Sunday, 10 December 2023 20:32

የነፍስ ‘ሰርጀሪ’

Written by  አንተነህ ይግዛው
Rate this item
(4 votes)

(በዘገባ ላይ የተመሰረተ አጭር ልብ ወለድ) ቴሌቪዥኑ የሰዓቱን ዜና አገባደደ… ቴሌቪዥኑ የዘመኑን መብረቅ አወረደ!!… ‘የዶክተር ፊሊጶስ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ’ የሚል ጉርምርምታን ተከትሎ የወረደው መብረቅ፣ እሴተን አልጋዋ ላይ እንዳለች አደረቃት፡፡ ዶክተር ፊሊጶስ መርሻ አረፉ፡፡ ስንቶችን ከህመም የፈወሱት፣ ስንቶችን ከሞት ያዳኑት፣ ታዋቂው የቀዶ ህክምና ሀኪም ዶክተር ፊሊጶስ፣ በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው አለፈ።  የሌሊት ተረኛ ሆነው ሲሰሩ ካደሩበት ሆስፒታል መርሴድስ መኪናቸውን እያሽከረከሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲጓዙ፣ ፍሬን የበጠሰ ጦሰኛ ሚኒባስ እላያቸው ላይ ወጣባቸው፡፡ ታዋቂው የቀዶ ህክምና ሀኪም፣ ለህክምና ሳይደርሱ መንገድ ላይ ተፈጸሙ፡፡

ከአገሪቱ ስመጥር የህክምና ባለሙያዎች  አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ፊሊጶስ፣ በድንገተኛ አደጋ ስለመሞታቸው ተነገረ - ብዙዎችም ደነገጡ፡፡ ቀብራቸውን በቴሌቪዥን አይተው ክፉኛ ከደነገጡና ካዘኑ ብዙዎች መካከል፣ እሴተ አንዷ ናት፡፡(ይቅርታ… አንዷ አይደለችም)፡፡ እንደዋዛ አንዷ ናት ብሎ እሷን ከብዙዎች መቀላቀል፣ ድንጋጤና ሃዘኗን ማቅለል፣ ጉዳቷን ማሳነስ ይሆናል። ዜና አንባቢው ቀጥሏል… “በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተነበበው የህይወት ታሪካቸው እንደሚያሳየው፣ ዶክተር ፊሊጶስ መርሻ ህዝባቸውን በትጋት ሲያገለግሉ የኖሩ ምስጉን ባለሙያ፣ ቸርና ለተቸገረ አዛኝ እንዲሁም …” “አይደሉም!... በጭራሽ ለተቸገረ አዛኝ አይደሉም!...” በንዴት ጦፋ ከአልጋዋ ዘላ ወረደች፡፡

