Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 29 September 2012 09:57

ሳልማን ሩሽዲ አሁንም ይፈለጋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከ24 ዓመት በፊት ለንባብ ባበቃው “ሳታኒክ ቨርሰስ” የተባለ መጽሐፉ “ፋታዋ” (የሞት ቅጣት) የታወጀበት ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ ዛሬም እንደሚፈለግ ዋሽንግተን ፖስት ገለጸ፡፡ ሰልማን ከግድያ በመሸሸግ ስላሳለፈው ህይወት ሰሞኑን አዲስ መጽሐፍ ለገበያ አቅርቧል፡፡ ባለፈው ሰኞ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የተገኙት የኢራኑ ፕሬዚዳንት አህመዲን ነጃድ በምዕራባዊያን ጋዜጠኞች ስለሳልማን ሩሽዲ ተጠይቀው ማረጋገጫ አልሰጡበትም፡፡ በኒውዮርክ ከምዕራባዊያኑ ጋዜጠኞች ጋር በጉዳዩ ላይ የተነጋገሩት አህመዲን ነጃድ “ለመሆኑ የት ነው ያለው፣ አሜሪካ ነው እንዴ? ያለበትን ተናግራችሁ ጉድ እንዳታደርጉት” ብለዋል፡፡

በ1989 እ.ኤ.አ የኢራኑ ኃይማኖታዊ መሪ አያቶላህ ሆሚኒ “ሳታኒክ ሰርቨስ” የሚባለው መጽሐፉ የእስልምናን ክብር አጉድፏል በሚል የተወሰቀው ሳልማን ሩሽዲ ባለበት እንዲገደል ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሳልማን ሩሽዲን ለገደለ ወይም ያለበትን ለጠቆመ እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እንደሚከፍል የኢራን መንግሥት ይገልጻል፡፡ ሳልማን ሩሽዲ የግድያ አዋጅ ከመጣበት በኋላ ባልታወቁ ስፍራዎች በመደበቅ ሲኖር ቆይቷል፡፡  ላለፉት 30 ዓመታት በሙያው የሠራው ደራሲው በህንድ ቦምቤይ ውስጥ ነው የተወለደ፡፡ “ጆሴፍ አንቶን” በሚል ርዕስ በ633 ገፆች ሰሞኑን ለገበያ የቀረበለ64ኛው ኤሚ አዋርድ ትልልቅ ተዋናዮች ተሸለሙ

 

ው አዲሱ የሳልማን ሩሽዲ መጽሐፍ ትኩረት ስቧል፡፡

 

 

Read 4907 times Last modified on Saturday, 29 September 2012 10:03