Tuesday, 27 February 2024 00:00

ከ90 በላይ ዓለማቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት 8ኛው ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

8ኛው ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይና ጉባኤ በመጪው ሳምንት በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል  


8ኛው ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይና ጉባኤ የአልጀሪያ ብሔራዊ ተሳትፎን ጨምሮ በ12 አገራት መሰረታቸውን ባደረጉ ኩባንያዎች ተሳትፎ በመጪው ሳምንት ከየካቲት 28 – 30 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ  እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

በዚህ አውደ ርዕይና ጉባኤ ላይ ከ4ሺ የሚበልጡ የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት ከዓለማቀፍ የዘርፉ መሪዎችና ስመጥር የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

በዘንድሮው ኹነት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ40 በላይ ነጥብ የሚያሰጡ የተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ሥልጠናዎችና ጉባኤዎች ከ22 የሙያና የዘርፍ ማህበራት ጋር በመተባበር እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

ይህ ልዩ አውደ ርዕይና ጉባኤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና አቅራቢዎችን ለሀገራችን በማስተዋወቅ፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግርን በማምጣት ለዘርፉ ልማት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ መድረክ መሆኑን ያስመሰከረ ነው የተባለ ሲሆን፤ በዘርፉ ተዋናዮች መካከል የንግድ ልውውጥን በማሳደግና የገበያ ትስስርን በመፍጠር ደረጃ ቀጣይነት ያለው ዕድል የፈጠረ ኹነት እንደሆነ  ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይና ጉባኤን ለ8ኛ ጊዜ ያዘጋጀው በበርካታ ዘርፎች የንግድ ትርኢትና አውደ ርዕዮችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ፕራና ኢቨንትስ ነው፡፡

Read 509 times