Sunday, 10 December 2023 00:00

አስማት

Written by  -ኪሩቤል ሳሙኤል-
Rate this item
(0 votes)

(Searching For Alternative Reality)
“--የሰበሰብኩት…ስለራሴ ያለኝን እውቀት በአንድ ሌሊት ድራሹን አጥፍቼ አዲሱን ማንነቴን
መፍጠር እንደምችል የዚህ ጥበብ ጉዞ አስተማረኝ፡፡ በሁሉም የተፈጥሮ ስርዓት ውስጥ በምድር
ቃላት ለመተረክ የሚከብዱ ሚስጥራት ታትመዋል፡፡ በነዛ ሚስጥራት ውስጥ ህይወቶች እየተመላለሱ
እንደሆነ የሚረዳው የነፍሱን አይኖች የከፈታቸው ብቻ ነው፡፡ --”
==========================================

ወደ ተከለከለውና ጥቂቶች ብቻ ወደሚረዱት (Esoteric) እውቀት አብረን ልንሰደድ ነው፡
፡ በቃላትና በቁጥሮች ብልሀት የሸሸጉብንን እውቀት ከጥልቁ ቀርጥፈን ልናወጣው ስለሆነ ለዚህ ስውር እውቀት አዕምሯችን ዝግጅቱን ያድርግ፡፡
ስለ አስማት ማውራት እፈልጋለሁ፡፡ ስለ አስማት ምንነት አለም ምን እንደሚል
ከማውሳቴ በፊት፣ ይህን አለም ቀርቤ ጥልቀቱን እንዳጠናው የጋበዘኝ የህይወት ገጠመኝ ላይ ጥቂት ማብራሪያ ልስጥ፡፡
አንድ ቀን… በአሁን ሰዓት ላይ የቅርብ ወዳጄ ከሆነው ሰው ጋር ተዋወኩኝ፡፡ ቡክ ወርልድ ውስጥ እየሰራሁ ነበር፡፡ በጊዜው እድሜዬ አስራ ዘጠኝ ነው፡፡ የመፅሐፍ ሽያጭ ስራ ብዙ አይነት ሰዎችን ያስተዋውቃል፤ ከዛም ባለፈ ከሰዎችም እንግዳ እውቀት ያላቸው ሰዎች ድንገት በህይወታችን ውስጥ ይከሰታሉ፡፡ ከነዚህም መካከል አሁን የምላችሁ ወዳጄ አንዱ ነው፡፡
በመፅሐፍ መሸጫ ክፍል ውስጥ ሲገባ በቅድሚያ ከእኔና ፈይሰል ከሚባለው የስራ ባልደረባዬ ጋር ነበር የተገናኘው፡፡ በቅድሚያ የጠየቀን መፅሐፍ የቲዎስዴ ሎባሳንግ ራምፓን “እናንተ ለዘላለም” የሚለውን ነበር፡፡ በወቅቱ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የነበሩ ጂኒየስ ተማሪዎችን የሚያሳብዳቸው መፅሐፍ ነበር፡፡ ምን እንደሚያሳብዳቸው እስካሁን ድረስ ግልፅ አልሆነልኝም፡፡ በተቻለኝ መጠን ለማበድ ሳይሆን ለማወቅ ካለኝ ጉጉት የሰውየውን አስራ አራት የሚደርሱ መፅሐፍቶች ለማንበብ ሞክሬያለሁ፡፡ ከነዛም መካከል ትኩረቴን ስበው በጥልቀት እንድመረምራቸው ያደረጉኝ መጻሕፍት፤Chapters_of_Life፣ Living_with_the_Lama፣
Cave_of_the_Ancients፣ The_Hermit እና You Forever ናቸው፡፡ ለማንኛውም ስለ ራምፓ ሌላ ጊዜ፡፡
እናም ይህ ሰው የራምፓን መፅሐፍ ሲጠይቀኝ ትኩረቴን ሳበው፡፡ በአስማት ጉዳዮች ላይ እውቀቴ እንጭጭ ቢሆንም ከአንድ አስማተኛ ከሆነ ሰው ጋር በጉዳዩ ላይ መወያየት ግን እችል ነበር፡፡ ይህም እውቀቴ በዚህ እንግዳ ሰው ላይ እንዳተኩር አደረገኝ፡፡ መፅሐፉ በመሸጫው ክፍል እንደሌለና እኔ ግን በግል ላመጣለት እንደምችል ነገርኩት፡፡ እሱም ያን
