Saturday, 13 April 2024 20:05

"ኢትዮጵያ ሪድስ" 4ኛውን ዓመታዊ የህፃናት ንባብ ጉባኤ አካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

- ለ22 ዓመታት በትምህርትና ንባብ ላይ በትጋት ሰርቷል
      - “በታዳጊ ክልሎች የልጆች የንባብ ክህሎት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው”
               
    ኢትዮጵያ ሪድስ አራተኛውን የህጻናት ንባብ ጉባኤ ከትላንት በስቲያ ሚያዚያ 3 ቀን 2016ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል የከፈተ ሲሆን፤
“ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ልጆችን በንባብ መደገፍ” በሚል መሪ ቃል ተጀምሯል። እስከ ትላንትና ሚያዚያ 4 ቀን በዘለቀው በዚህ ንባብ ጉባኤ፤ የድርጅቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴና ውጤት የተገለፀበት ሪፖርት፣ ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች ጥናት፣ የልጆችመፅሐፍት አውደ ርዕይና በአጠቃላይ በልጆች ንባብ ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይትም ተካሂዷል። በጥናት ውጤቱ በተለይ በታዳጊክልሎች ማለትም አፋር ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች የልጆች የንባብ ክህሎት በእጅጉ አሳሳቢ እንደሆነም ተብራርቷል።

ኢትዮጵያ ሪድስ /Ethiopia Reads/ ንባብበኢትዮጵያ ውስጥ እንዲስፋፋና እንዲጎለብት የሚሠራ ዋና መስሪያ ቤቱን በአሜሪካን ሀገር ሚኒአፖሊስ-ሜኒሶታ ስቴት ያደረገ የዉጭሀገር የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ላለፉት 22 ዓመታት በኢትዮጵያ ትምህርትን በማስፋፋት ሂደት በሚደረገው ተግባር ላይ በመሳተፍ፤ቤተ መፅሐፍትን በመገንባት እንዲሁም በመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ቤተ መፅሐፍትን በማቋቋም፣ ለቤተ መፅሐፍት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታስልጠና በመስጠትናበመከታተል እንዲሁም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር አጋዥ መፅሐፍትን ለትምህርት ቤትና ለህዝብ ቤተ- መጽሐፍቶች በመስጠት አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ ተንቀሳቃሽ የቤተ-መጽሃፍት ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ገጠር አካባቢ ለሚገኙ እና የንባብ እድል ላላገኙ ህጻናት በፈረስ/በአህያና በሰው ሀይል በመታገዝ መንደራቸው ድረስ በመሄድ የንባብ አገልግሎት የሚያቀርብ ሲሆን በዚህ ፕሮጀክት በደቡብ እና በኦሮሚያክልሎች ለሚገኙና ከ 8 ሺህ ለሚበልጡ ህጻናት በፈረስና በሰው ኃይል በመታገዝ በየመንደራቸው በመግባት፣ መጽሐፍትን ይዞ የንባብ አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ትምህርትና ቤተ-መጽሐፍት ተኮር ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ በሁሉም የሀገራችንክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ሲሰራ የቆየ ሲሆን አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ቋሚ ቤተ-መፅሐፍትን በማቋቋም፣ በማደራጀትናበማስተዳደር በሐዋሳ እና በአዲስ አበባ ከተሞች የህጻናትና የሕዝብ ቤተ-መጽሐፍት በመክፈት በአካባቢው ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የንባብአገልግሎት በመስጠት እያገለገለ ሲሆን ድርጅቱ  ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በሀገሪቱ በሁሉም ክልሎች ከ70 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤቶች ውስጥ ቤተ መጽሐፍትን በማቋቋም ከመንግስት እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ በዚህም እስካሁን ድረስ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ መምህራንና ሌሎች የትምህርት ቤት ማኅበረሰብ በተለያዩ ትምህርትና ንባብ ተኮር ፕሮግራሞች ድጋፍ ስለማድረጉ በጉባኤው ላይ በቀረበው ሪፖርት ተብራርቷል።
    የድርጅቱ አብዛኛው የፕሮጀክት ትኩረት ህጻናት ላይ ሲሆን፤ ይህንንም ለማድረግ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ መቶ ሺህ የሚቆጠሩየሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር መጽሐፍትን በተለያየ መንገድ ለህጻናትና ለተማሪዎች ተደራሽ አድርጓል፡፡