“… ዶክተር ፊሊጶስ መርሻ ባለትዳርና…” ዜና አንባቢው እስኪጨርስ አልታገሰችውም፡፡ ቴሌቪዥኑን ዘግታ ጸጉሯን እየነጨች ተወራጨች፡፡ የማይነጥፍ እንባ ረጨች፡፡ “ለተቸገረ የሚያዝን ሰው፣ ‘እረዳሻለሁ’ ብሎ የገባውን ቃል አያጥፍም!... አይዞሽ ብሎ ተስፋ ከሰጠ በኋላ ሜዳ ላይ ጥሎ አይሄድም!... ውሸት ነው!... እሳቸው ለተቸገረ አያዝኑም!... ፍጹምውሸት ነው!...” አልጋዋ ላይ ተደፍታ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች፡፡ ‘ከጭንቀት ነጻ ያወጡኛል’ ያለቻቸው ብቸኛ ሰው፣ ከጭንቀቷ ጋር ጥለዋት ሞቱ፡፡ ‘ራሴን እየወቀስኩ ከመኖር ይገላግሉኛል፣ የሃጢያተኝነት ስሜቴን ያጥቡልኛል’ ብላ ተስፋ ያደረገችባቸው ዶክተር ፊሊጶስ ቃላቸውን አፈረሱ፡፡ አርብ ከሰዓት
በኋላ ወደ ቢሯቸው ተመልሳ እንድትመጣ ቀጠሮ ሰጥተዋት፣ ሰኞ ጠዋት ወደማይመለሱበት እብስ አሉ፡፡ አርብ ከሰዓት በኋላ ከዶክተሩ ጋር ተገናኝታ፣
እውነቱን እስኪነግሯትና የዕድሜ ልክ ጥያቄዋን እስኪፈቱላት ቸኩላ ነበር፡፡ ከሚያስጨንቃት የሃጢያተኝነት ስሜት ነጻ የምትወጣው እሳቸውን
ስታገኝ ብቻ ነው፡፡ እሳቸውን ማግኘት፣ እንጥፍጣፊ የመኖር ሰበብ ማግኘት ነበር፡፡ መኖሯ ትርጉም አልባ ሆኖባት ስትሰቃይ ኖራለች፡፡ መፈጠሯን እንድትወደው የሚያደርግ አንዳች እንኳን ምክንያት የላትም፡፡ ከመኖር ያተረፈችው መሳቀቅና ባይተዋርነትን ብቻ ነው፡፡ እየተሳቀቀችነው ልጅነቷን ያሳለፈችው። አፈር መፍጨት፣ ውሃ መራጨት ብሎ ነገር በእሷ ልጅነት ውስጥ የለም፡፡ ከዕድሜ እኩዮቿ ጋር አልተጫወተችም፡፡ አልፈነደቀችም፡፡ ቅስም ሰባሪ ስም ከሰጧት የመንደሩ ልጆች እየሸሸች ነው ያደገችው፡፡ “ጠባሴ!” እያሉ ነበር የሚጠሯት፡፡ አባቷ ያወጡላትን ስም ትተው፣ከደረቷ እስከ እምብርቷ በሚዘልቀው የገላዋ ጠባሳ ነበር የሚጠሯት፡፡ ይህን ስም መስማት አሳቅቋት፣ ባዶ ቤት ተደብቃ ነው ልጅነቷን የገፋችው፡፡ ባዶቤት… እህት ወንድም አልቦ… ያለ እናት… ከጡረተኛአባት በቀር ወዳጅ ዘመድ የማይጎበኘው ባዶ ቤት ነውያደገችው - ባይተዋር ሆና፡፡ ሳታውቀው ራሷን አድጋ
አገኘችው - ወጣትነት ላይ ቆማ፡፡ ከእለታት አንድቀን በረከት የሚባል ሰው መጣ። በረከት ሰዓሊው…ወደተገፋችው እሴተ ገፍቶ መጣ፡፡ “መርጬሻለሁ”
አላት፡፡ ፍቅር የሚባል ነገር እንዳለ አስታወሳት፡፡ብቸኝነቷን አፍርሶ ሁሉንም የሚያስረሳትን፣የህይወቷን ጣዕም የሚቀይር፣ ፍቅር የሚባልቅመም ይዞላት መምጣቱን አበሰራት፡፡ ለአመታትያቀረቀረችዋን እሴተን፣ በረከት የሚባል ወንድደጋግፎ ቀና አደረጋት፡፡ አንድ ቀን እንዲሁ በረከትየሚባለው ሰው ሄደ። በረከት ፍቅረኛዋ… ገፍቶ መጥቶከጎኗ የቆመው በረከት፣ ብዙም ሳይቆይ ገፍቷት ሄደ፡፡ደስ ብሏት ሳትጨርስ፣ ቀና ብላ ሳታበቃ፣ እንዳትቃና
አድርጎ ሰብሯት ሄደ፡፡ ‘ፍቅር ነው ያመጣኝ’ ያላትበረከት፣ የሄደበትን ምክንያት ሳይነግራት ድንገትከጎኗ ተሰወረ፡፡ ለነገሩ ባይነግራትም ምክንያቱን
ታውቀዋለች፡፡ በዚያች የተኮነነች የመጨረሻ ምሽት፣እዛች የተረገመች የኪራይ ጫጉላ ውስጥ የሆነውንሁሉ አትረሳውም፡፡ በውስጡ የተለኮሰውን ነዲድ
ስሜት፣ ፋታ የነሳውን የወሲብ አምሮት፣ ችኮላና ጥድፊያውን አትረሳውም፡፡ ልብሷን ላለማውለቅ መፈለጓንና በጭንቀት ተውጣ ከአልጋው ጫፍ ላይ ተኮራምታ መቀመጧን፣ ከመግደርደር እንደቆጠረው አትዘነጋውም፡፡ ተጣድፎ ልብሱን ሲያወላልቅ ፊቱ ላይ ይግለበለብ የነበረውን ወላፈን ታስታውሰዋለች። ከንፈሯን እያኘከ ትንፋሽ እስኪያጥራት ስሞ፣ አዘናግቶ ልብሷን እስኪያወልቅላት ድረስ በስሜት ሲርገፈገፍ ነበር፡፡ ስስ ቲ-ሸርቷን እስኪያወልቅላት ድረስ በስሜት ተወጥሮ ከላይዋ ላይ ሲቃትት አይታዋለች፡፡

