደ ሀገርና እንደህዝብ መድረስ ይገባን ነበር እያልኩ የምቆጭባቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ነው፡፡

እንደ ሀገርና እንደ ህዝብ የምንኮራባቸው በርካታ ሀብቶች ቢኖሩም ልናስተካክላቸውና ልናርማቸውየሚገቡን ደግሞ ብዙ ጉዳዮች ወይም “ቢሆን”የምለውን ምኞቴን በዚህ መፅሀፍ አይቻለሁ…”በማለት አስተያየቱን ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴአስፍሯል፡፡ በሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በሁሉምቅርንጫፎች የሚሰጠው ወጥ እና ተመሳሳይየአገልግሎት ጥራት “እኔም ሀይሌ ነኝ”….. ይቻላልበሚል መርህ ላይ የተመሰረተና በአገር ልጅ ችሎታናብቃት ላይ የተመሰረተ ፍልስፍና መሆኑ እንደሀገር ተግባር ላይ ሊውል የሚገባው ትልቅ ተግባርመሆኑም በመፅሀፉ ተካትቷል፡፡በ5 ምዕራፍ ተከፋፍሎ በ198 ገጽ የተቀነበበው“ሆኖ መገኘት” መፅሀፍ በ350 ብር ለገበያ የቀረበ
ሲሆን በቅርቡ ለምርቃት እንደሚበቃም ከደራሲያኑእና “ከእሺ” ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃያመለክታል፡፡ የመፅሀፉ አርታኢ ደግሞ ደራሲና
ጋዜጠኛ ደሳለኝ ስዩም መሆኑም ታውቋል፡

Read 802 times