ያህል መደነቅ ውስጥ ሳይገባ ተስማማ፡፡ “የአስማታዊ ጥበቦች ይመቹሀል?” ብዬ ጠየኩት፡፡
“ጥበቡን አውቀዋለሁ…ሆኖም ይሄ ራምፓ የሚባለው ሰው ስሙን በተደጋጋሚ እየሰማሁት
ስለሆነ ጥቂት ከጥበቡ የማገኘው ነገር ካለ ብዬ ነው እንጂ…አሁን ካለኝ ላይ ብዙም ልጨምር የማስበው እውቀት የለም፡፡” አለኝ፡፡
“ጥበቡን አውቀዋለሁ ነው ያልከኝ?” ብዬ ደግሜ ጠየኩት፡፡
ፈገግ ብሎ በተረጋጋ መንፈስ ከተመለከተኝ በኋላ …”ና አንድ ነገር ላሳይህ” ብሎኝ ወደ ክፍሉ
ጥጋት አስጠግቶ አቆመኝ፡፡ ከፊት ለፊቴም ከቆመ በኋላ በአራቱም አቅጣጫ እያመላለሰ እንግዳ
የሆኑ የእጅ መንቀሳቀሶችን ካደረገ በኋላ ከመልኬ ላይ የተለጠፉት ሁለቱም አይኖቼ እያዩ በአየር ላይ ተንሳፈፈ (levitate አደረገ)፡፡ የዛን ቀን የስራ ባልደረባዬ የኔን ስራ ደርቦ
እንዲሰራልኝ አስማምቼው፣ ይህን ጥበበኛ ፍለጋ በሩጫ ከስራ ቦታዬ ወጣሁ፡፡ አገኘሁት….
ከዚህ በኋላ አብረን የምንገባበትን አለም አሀዱ ብዬ እንድጀምር የሚያደርገኝን መፅሐፍ
አስተዋወቀኝ፡፡ የመፅሐፉም ስም goetia (The lesser keys of Solomon) ይባላል፡፡ መፅሐፉን ሰጥቶኝ እንደተለያየን በምን አይነት መስገብገብ ውስጥ ገብቼ መፅሐፉን እንደገለጥኩት አትጠይቁኝ፡፡ መጀመሪያ ለማየት የሞከርኩት PRELIMINARY DEFINITION OF MAGIC. LEMEGETON VEL CLAVICULA SALOMONIS REGIS የሚለውን መግቢያ ነው፡፡ እንደገባሁበት ከዚህ አንቀፅ ጋር አይኖቼ ተጋጠሙ፡፡
“Magic is the Highest, most Absolute, and most Divine Knowledge of Natural

Philosophy, advanced in its works and wonderful operations by a right
understanding of the inward and occult virtue of things; so that true Agents being applied to proper Patients, strange and admirable effects will thereby be produced. Whence magicians are profound and diligent searchers into Nature; they, because of their skill, know how to anticipate an effort, the which to the vulgar shall seem to be a miracle.Origen saith that the Magical Art
doth not contain anything subsisting, but although it should, yet that it must not be Evil, or subject to contempt or scorn; and doth distinguish the Natural Magic from that which is Diabolical.”