እርቃን ገላዋን ሲመለከት በድንጋጤ ከል የለበሰፊቱን፣ የተረበሸ ስሜቱን፣ የረገበ አምሮቱን፣ የተነፈሰ ወንድነቱን… ሁሉንም በእንባዋ መነፅር ስር አይታለች። ወንድነቱ እሱ እንዳለው በሱስ ሰበብበድንገት እንዳልተልፈሰፈሰ ታውቃለች። የናፈቀውን ወሲብ በወጉ እንዳይፈጽም በድንገት ያኮላሸው ገላዋ ላይ ያለው ጉድ መሆኑን ነጋሪ አያሻትም፡፡ ከዚያችምሽት አንስቶ አድራሻውን ያጠፋበትንና ስልኳንየማያነሳበትን ምክንያት ጠንቅቃ ታውቃለች። ይህከደረቷ አንስቶ እስከ እምብርቷ የሚወርድ ጦሰኛጠባሳ ነው፡፡ ለመኖሬ ትርጉም ይሰጠዋል ብላ ተስፋያደረገችበት በረከት፣ ተስፋዋን ገድሎባት ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ መኖር፣ ለረዥም ስቃይ ራስን ማዘጋጀት ሆኖ ታያት፡፡ ለዚህ ነው መርዝ ጠጥታ ለመሞት የወሰነችው፡፡ ወደ ሞት የሚወስዳትን መርዝ ጨልጣ ሳትጨርሰው አባቷ ደረሱባት፡፡

“ምነው ልጄ!?... እኔን ለማን ጥለሽኝ ለመሄድ ጨከንሽ!?” እያሉ አቅፈዋት ተንሰቀሰቁ፡፡ አንድ ልጃቸውን አጥተው ባዶ ቤት ብቻቸውን ሲቀሩ ታይቷቸው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ፣ በእንባ እየታጠቡ አምርረው ወቀሷት፡፡ በረከት ተደብቋት ሄዶ እንደቀረው፣ እሷም ተደብቃቸው ወደሞት ሄዳ ልትቀር መወሰኗን አወቁ፡፡ “ለምን ብለሽ ይሄን ክፉ ነገር አሰብሽ ልጄ?... እስኪ ንገሪኝ…” አሏት፡፡“አንተ ንገረኝ!” አለቻቸው እንደ እብድ እያደረጋት፡፡ ስለ ሁሉም ነገር ነገሯት፡፡ “በልጅነትሽ የፈላ ውሃተደፍቶብሽ ነው” እያሉ ሲነግሯት ስለኖሩት የደረቷላይ ጠባሳ እውነቱን ተነፈሱላት፡፡ እናቷም በነቀርሳህመም ሳይሆን፣ እሷን እርጉዝ ሆነው በቀዶ ህክምናሲገላገሉ በወሊድ እንደሞቱ አረዷት፡፡ ሃኪሞቹ እናቷንለማዳን ባይችሉም ጽንሱን ለማትረፍ ሲረባረቡ፣በእናትየዋ ማህጸን ውስጥ ፈፅሞ ያልጠበቁት ዱብዕዳይገጥማቸዋል - ሁለት የተጣበቁ ጽንሶች፡፡ጽንሶቹ ልባቸውን ጨምሮ የተወሰነ የሰውነትክፍላቸውን የሚጋሩ ሆኖ መገኘቱ ህክምናውንአደገኛ እንዳደረገው፣ ሀኪሞቹም ጽንሶቹን በቀዶህክምና በመለያየት አንደኛው ጽንስ ለማትረፍመገደዳቸውን ነገሯት፡፡ መንታ እህቷ ሞታ፣ እሷመትረፏንም አረዷት፡፡

