ጨቅላ ህጻናት የተሟላ ጤንነት ይዘው ቢወለዱም እንኩዋን ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደ ረገላቸው በቀላሉ እንደሚሰበሩ እቃዎች ተደርገው
ሊታዩ ይገባል፡፡ ጨቅላ ህጻናት አንዳንድ ጊዜ ከክብደት በታች ሆኖ መወለድ፤የመወለጃ ጊዜያቸው ሳይደርስ የመወለድ እጣ ሊገጥ ማቸው ይችላል፡፡ እነዚህን ጨቅላዎች ተንከባክቦ ሰው የሚባለው ደረጃ እንዲደርሱ ለማድረግ በእንክብካቤ የሚቆዩባቸውን ቦታዎችና በእንክብካቤ የሚይዙአቸው የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲሁም ልጅዋን አስፈላጊውን መስዋእትነት ከፍላ የምትንከባከብ እናት ፤እናትየውን በማገዙ ረገድ ደግሞ አባትየውባጠቃላይም ሁሉምድርሻ አላቸው፡፡ጨቅላ ህጻናት ከአያያዝ ጀምሮ የሚደረግላቸው እንክብካቤ ከሌሎች ህጻናት ይለያል፡፡በአገራችንም ሆነ በውጭው አገር የጨቅላ
ህጻናቱ ጤንነት መታከም አለመቻል ፤ኢንፌክሽንና ጊዜያቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ልጆች ይበልጥለጉዳት እንዲያውም ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡ ስለዚህ
እነ ሱን ማዳን መቻል ትልቅ ነገር ነው ብለዋል ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ፡፡ በዚህም ረገድ በየሆስ ፒሎቹ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ወደ ጤና ጣቢያም ዝቅ እንዲልና ባለሙያዎች እንዲ ሰለ ጥኑ ሁኔታዎች የተመቻቹበት እድል መኖሩን ባለፈው እትም ቀንጨብ ማድረጋችን አይዘ ነጋም፡፡ዶ.ር ሙሉአለም ገሰሰ የሙሉ ጂ ሆስፒታል ባለቤት ከሆኑት አንዱዋ ባለፈው እትምም እንደገለጹት እሳቸው የህጻናት በተለይም የጨቅላ ህጻናት ህክምና እስፔሻሊስት ከመሆናቸው አስቀድሞና ከሆኑም በሁዋላ በዚህ ዙሪያ ያሉትን ክፍተቶች ለመዝጋት የቻሉትን ሁሉ ጥረ ዋል፡፡ ከዚያም ያመሩት የግላቸውን ሆስፒታል ወደ ማቋቋም ነበር፡፡ ከባለቤታቸው ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ጋር በህብረት የመሰረቱት ሙሉ- ጂ የጤና አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ሆስፒታሉ የውስጥ
ደዌ ሕክምና ፤የህጻናት ህክምና ፤እንዲሁም የማዋለድ አገልግሎትን የሚሰጥ ነው፡፡ ሆስፒታሉ የጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ መስጫ የተለየ ክፍልም