ስፈልገው የነበረው ይሄን ነበር፡፡ ገና የኑሮን አረር ሳልቀምስ፣ ገና የምድርን ጉድፍ ፈትጌ
ሳላስለቅቅ፣ ገና ህይወት እጆቼን ይዛ ወደየት ይዛኝ እንደምትሄድ ሳልረዳ፣ ገና የአስራ ዘጠኝ አመት ልጅ እያለሁ ስመኘው የነበረው ይሄን ነበር፡፡ አማራጭ ህልውና ማግኘት፡፡ አለምን አሁን ከማያት አይኔ ውጪ ሆኜ ጥበቦቿን መቃኘት፡፡ አማራጭ ህልውና (Alternative Reality) ብዬ ስም ሰጠሁት፡፡ ከደረቁ አለም አፋቶኝ አዲስ እኔነቴን የሚያበጃጅልኝ
እውቀት ሳስስ የነበረው በገፍ ከሚታተሙት የሳይኮሎጂ (Self Help) መፅሐፍ ውስጥ ሳይሆን
ከአስማት መጻሕፍት ውስጥ ነበር፡፡ አሁን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ የሰለሞንን ጥበብ በዚህ goetia (The lesser keys of Solomon) የተባለው መፅሐፍ ውስጥ በማስስበት ወቅት ላይ ከአይናችን ውጭ ሆነው በኛ ላይ መሰልጠን የሚችሉ፣ ከዛም ባለፈ እኛ በጥበብ
የምናዛቸው መናፍስት በዙሪያችን እንዳሉ መገንዘብ ቻልኩ፡፡ እኛ ብቻችንን አይደለንም የሚል እምነት ውስጥም እንድገባ አደረገኝ፡፡ ሆኖም ጭንቅላቴ ፍልስፍናን በመፍተል ላይ ስራዋን ስላደረገች ምንም ነገር ከማመኔ በፊት መመስጠሬን ቅድሚያ ልሰጠው እንደሚገባ ገባኝ፡፡ ወደ ውስጥ ዘልቄ ገባሁ…ሰለሞን በሚስጥራዊው የፈጣሪ ህቡዕ ስም በአንድ እንስራ
ውስጥ ሰብስቦ ያሰራቸውን፣ 72 ሀያላን መናፍስት የሚባሉትን በግላቸው እያወጣሁ ማጥናት ውስጥ ገባሁ፡፡
ለምሳሌ BAEL (ባኤል) በምስራቅ ያሉት መናፍስት እንደሚመራ፣ አንድን ሰው መሰወር
የሚችል፣ ወደ 66 ሌጊዮኖችን እንደሚመራ፣ ድምፁ እንደ ፈረስ ሆኖ በአይን ሲታይ አንዳንዴ እንደ እንቁራሪት፣ አንዳንዴ እንደ ድመት፣ አንዳንዴ ደግሞ እንደ ሰው ሆኖ ራሱን ማሳየት እንደሚችል ተረዳሁ፡፡ ይህንንም መናፍስት ለመጥራትና በአካል ለማዋራት የሚያስኬደውንም ርቀት፣ እልህ አስጨራሽ በሆነ የእውቀት መንገድ ውስጥ ሄጄ ደረስኩበት፡፡ ከዛስ?…
እሱን ሌላ ጊዜ፡፡
በአንድ መፅሐፍ እውቀት ብቻ ነፍሴ እንደማትረካ ስለተረዳሁ፣ ይህን መፅሐፍ አዘጋጅቶ ያቀረበውን ፀሀፊ ስም ተመለከትኩ፤ Aleister Crowley ይባላል፡፡ ከዚህ በፊት ስለዚህ ሰው ጥቂት ብያችሁ ነበር፡፡ በሀያ አንደኛው ዘመን ላይ ላለው የአስማት አለም፣ እንደ አባት የሚጠራ ሰው ነው፡፡ እጅግ ብዙ መጻሕፍትን አሳትሟል…ጊዜና እድል አግኝቼ
ካነበብኩለት መጻሕፍት መካከል እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው… The Book of the Law, Meditation, The book of Thoth, The Heart Of The Master, The Necronomicon, The Complete Astrological Writings, 777, The Vision and The Voice, Book 4 Part III Magick in theory and practice 1-4…ናቸው፡፡