በወቅቱ አስቸጋሪውን ቀዶህክምና በስኬታማ ሁኔታ ያጠናቀቀው የሃኪሞችቡድን ከፍተኛ አድናቆት ማትረፉን፣ የቡድኑ መሪየነበሩት ዶክተርም በቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅእንደተደረገላቸው አወጓት፡፡ አባቷ እውነታቸውንነው፡፡ ሰዓታትን የፈጀው በቀዶ ህክምና የታገዘ
ወሊድ፣ ብዙዎችን አስደንቋል። አስደምሟል፡፡ በአገሪቱ የቀዶ ህክምና ታሪክ ጉልህ ሥፍራእንደሚኖረውና የሀኪሞቻችንን ብቃት እንደሚያሳይ
ተመስክሮለታል፡፡ እሴተ ራሷን ጠላች፡፡ ሌሎች ወደሞት በተሸኙበት መንገድ ወደ ህይወት የመጣችጨካኝ፣ ስለእናቷ የማትራራ የእፉኝት ልጅ፣ ከእህቷ
በቀማችው ትንፋሽ ነፍስ ዘርታ፣ የቆመች እርጉም ፍጡር አድርጋ ራሷን ቆጠረች፡፡ ከተፈጸሙ መንታ ነፍሶች የተወጠነች የግፍ ፍጡር እንደሆነች ተሰማት፡፡ አባቷ እውነቱን ከነገሯት እለት አንስቶ፣ የእናቷና የእህቷ የሙት መንፈስ እረፍት ይነሳት ጀመር፡፡ በህይወት ለመቀጠል የሚያበቃ አቅምና ወኔ አልነበራትም፡፡ ዶክተሩ አቅም ይሆኑኛል ብላ ነበር ተስፋ የጣለችው፡፡ ተጭኖ ካጎበጣት የበደል ሸክም እፍኝ ቆንጥረው ቀለል ሊያደርጉላት፣ ትንሽም ቢሆን የመጽናናት ምክንያት እንደሚፈጥሩላት አስባ ነበር፡፡ አሁን ግን የመጽናኛ ምክንያቷን ተነጠቀች። ዶክተር ፊሊጶስ መሞታቸውን የቴሌቪዥኑ ዜና አንባቢ አረዳት፡፡ ራሷን ትራሷ ስር ቀብራ ተንሰቀሰቀች፡፡ ዶክተር ፊሊጶስ ጭላጭ ተስፋዋን ይዘውባት ላይመለሱ ሄደዋል፡፡ “ዛሬ እንኳን ፔሸንት ይበዛል፣ ለምን አርብ ብቅ አትይም?” ብለው አዘናጓትና እስከወዲያኛው አሸለቡ፡፡ የሆስፒታሉን ኮሪደር ካጣበበው ታካሚየማይተናነስ የውስጥ ህመም እንደሚያሰቃያትአያውቁም፡፡ ኮሪደሩ ላይ ቆማ ሲያዩዋት፣ ከባለጉዳይ እንጂ ከታካሚ አልቆጠሯትም፡፡ እንደምትፈልጋቸው
ስትነግራቸው ሌላ ቀጠሮ ሰጥተው ያሰናበቷት፣ጉዳይዋ አስቸኳይ ስላልመሰላቸው ነበር፡፡ ወደሳቸውየወሰዳት፣ ፋታ እማይሰጥ አስቸኳይ ጉዳይ መሆኑን
የምታውቀው እሷ ብቻ ናት፡፡ ራሷን ለማጥፋትስትሞክር እጅ ከፍንጅ የያዟት አባቷ፣ የሆነውን ሁሉከነገሯት ዕለት አንስቶ እንደቸኮለች ናት፡፡ መወለዷ
ድራማ የሚመስል፣ ለማመን የከበደ፣ ገድል መሳይ]ዜና እንደነበር አባቷ ነግረዋታል፡፡ እንደነበር አባቷ ነግረዋታል፡፡ ድራማ በሚመስለው ዜና ውስጥ፣ ብዙ ተዋንያን ነበሩበት፡፡ ከሁሉም ጎልተው የወጡት ግን፣ ቀዶ ህክምናውን ያከናወነው የሃኪሞች ቡድን መሪናቸው፡፡ ብዙዎች ዜናውን ሰምተው አጀብ ያሉት ስለ እሳቸው ነው፡፡ ሌሎቹን የድራማው ተሳታፊዎችነገሬ ያላቸው አልነበረም፡፡ መሪ ተዋናዩ ስለሰሩትየህክምና ገድል ብዙ ተብሏል፡፡ በወሊዱ ስለሞቱትምስኪን ነፍሶች ግን ያሰበም የጠየቀም አልነበረም፡፡እሴተ ወደሞት ይወስደኛል ብላ ተስፋ ያደረገችውንየመርዝ ብልቃጥ ከጣለች ከወራት ጊዜ በኋላ፣በህይወት ለመኖር መጽናኛ ይሆነኛል ያለችውንይህን ጥያቄ አነሳች፡፡ “ቆይ ሃኪሙ ግን ስማቸው ማንይባላል?” በጉጉት ስሜት አባቷን ጠየቀች፡፡ አባትየውበረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ወደ ሰማይ እንዳንጋጠጡማሰብ ጀመሩ፡፡ “ማን ነበር ያሏቸው?...የኔ ነገር!...በየራዲዮናው ሲጠሩ ነበርኮ…” ለማስታወስ ሞከሩ፡፡ እሴተ ቸኩላለች፡፡ “እ… እሺ… የትኛው ሆስፒታልነበር የሚሰሩት?” በጉጉት ተውጣ ጠየቀች፡፡ለጊዜው ሆስፒታሉን ማወቋ በቂ ነበር፡፡

