Saturday, 13 April 2024 20:10

የፖለቲካ ፓርቲዎች የአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ተጣርቶ ይፋ እንዲሆን ጠየቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

    መንግስት የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ በአፋጣኝ አጣር ለህዝብ ይፋ ማድረግ አለበት ሲል ኢዜማ ገለጸ። አቶ በቴ ሃሳባቸውን በግልፅና በሰከነ መንገድ የሚገልፁ፣ ጮክ ብለው እንኳን የመይናገሩና የተረጋጉ በሳል ፖለቲከኛ ነበሩ ያሉት የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ በተፈጸመባቸው የግፍ ግድያ በእጅጉ ማዘናቸውን ተናግረዋል።

“ግድያቸው ፖለቲካዊ ነው ተራ ግድያ የሚለውን ለመገመት ያስቸግራል ያሉት ዶ/ር ሙሉአለም”፤ መንግስት ገለልተኛ አካል በአስቸኳይ አቋቁሞ የግድያቸውን ሁኔታ ይፋ ማድረጉ ላይ ዳተኝነት ካሳየ ግን፣ ግድያው ፖለቲካዊ ነው ወደሚለው እንዳያጋድል ስጋት
እንዳላቸው ተናግረዋል። ባለፉት 6 ዓመታት ሰዎች በየቦታው እንደሚገደሉ ታዋቂ ሰዎችና ፖለቲከኞች እየተገደሉ እስከዛሬ እከሌ የተገደለው በዚህ
ምክንያት ነው፣ ገዳዮችም እንዲህ አይነት ቅጣት ተቀጥተዋል ተብሎ ይፋ ስለማይሆን ፖለቲካው ወርዶ ወርዶ ከጠረጴዛ እርቆ ጫካ ገብቷል
ሲሉ ሃላፊው ያማርራሉ። በምርጫው ወቅትም ግርማ ሞገስ የተባለ የኢዜማ አባል ቢሾፍቱ ላይ ተገድሎ እስካሁን ገዳዮቹ እንዳልታወቁ ዶ/ር
ሙሉዓለም አስታውሰው፣ ይህ ደግሞ የበለጠ ልብ ይሰብራል ብለዋል።

“ከ6 ዓመት በፊት ለውጥ ይመጣል፣ ዴሞክራሲ ይሰፍናል የበኩሌን ላዋጣ ብሎ ወደ ትግሉ ለገባ እንደኔ አይነት ሰው አሁን ያለው ሁኔታ በእጅጉ ያሳዝናል” ያሉት የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ሰዎች እየሞቱ ገዳዩእየተድበሰበሰ በሄደ ቁጥር ፖለቲካው ይበልጥ ከጠረጴዛ እየሸሸ ሀሳብ ያላቸውም ሰዎች እንደለለሁ በሚል እየሸሹ ሰላማዊ ትግል ጨርሶ ይጠፋል ብለዋል። ይህ እንዳይሆን መንግስት ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፣ የአቶ በቴ ኡርጌሳም ግድያ ልዩ አትኩሮት ተሰጥቶት በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ የግድያው ሁኔታና ገዳዮቹ ለህዝብ ይፋ መሆን አለባቸው ሲሉ አሳበዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የነበሩት የአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያበገለልተኛ አካል ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት ሲሉ የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት ሰይፈ ስላሴ አያሌው(ዶ/ር) ለአዲስ አድማስተናግረዋል፡፡

አቶ በቴ በፖለቲካው ንቁ ተሳትፎ ያላቸውና ሞጋች እንደነበሩ የገለፁት የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንት፤ በተፈፀመባቸው ግድያበግላቸውም እንደ ፓርቲም በእጅጉ ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ አቶ በቴ ላቅ ያለ ደረጃ ያላቸው ሞጋችና ንቁ የነበሩ ሰው እንደመሆናቸው ግድያቸውፖለቲካዊ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ያላቸውአቶ ሰይፈ ስላሴ፤ ይህ ከሆነ ደግሞ የአገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር የሚያጠብና ችግር የሚፈጥር በመሆኑ መንግስት በገለልተኛ አካል ግድያውን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ ማድረግና ገዳዮቹን ለፍርድ ማቅረብ አለበት ብለዋል፡፡


      “ከ1960ዎቹ ጀምሮ ላለፉት 50 ዓመታት ተከትሎን የመጣው የፖለቲካ ግድያ አገሪቱን ወደተሻለ ደረጃ ወስዷት ቢሆን ጥሩ ነበር” ያሉት የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንቱ፤ ይሁን እንጂ እንደዚህ አይነት ግድያዎች አገሪቱን ከድጡ ወደማጡ እየወሰዱ አሁን ላለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ ከመዳረግ ባለፈ ያመጡት ፋይዳ የለም ብለዋል፡፡ እንዲያውም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እስራትና እንግልት እየተባባሰናአገር ወደባሰ ቀውስ እየሄድ ነው ያሉት ሰይፈ ስላሴ፤ በቅርቡም አንድ የኢህአፓ አመራር መታሰራቸውንና ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ከፖሊስ ጣቢያ መሰወራቸውንአስታውሰው፤ ይህ ሁሉ የፖለቲካ ትግሉን ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ የሚወስድና አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡ ምንም እንኳ እናት ፓርቲና የኦሮሞ ነፃነትግንባር (ኦነግም) ሆነ እኔና አቶ በቴ በርዕዮተ ዓለም የተለያየን ብንሆንም፤ የምንታገለው ለአንድ አገር በመሆኑ፣ የእሳቸው ግድያለፖለቲካው ዓለም ያጎድላል ሲሉተናግረዋል፡፡


“በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ግድያው ፖለቲካዊ ከሆነ የተቃውሞ ፖለቲካን ዝም ለማሰኘት በተቃውሞ ጎራ ሆነው ትግል የሚያካሂዱ ሰዎች እንዲሸሹ የሚያደርግ ነውና በእጅጉ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ መንግስት በጉዳዩ ሊያስብበት ይገባል ብለዋል ሰይፈ ስላሴ (ዶ/ር)፡፡ የፖለቲካ ግድያዎች የሚካሄዱት ተቃውሞን ዝም ለማሰኘት ከሆነ ይህ ጭራሽ መሆን የለበትም የሚሉት የእናት ፓርቲ ፕሬዚዳንትበምድር የሚኖር ዘላለማዊ መንግስት የለምና ለሚያልፍ መንግስት ሰዎች መገደል መሰደድና መሰቃየት የለባቸውም ብለዋል፡፡የአቶ በቴ ግድያ ተድበስብሶ መቅረት የለበትም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ “እርግጥ ነው ከዚህ በፊቱ ልምድ በመነሳት ግድያዎች ተጣርተው ይፋ ሆነው አያውቁም ከዚህ አንፃርየአቶ በቴም ግድያ ተጣርቶ ይፋ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም ብለዋል፡፡

Read 800 times