ከመጽሐፍ ህትመት ጋር ተያይዞድርጅቱ ከዚህ በፊትካሳተማቸው መጽሃፍት በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜም Ready- Set-Go በሚል መጠሪያ ከOpen Hearts big Dreams Foundation ጋራ በጋራ በመሆን ከ200 ሺህ በላይ የሕጻናት መጽሐፍትን (Story Books) በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሲዳምኛ ፣ አፋርኛ፣ ትግርኛ ፣ ጉሙዝ፣ሺናሻ ፣ ዲዚኛ እና ጠምባሪሳ፣ 45 በሚደርሱ ርዕሶች በማዘጋጀትና በማሳተም በተለያዩ የሃገሪቱ ክልል ከተሞች በሚገኙ ት/ቤቶችና የንባብ ማእከላት ውስጥ በነጻ አሰራጭቷል፡፡ ይህንንም ስራ በማስፋት በሀገራችን በግጭት ምክንያት ከት/ቤት ለተስተጓጐሉናየስነልቦናናሌሎችግጭትየሚፈጥራቸው ችግሮች ተጎጂ የሆኑ ልጆችን ለማገዝ የሚሆኑ የተለያዩ ይዘት ያላቸው 80,000 የልጆች መጽሃፍትን በየቋንቋው አሳትሞ እያሰራጨ ይገኛል፡፡

ይህም ስራ መጽሃፍት ልጆችን ከድብርት በማውጣት ተስፋ እንዲኖራቸውና ከት/ቤት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የቀረባቸዉን መሰረታዊ ትምህርት በቤታቸው ሆነው እንዲማሩ የሚያደርግ መሆኑ ታውቆ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎች ላይ ከሌሎች የእርዳታ ስራዎች እኩል እንዲታይና እንዲካተትየሚያስገነዝብ ነው፡፡      በተጨማሪም ድርጅቱ በሚሰራቸው ንባብ እና መጽሃፍ ተኮር ስራዎች የሆሄ ሽልማትን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩማበረታቻዎች እና እውቅናዎች ከተለያዩ አካላትአግኝቷል፡፡


    በአጠቃላይ ድርጅቱ የመማር የማስተማር ሂደቱ መጽሀፍ ተኮር እንዲሆንእና የተሻለ ጥራት እንዲኖረው በመደገፍና በማሳደግሂደት ውስጥየራሱን ጉልህ ሚና እየተጫወተ ሲሆን በተለይም የቅድመ መደበኛ የልጆች የንባብ ልምምድ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠውከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ እንደሚገኝ የኢትጵያ ሪድስ ሃላፊዎች ገልፀው፡፡ በመሆኑም መንግስትም ሆነ ሌሎች የትምህርት ጥራትን በተለይም የንባብ ባህልን ለማሳደግየተቋቋሙ
ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ድርጅቱ የሚሠራቸውን ሥራዎች በማየት በተለያየ መልኩ ከድርጅቱ ጎን እንዲቆሙና ተባባሪእንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ጉባኤው ላይ የብሔራዊ ቤተ-መጻህፍትና ቤተ-መዛግብት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡን ጨምሮ ከትምህርትሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣ ከአገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችና ከተለያዩ ተቋማት የተጋበዙእንግዶች የታደሙ ሲሆን እውቅየህፃናትመጽሐፍት ደራሲያንና ከያንያንም ተገኝተዋል።


Read 670 times