እሴተ ወደሆስፒታሉ ሄዳ ዶክተሩን መፈለግ ጀመረች፡፡ ከብዙልፋትና ድካም… ከአስቸጋሪ ውጣውረድ… ከእልህአስጨራሽ እንግልት በኋላ… ዶክተሩ የግላቸውንሆስፒታል ከፍተው እየሰሩ እንደሆነ ደረሰችበት፡፡ ጋውናቸውን እንደለበሱ ወደ ታካሚዎች መኝታክፍል ሲጓዙ ኮሪደር ላይተገጣጠሙ፡፡ ለጉዳይእንደምትፈልጋቸው ስትነግራቸው፣ እርምጃቸውንሳይገቱ ነበር መልስ የሰጧት፡፡ “ኧርጀንት ኬዝ ስላለብኝ ላነጋግርሽ አልችልም” አሏት፡፡አርብ ከሰዓት በኋላ ተመልሳ እንድትመጣ ቀጠሮ ሰጥተዋት ተለያዩ፡፡ ዶክተሩ በመኪና አደጋመሞታቸውን ቴሌቪዥኑ ሲነግራት፣ ትራስ አቅፋተንሰቀሰቀች፡፡ “አገኘሁት!... እሴቴ… የዶክተሩንስም አገኘሁት!” የአባቷ የደስታ ድምጽ ከሳሎንተሰማ፡፡ ለቅሶዋን አቁማ ቀና ብላ ልታያቸውምሆነ ልትሰማቸውም አልፈቀደችም፡፡ ሲያምባርቅበቆየው የቴሌቪዥኑ ድምጽ ፋንታ፣ የልጃቸውለቅሶ ተሰማቸው፡፡ በእጃቸው የያዙት አሮጌ ጋዜጣእስከሚርገበገብ በድንጋጤ እየተርበተበቱ የመኝታቤቷን በር በርግደው ገቡ፡፡