አለው፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም በተለይም አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦችን ህጻናት በነጻ ህክምና በመስጠት ለማዳን በመንግስት ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን ለካስ በግልም ይቻላል የሚለውን ያዩበት እና እድሉንም ለብዙ ልጆች የሰጡበት፤ ህጻናቱን ከሞት ያተረፉበት ሁኔታ በመኖሩ እጅግ ደስተኛ ናቸው፡፡ ዶ/ር ሙሉአለም ስልጠና አስፈላጊ በመሆኑ የስልጠናውን መመሪያ አዘጋጅተው ሲፈቀድላቸው ነርሶችን ማሰልጠን የመሳሰለውን ከብዙ የህጻናት ሐኪሞች ጋር
በመተባበር በመሰራቱ የህጻናቱ ሞት ከ37% ወደ 21% የደሰረበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁን ግን ተመልሶ ወደ33% በማሻቀቡ እጅግ አዝኛለሁ ብለዋል ፡፡
በኮሮና ህመም ምክንያት ዶ/ር ሙሉአለም ለ45 ቀናት ያህል በራሳቸው ጤንነት ላይ ማተ ኮር ግድ ስለነበረብኝ በዚያው አጋጣሚ እረፍት በመውሰድ
ሁኔታዎችን ሳስብ በተናጠል ለእናቶች፤አብረውኝ ለሚሰሩ ጭምር ብዙ ምክር የምለግስ ሲሆን ይህንን እድል የማያገኙ፤ እኔ የማላገኛቸው ብዙዎች መኖራቸውን አሰብኩ ይላሉ ዶ/ር፡፡ ስዚህ በአማርኛ ያልተጻፈ ፤ነገር ግን ለእናቶች በጣም ጠቃሚ የሆነ ስለእናቶችና ህጻናት የተጻፈ መጽሐፍ ስላለ ይህንን ለምን አልተረጉም ላቸውም በሚል ከማርገዝ በፊት፤ ስለእርግዝናው፤ በመውለድ ጊዜ፤ልጅ በማሳደግ ወቅት ምን ሊያውቁ ይገባቸዋልየሚለውን ሁሉ ተርጉሜ ጻፍኩ፡፡ በተጨማሪም ካለእድሜአቸው ለሚወለዱም ጽፌአለሁ፡፡ ነገር ግን አሁንም አይበቃም አልኩ፡፡ ይህንን ምን ያህል ሰው ሊያገኘው እና ሊማርበት ይችላል የሚለውን አሰብኩ፡፡ ስለዚህም በቀጣይ ያደረግሁት ለእናቶች ስለ እያንዳንዱ በሽታ ትምህርት መስጠትየሚቻልበትን መንገድ መቀየስ ነበር ፡፡ ሁልጊዜ በምሰራው ስራ ቤተሰቤን ኪሳራ ውስጥ የማስገባ ብሆንም ቤተሰቤ ግን ስለማያማርረኝ እድለኛነኝ፡፡ ምንጊዜም የማስበው ነገር ብዙ ጊዜ ለሞት ከሚያደርስ ህመም እግዚአብሔር ያዳነኝ ያልሰራሁት ስራ ስላለ ነው የሚለውን ነው ብለዋል ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ የህጻናት በተለይም የጨቅላ ህጻናት እስፔሻሊስት ሐኪም፡፡ እናቶች ምንጊዜም የስልክ ቁጥሬን ያገኛሉ፡፡ እሰጣቸዋለሁ፡፡ በቤት ውስጥ ሊኖር የሚችለውን ችግር በጉብኝት ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡ ለምሳሌ በየሳምንቱ ልጄ ሳል ያመዋል ብላ የምትመጣ እናት ትኖራለች፡፡ ምናልባት የምትኖርበት ቤት ግድግዳ ፈንገስ ቢኖረውስ የሚለውን መጠራጠር ይገባል፡፡ ስለዚህ ያንን ማጽዳት ይገባል፡፡ ከሚመገበው ምግብ የትኛው ነው የማይስማማው?