ሰውየው እጅግ እውቀት የጠገበ ነው፡፡ በዛው ልክ ጨለማ የሆነ ህይወቱን የሚረዳ ሰው አንዱንም መፅሐፉን ከመግለጥ ይቆጠባል፡፡ እኔን ግን ሳበኝ፡፡ አንዱን መፅሐፍ ስታነቡ ወደ አንዱ መፅሐፉ ይመራችኋል፡፡ የጥበቡ ፍሰት ማቆሚያ የለውም፡፡ የሰው ልጅ ከመረዳቱ በላይ የሆኑትን አለማት በጠንካራ ቃላት እየደረደራቸው፤ በሚስጥር ላይ ሚስጥር እየከመረ፣ በቅደም ተከተል ለአዕምሮ የሚመች እውቀት ጋር ያደርሳችኋል፡፡
ሰውየው ያልነካካውና እኔንም ያልመራኝ የአስማት እውቀት ያለ አይመስለኝም፡፡ ከነዚህ
የምትሀታዊና ሚስጥራዊ እውቀቶች መካከል Ceremonial Magic, Chaos Magick, enochian calls, Kabbalah, Geomancy, Gematria, Tarot card reading, Sprit summoning እና ፅፌ የማልጨርሳቸው Spells እና Incantations አሳይቶኛል፡፡ በዚሁ ሰውዬ መፅሐፍት ምክንያት ስለ A.’. A.’, Golden Dawn, O.T.O, Thelema እና Hermetic ን የመሳሰሉ ሚስጥራዊ ማህበራትን ማወቅ ችያለሁ፡፡ እነዚህን ሁሉ ጉዶች ሲመሰጥር የከረመው ክራውሌይ፤ ከመድረክ ላይ ምትሀት በላይ የሆነውን
እውነተኛውን የአስማት እውቀት ስሙን ከ Magic ወደ Magick ቀይሮታል፡፡ ይህም በራሱ አገላለፅ አስማትን (Magick)ን ሲተረጉመው እንዲህ እያለ ነው… “the science and art of causing change to occur in conformity with will”ይህም ማለት አስማትን ለመስራት የሚያስፈልገው ከመናፍስት ጋጋታ በላይ ከውስጣችን ያለው ነፃ ፍቃድ መሆኑን እንረዳለን፡፡ የክራውሌ አላማ ግን ከዛም በላይ ነበር፡፡ በዚህ እሱ The Great Work ብሎ በሚጠራው Experiment ውስጥ ዋናው አላማ፣ ከጠባቂ መላዕክቶቻችን ጋር የሚያገናኘን
ጥበብ ድረስ እንድንጓዝ ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ጥበባዊ መሰላል ተመቻችተን በስተመጨረሻ ላይ ወደ GODHOOD ማንነታችን ጋር መድረስ ነው
አላማው፡፡
ይሄም አሁን ላይ ታላቁ ሚስጥር እየተባለ በሚጠራው መፅሐፍ ውስጥ ያለ እንደ The Law
Of Attraction የመሳሰለ፣ ከዚህ ሳይንሳዊ ፍልስፍና ውስጥ ተመዝዞ የወጣ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በቴሌማ ፍልስፍና ውስጥ እንደ ታላቅ ስራ ተቆጥሮ ስሙ የሚጠራለት መፅሐፍ አለ…አሁንም ድረስ ተከታታይ መፅሐፍቱ በመውጣት ላይ ናቸው፡፡ የመፅሐፉ ርዕስ equinox፡ THE OFFICIAL ORGAN OF THE A.’. A.’. THE REVIEW OF SCIENTIFIC ILLUMINISM ይባላል፡፡
መፅሐፉ ፊት ገፅ ላይም ይህን አባባል ታነባላችሁ…
“THE METHOD OF SCIENCE—THE AIM OF RELIGION” ይህም እውቀቱ ከሁለት
ፅንፍ እውቀቶች ውስጥ ተመሳጥሮ መበጀቱን ይጠቁመናል፡፡
እነዚህን መጻሕፍት ለማንበብ አመታት በላዬ ላይ አልፈዋል፡፡ ከሰው ጋር የነበረኝ ግንኙነት ላይ ተፅዕኖ ፈጥሮብኛል፡፡ ከምንም በላይ ብቻዬን ሆኜ አርምሞ እንዳደርግ የእውቀቱ ፀበል ከወደዛ መራኝ፡፡ ከሰው ይልቅ ሰው ያልሆነ አለም ናፈቀኝ፡፡ ምድር ላይ አደገኛው ፍጥረት የሰው ልጅ ከሆነ፣ ስለምን ይሄ ጨካኝ ፍጥረት የሸሸገብኝን እውቀት የደረሰበት