እሴተ በእንባ እየታጠበች አልጋዋ ላይ ተዘርራለች፡፡ አጽናንተው ቀናማድረግ ይቅርና የሆነችውን ለማወቅ አልቻሉም፡፡ አቅፈዋት ተንሰቀሰቁ፡፡ ቀና ብላ ልታያቸውም፣የሚሉትን ልትሰማቸውም አልፈቀደችም፡፡ ቀና ብላብታይ ኖሮ፣ የተወለደች ሰሞን ለንባብ የበቃውን አሮጌ ጋዜጣ ትመለከተው ነበር፡፡ “አስደናቂው የወሊድ ቀዶ ህክምና በስኬት ተጠናቀቀ” የሚልርዕስ ካለው ዜና ስር፣ የአንድ ራሰ በራ ጎልማሳናአይኗን ያልገለጠች ጨቅላ ፎቶግራፍ ጎን ለጎን ሆኖትመለከት ነበር፡፡ ራሰ በራው ጎልማሳ፣ ዶክተርፊሊጶስ… አይኗን ያልገለጠችዋ ጨቅላ፣ ራሷ መሆኗን ታውቅ ነበር፡፡ ዶክተሩን ትፈልግ የነበረው አንድ ነገር እንዲነግሯት ነው፡፡ የሆነ… ጸጸቷን የሚያቀልላት ነገርእንዲያቀብሏት፡፡ ቢያንስ እሷን ለመውለድ ሲሉ በሞቱ እናቷ እንጂ፣ ተጣብቃት ወደ ምድር በመጣችእህቷ ሞት ተጠያቂ እንዳልሆነች እንዲያረጋግጡላ። ዶክተሩ የፈለገችውን ሳይነግሯት ወደማይቀርበትእብስ አሉ፡፡

እርግጥ ለእሷም ባይሆን፣ ለህዝቡ ተናግረውነበር፡፡ ከአመታት በፊት የተናገሩትን እውነት ነው፣ይህ አሮጌ ጋዜጣ የያዘው፡፡ ቀና ብላ ጋዜጣውንብታየው፣ ከዶክተሩ አንደበት የወጣውን እውነትትመለከት ነበር፡፡ “የምትጋሩትን ልብ ለመንታእህትሽ ብንሰጣት፣ የመኖር ዕድል እንደማይኖራትእናውቅ ነበር፡፡ ሁለታችሁም ከመሞታችሁ በፊትልቡን ለአንቺ በመስጠት፣ ቢያንስ አንቺን ማትረፍእንዳለብን የህክምና ቡድኑ አባላት የጋራ ውሳኔ ላይደረስን፡፡ እሷ መሞቷ እንደማይቀር የሚያረጋግጡምልክቶች ስላየን እንጂ፣ አንቺን በህይወት ለማቆየትበሚል አይደለም በእህትሽ ላይ የፈረድነው…” ሲሏትታደምጣቸው ነበር፡፡ ቀና ብትል ኖሮ የጓጓችለትንእውነት ተንፍሰው፣ ከጭንቀቷ ይገላግሏት ነበር፡፡እሴተ ግን አባቷ ክንድ ላይ ሆና ትንሰቀሰቃለች፡፡


Read 330 times