ልጁዋን አለርጂክ የሚያስይዝባት የትኛው ምግብ ነው? የሚጠቅመው የትኛው ምግብ ነው ?ይህንንማስተማር ይገባል፡፡ አንዲት እናት እንዴት አድርጋ ኢንፌክሽንን እንደምትከላከል ማስተማር ለልጁ ጤና ወሳኝ ነው፡፡በተጨማሪም አንዲት እት ልጁዋ መቼ ነው መሳቅ የጀመረው፤መቼ ነው መቀመጥየጀመረው፤መቼ ነው መዳህ የጀመረው፤መቼ ነው ለመሄድ ጥረት አድርጎ የተነሳው፤መቼ ነው መሄድ የጀመረው የሚለውን በእድሜው መሰረት መታየት አለበት፡፡ ሌላው ነገር በዚህ እድሜው ክብደቱ ይህን ያህል መሆን አለበት፤ቁመቱ ይህን ያህል መድረስ አለበት የሚለውን ሁሉ በሰንጠረዥ እና ትየው ይዛ እንድትከታተል እና ወደሐኪምዋ ስትቀርብ እንድታስረዳ ስልጠናው ይሰጣታል፡፡ እስከ ስድስት ወር ድረስ ጡት እንድታጠባ እና ከዚያ በሁዋላ
የምትሰጠውን ምግብ እና መጠን ፤ሰአት ሁሉ በጨመረ መንገድ በሰንጠረዥ ይሰጣታል፡፡ በተቻለ መጠን የታሸገ ምግብ እንዳትሰጥ እና በአገር ውስጥ
ያሉ ፍሬሽ የሆኑ ምግቦችን እያበሰለች እንድትሰጥ ምክር ትለገሳለች፡፡ የዚህም ውጤቱ አስተሳሰቡ የዳበረ፤ሩህሩህ ፤ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድን
በቀጣይ ለማፍራት እንዲቻል ያግዛል ፡፡ አስተዳደጉና አመጋገቡ የተዛባ ህጻን ወደፊት ሲያድግ ጨካኝ ወይም ነ ጭናጫ እ ንደሚሆን ጥ ርጥር የ ለውም፡፡ ይህን በማድረግ የራሴን ድርሻ ለመወጣት ጥረት አደርጋለሁ፡፡ በ37 አመት የስራ ጉዞዬ ሌላው የታዘብኩት ነገር የዘንድሮ እናት በተለያዩ ቦታዎች በስራ ላይ የተሰማራች ልትሆን ትችላለች፡፡ ስለዚህ ልጅዋን የምትሰጠው ለሞግዚት ነው፡፡ ሞግ ዚትዋ ደግሞ ስለልጅ አስተዳደግ ምንም የማታውቅ የተነገራትን ብቻ ልታከናውን የምትችል ልትሆን ትችላለች፡፡ ሞግዚቶች ስለቫይታሚን እጥረት፤በጊዜው ተነስቶ ስላለ መሄድ …ወዘተ ባጠቃላይ ስለህጻናቱ ምንም የሚያውቁት ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ልጁ ሲተ ኛልሽ ወጥ ሰርተሽ፤እንጀራ ጋግረሽ …ወዘተ…የቤት ስራ ሰርተሸ ቆዬ የምትባል ልትሆን ትችላ ለች፡፡ ስለዚህ በተፈጥሮ ካለምንም ክፍያ የምናገኘውንየፀሐይ ብርሀን እንኩዋን ሳያ ገኙ በቫይታሚን ዲ
እጥረት የሚሰቃዩ ህጻናት ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሞግዚቶችን ማስተማር አንድ የስራ ዘርፍ መሆንአለበት ከሚል ለአስር ቀን ያህል እየሰለጠኑ ወደ ስራ