ደርሼ ደባውን አልረዳውም ወደሚለው የፍለጋ ትግል ውስጥ ገባሁኝ፡፡
ወደ ሀገራችን አስማቶች ፊቴን አዙሬ በድፍረት መልካ ሰይጣን የሚሉትን ድብቅ መፅሐፍ ማሰስ ውስጥ ገባሁ…ለምን ሸሸጉት በሚል አፍላ ሰበብ፡፡ በኮከብ ቆጠራ እውቀት ውስጥ ጥቂት ሰንብቼ፣ በኛና በከዋክብቱ መካከል ያለውን ጥምረት አጠናሁ፡፡ ሓሳበ ፊደል ወፍካሬ ጠባያት እና በፍካሬ ከዋክብት ጥበብ ውስጥ ገብቼ በስምና በቁጥር ሰበብ የአስራ ሁለቱንም ከዋክብት ስምና ባህሪይ ለመገንዘብ ሞከርኩ፣ ጠልሰሞችን ሰብስቤ ከፊቴ በመደርደር ምንም እንደማይገባኝ እያወኩኝ በስዕላቸው ውስብስብነት ተደመምኩኝ፤ እፀ ደብዳቤን የቻልኩት ድረስ መርምሬ የዕፅዋትን ጥበብ በጥቂቱም ቢሆን ለመረዳት ሞከርኩ፤ የባህረ ሀሳብና የአቡሻክርን የጊዜ ቀመር ተገንዝቤ የቁጥሮችን ጥበብ አከበርኩ፡፡ ሊተ ለገብርከ……በምትል ሀረግ ውስጥ
የአንድን ሰው የክርስትና ስም በመክተት በድግምት ሰበብ፣ የዛን ሰው እጣፈንታ በጥሩም ሆነ በመጥፎ መከሸን እንደሚቻል የብራና መጻሕፍት ጠቆሙኝ፡፡ በመላዕክትና በፈጣሪ ህቡዕ ስም ተከትቦ የተበጀው የአንገትና የክንድ ክታብ፣ ከምድር መንግስት በላይ አንድን ሰው ከሀያላን አጥፊዎች ጥቃት እንደሚጠብቅ ተገነዘብኩ፡፡ በነጭ አስማትና በጥቁር አስማት
መካከል ያለውን የጭካኔንና የማዳንን አቅም እሬት እሬት እያለኝ በረበርኩት፣ የራሴን Book of Shadow አዘጋጅቼ ሌሊቱ የሚገብርልኝን ህልም መዝግቤ ያዝኩኝ….ይህ ሁሉ ወደ የት ሰደደኝ? ወደ ራሴ…
የእውቀት ባህር የሆነችው ሀገሬ ላይ ሆኜ ህይወትን ከሞት ላስታርቅ እየሞከርኩ መሰለኝ፡
፡ የምትሀቱ አለም ማብቂያ የሌለው አማራጭ ሁለንታን የሚሰራ እንደሆነ ነፍሴ ሰበከቺኝ፡፡
ኪሩቤል የሚባለውን ሰው እንደማላውቀው ገባኝ፡፡ የማይታየውን ማየት የሚችል፣ የማይሞከረውን እውነት የሚያደርግ፣ የማይታሰበውን ሀሳብ በድፍረት የሚተርክ፣ የማይነካውን አለም ዳሶ የሚያረጋግጥ ኪሩቤል፣ አሁን ያለው ኪሩቤል ውስጥ እንዳለ ደረስኩበት፡፡ አማራጭ እንዳለኝ ገባኝ፡፡
የሰበሰብኩት…ስለራሴ ያለኝን እውቀት በአንድ ሌሊት ድራሹን አጥፍቼ አዲሱን ማንነቴን መፍጠር እንደምችል የዚህ ጥበብ ጉዞ አስተማረኝ፡፡ በሁሉም የተፈጥሮ ስርዓት ውስጥ በምድር ቃላት ለመተረክ የሚከብዱ ሚስጥራት ታትመዋል፡፡ በነዛ ሚስጥራት ውስጥ ህይወቶች እየተመላለሱ እንደሆነ የሚረዳው የነፍሱን አይኖች የከፈታቸው ብቻ ነው፡፡
ልክ እንደ ሌሎች ሀይማኖቶች የአስማት ጥበብን የሚያስተምሩ የጥበብ ቤቶች የራሳቸው የሆነ የደረጃ እርከኖች አሏቸው፡፡ ለምሳሌም ያክል በቴሌማ ስርዓት ውስጥ አንድ ሰው ከፍተኛው የማንነት እውቀት እርከን ላይ (Magus) የሚደርሰው በቅድሚያ The Probationer፣ The Neophyte
