Wednesday, 03 January 2024 20:37

መላ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

መላ

የአለምን ጫጫታ ላፍታ ለማስታገስ
ሆድ ውስጡን ባሰሰ፤
ላገኘ በልቡ የህሊና ጩኸት
ከውጩ የባሰ፤
ልቡን ከሆዱጋ'፥ ላልቻለ ማስማማት
በበደል ተከ'ባ፥ ነፍሱን ለደከማት
.
ኑሮ ትግል ጣጣው፥
ንዋይ እድል እጣው፥
ሁሉም ግራ ሆኖ መሄጃ ላሳጣው፤
.
ጊዜ ነው አቃፊው፥
መጥፎን ከጥሩጋ' አጣምሮ አሳላፊው፤
.
ዝምታው ነው ጌታ፥
የጭንቀት ወራትን ባ'ርምሞ 'ሚረታ፤
.
ተስፋ ነው መድሀኒት፥
የነገን ሁኔታ ዛሬ ላይ 'ሚገምት፤
.
ፍቅር ነው መካሪው፥
ውሸትን ገፍትሮ ለእውነት መስካሪው፤
እምነት ነው አዛኙ፤
ጥፋትን ሳይቆጥር የልብን መዛኙ።
✍️ Sami Anteneh]

Read 419 times