እንዲገቡ እናመቻቻለን ብለዋል ዶ/ር፡፡ ዶር ሙሉአለም መክሊትን እንዲህ ብለውገልጸውታል፡ ‹‹…እግዚአብሔር ለሰዎችለግማሹአንድለሌላውሁለት፤ሶስት፤አራት እያደረገ ይሄ መክሊ ታችሁ ነው ለግማሹአንድለሌላውሁለት፤ሶስት፤አራት እያደረገ ይሄ መክሊ ታችሁ ነው፡፡ በእውነት ሰርታችሁ አትርፋችሁ ይዛችሁ ተመለሱ ብሎ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ሰዎ ቹም ሰርተው፤አትርፈው ሲመጡ አንዱ ግን ሳይጠቀምበት ፤እንዲያውም
ሳይጠፋብኝ ልመ ልስለት ብሎ ቀብሮ ካስቀመጠ በሁዋላ መልሱ ባለው ጊዜ መክሊቱን ሳይጠቀምበት ያንኑ የወሰደውን መለሰለት፡፡ ስለዚህ አንደኛው…
እናት መክሊቱ ናት፡፡ ልጅ ወልዳለችና ለልጅዋ መንሰፍሰፍ አለባት፡፡ ሁለተኛው እናት ሶስት አራት ብትወልድ እራስዋን ካልጠበቀች ለልጆችዋ ዋጋ
የላትም፡፡ በመደሰቻዋ ጊዜ ልትሞት ትችላለች፡፡ ስለዚህ እናት ከመውለድዋ በፊት፤በመውለድዋ ጊዜ፤ከወለደች በሁዋላ ምን አይነት በሽታዎች
ሊያጠቋት ይችላሉ? የሚሉትና የመሳሰሉትን ነገሮች በማወቅ ረገድ ክፍተት እንዳይኖረን ለማድረግ ስልጠና መስጠት ግድ ስለሆነ መክሊት በሚል ስም
መስርተነዋል፡፡ ብዋል ዶ/ር ሙሉአለም፡፡ ሙሉ ጂ ሆስፒታል እናቶች ልጆቻቸውን ለማሳከምም ሆነ የእርግዝና ክትትል ለማድረግሲመጡ መክሊት የተባለ የስልጠና ማእከል መኖሩን እና ሊሳተፉ እንደሚችሉ መረጃው ይሰጣቸዋል፡፡ ፈቃደኛ የሚሆኑት አባል ይሆናሉ ፡፡ በዚህ ጊዜየያዙት ልጅ በደንብ ሁለ መናው ይጠናል፡፡ የቀድሞታሪኩ፤ቁመት እና ክብደቱ፡ የመሳሰለው ሁሉይታያል፡፡ ልጁ አሁን ያለበትን እና ቀድሞ የነበረውንሁኔታ በማገናዘብ የላቦራቶሪ ፍተሻ ጭምር ከተደረገበሁዋላ እ ናትየው ል ጅዋ ሲ ታመም ወ ይም በ የወሩ እየተደወለላቸው ስለ ልጃቸው ሁኔታ ጥያቄይቀርብላቸዋል፡፡
መክሊት ከወላዶች ጋር ለሚያደርገውግንኙነት የ ቴሌግራም ቻ ናልም አ ለ፡፡ በ ቴሌግራምየማህበሩ አባላት በቀጥታ እርስ በርሳቸውየሚወያዩበት፤በዚያ ያሉት ባለሙያዎች ከዶ/ር ሙሉ ጋር የሚገናኙበት፤አባላት ሐኪማቸውን የሚያማክሩበት…በሚል የተለያዩ መስመሮች ስላሉበግልጽ ውይይት ይካሄዳል፡፡ የመክሊት አባል በመሆን ብዙ ትምህርት ይገኛል፡፡ በምርመራ ወቅት ስለሚደረገው ነገር ሁሉ ጠይቀው የመረዳት መብትአላቸው፡፡ እኛጋ የጀመሩትን ሕክምና ታሪክ የትምሆነው ቢጠይቁ፤ለልጃቸው ሊያደርጉ ያሰቡትን ነገር ለሐኪማቸው ደውለው ቢያማክሩ መልስ ያገኛሉ፡፡ትልቁ ነገር ቅርብ መሆን የሚችሉበት ነው ብለዋልዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ የህጻናትና የጨቅላ ህጻናትሕክምና እስፔሻሊስት እንዲሁም ከባለቤታቸውዶ/ር ገመቺስ ማሞ ጋር የሙሉ ጂ ሆስፒታል ባለቤት፡፡
Saturday, 16 December 2023 20:38
ገና ያልሰራሁት ስላለ ከሞት ተርፌአለሁ
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