(he builds up the magic Pentacle) ፣ The Zelator (he is given two editationpractices corresponding to the two rituals DCLXXI and CXX.) ፣ The Practicus (He is given a meditation-practice on Expansion of Consciousness. He is given a meditationpractice in the destruction of thoughts. ) ፣ The Philosophus (He is given a meditationpractice on the Senses, and the Sheaths of the Self, and the Practice called Mahasatipatthana. He meditates upon the diverse knowledge and power that he has acquired, and harmonizes it perfectly.) የሚባሉትን ደረጃዎች ማለፍ አለበት፡፡ ይህም A Syllabus of the
steps upon the Path , liber XIII Vel Graduum Montis Abiegni) በተሰኘው መፅሐፋቸው ውስጥ ገልፀውታል፡፡ ሁሉም ስራ የሚሰራውም ማንም ላይ ሳይሆን
ራስ ላይ ነው፡፡ የሚታየውም ምትሀት የሚከሰተው በቅድሚያ ከሌላ ቦታ ሳይሆን ከውስጥ ነው፡፡ እዚህ ውስጥ ማብቂያ የሌለው ውበት ይታየኛል፡፡ ማብቂያ የሌለው ሁለንታን ከርቀት ያስጎበኘኛል፡፡ የዚህን ቀውስ ፈላስፋ ንግግር Magick without Tears ከተሰኘው መፅሐፉ ውስጥ ቆርሼ ላጉርሳችሁና ልሰናበት…
“There is no limit to the extent of the relations of any man with the Universe in essence; for as soon as man makes himself one with any idea, the means of measurement cease to exist. But his power to utilize that force is limited by his mental power and capacity, and by the circumstances of his
human environment.” “We who accept the Law of Thelema, even should we concur in this doctrine theoretically, cannot admit that in practice
the plan would work out; our aim is that our Nothing, ideally perfect as it is in itself, should enjoy itself through realizing itself in the fulfillment of all possibilities. All such phenomena or “point-events” are equally “illusion”; Nothing is always Nothing; but the projection of Nothing on this screen of the phenomenal does not only explain, but constitutes, the niverse. It is the only system which reconciles all the contradictions inherent in Thought, and in Experience; for in it “Reality” is “Illusion”, “Free-will” is “Destiny”, the “Self” is the “Not-Self”; and so for every puzzle of Philosophy.”

Read 1404 times