Administrator

Administrator

በፊልሙ ላይ 70 የሚያህሉ ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን ሰለሞን ሙሄ ፣ መኮንን ላዕከ፣ ዘላለም ይታገሱ ፣ንጉሱ መልጌታ፣ፍቅረተ ደሳለኝ፣ ህይወት ጌታሁን፣ሰለሞን ተካ፣ችሮታው ከልካይ እና ሌሎች አንጋፍና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል ።

የቻይና ተመራማሪዎች ከአጥንት ስብራት ለማገገም ወራት ይፈጅ የነበረውን ሂደት የሚቀይርና በ3 ደቂቃዎች ውስጥ የተሰበረ አጥንትን የሚገጥም ግኝት ይፋ ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡
'ቦን -02' የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ግኝት፤ ተጨማሪ ቀዶ ጥገና ሳያስፈልግ የተሰበሩ አጥንቶችን የሚገጥም ነው፡፡
በሃንግዙ ሰር ሩን ሾው ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ባለሙያ የሆኑት ሊን ዢያንፌንግ እንደገለጹት፤ ሕክምናው በመርፌ መልክ የሚሰጥና የተሰበሩ አጥንቶችን በደቂቃዎች ውስጥ አንድ ላይ እንዲጣበቁ የሚያደርግ ነው።
'ቦን 02' በሰው አካል ውስጥ ከገባ በኋላ በተፈጥሮ መንገድ እንዲዋሃድ ተደርጎ መሰራቱም ተመላክቷል።
ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረው ማጣበቂያውን ለማስወገድ ሁለተኛ ቀዶ ጥገና ባለማስፈለጉም የኢንፌክሽን አደጋን ይቀንሳል ነው የተባለው።
በ'ዠይጂያንግ' ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በተሰራው በዚህ ግኝትም፣ ከ150 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሕክምና በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ኦዲቲ ሴንትራልን ጠቅሶ ኢቢሲ መዝናኛ አስነብቧል፡፡
የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ ድምጻዊ ጆኒ ራጋ፣ በአዲሱ "እሳት እና ውሃ" አልበሙ እና በአልበም ቅምሻ ፕሮግራሙ፣ ከቴክኖ ከሞን 40 ስልክ ሞዴል ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
ለበርካታ ዓመታት ድምጹ የጠፋው ጆኒ ራጋ ከሰሞኑ "እሳት እና ውሃ" የተሰኘ ሁለተኛ አልበሙን ይዞ መምጣቱ ይታወቃል፡፡
በአረርቲ ከተማ አስተዳደር አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል ላይ እየተሰራ ያለው ቤተክርስቲያን እየተጎበኘ ባለበት ‎ሰዓት፣ ለፊኒሺንግ ሥራ የተረበረበው እንጨት ተደርምሶ በርካታ ምዕመናን ላይ የሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።
እስካሁን ትክክለኛ የሟቾችና ተጎጂዎች ቁጥር አልታወቀም። አሁንም ሰዎችን ከተናደው ርብራብ የማውጣት ስራ እየተሰራ ነው።
የአረርቲ ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ፤ የጉዳቱ መጠን ከፍተኛ በመሆኑና ከእንጨት ርብራቡ ሥር ያልወጡ ሠዎች በመኖራቸው የጉዳት መጠኑን መገመት አስቸጋሪ እንደሆነ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጿል።
ከሆስፒታል በተረጋገጠው እስካሁን የ22 ሠዎች ሕይወት ማለፉን፣ በተጨማሪ 55 ሰዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አሳውቋል።
ለተጎጂዎች የመጀመሪያ ሕክምና በአንድ ሆስፒታል እና በ4 ጤና ጣቢያዎች እየተሠጠ ሲሆን፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሠባቸው 5 ተጎጂዎች ለተጨማሪ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ተልከዋል።
ተጎጂዎችን ለማትረፍ ኅብረተሠቡ ጥረት እያደረገ ሲሆን፤ አሁንም ድረስ ከርብራቡ ሥር ያልወጡትን ዜጎች ሕይወት ለማትረፍና ሕክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ ነው።
Tikvah-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ኬንያ ከውጭ ከምታገኘው አጠቃላይ የሃይል አቅርቦት 83 በመቶውን ኢትዮጵያ እንደምታቀርብ ተገለጸ፡፡ በዚህም ኬንያ በዓመት 10 ሚሊየን ዶላር ገደማ ማዳን ችላለች ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት እስከ ሰኔ 2025 ድረስ ኬንያ ከውጭ ካስገባችው ጠቅላላ የኤሌክትሪክ ሃይል 83 በመቶውን በመሸፈን ፣ የኬንያ ቀዳሚ የኃይል ምንጭ መሆኗ ተጠቁሟል፡፡
የኬንያው ካፒታል ኤፍ ኤም የአገሪቱን የኢነርጂና ነዳጅ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦት ከአገር ውስጥ የኃይል ማመንጫ የበለጠ ወጪ ቆጣቢ ሲሆን፤ ይህም ኬንያ በዓመት 10 ሚሊዮን ዶላር እንድታድን ያስችላታል፡፡
የኬንያው ቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ ጋዜጣ በበኩሉ፤ የኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦት በኬንያ ሊፈጠር የሚችለውን የኃይል ቀውስ በመከላከል ረገድ ወሳኝ ነው ሲል ገልፆታል፡፡
“ኢትዮጵያ ኬንያን ከመብራት መጥፋትና ከፈረቃ ታድጋለች” ሲልም ጋዜጣው ዘግቧል፡፡
AS-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ህወሓት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ዋስትና ሰጪ የሆኑት አሜሪካ፣ አውሮፓ ኅብረት፣ አፍሪካ ኅብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የገቡትን ቃል ተግባራዊ ሳያደርጉ ቀርተዋል ሲል ከሰሰ።
ፓርቲው ስምምነቱ ከተፈረመ ከሦስት ዓመታት በኋላም ቢሆን፣ በትግራይ ክልል “በዝምታ ውስጥ እየተፈጸመ ያለ ዘር ማጥፋት ቀጥሏል” ሲልም ገልጿል።
ህወሓት መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን ውድመት ለማስቆም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ አሳስቧል። አክሎም፣ “ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁን እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን። የትግራይ ውድመት በዝምታ እንዲቀጥል አትፍቀዱ። ለሰላም የገባችሁትን ቃል አክብሩ፣ ንጹሐንን ጠብቁ፣ እናም ሌላ አሳዛኝ ክስተት እንዳይከሰት ተከላከሉ” ብሏል።
ፓርቲው፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱና የተያዙ ቦታዎች እንዲለቀቁ ለማስቻል በህዳር 2022 የተፈረመው የፕሪቶሪያው ስምምነት በአብዛኛው ሳይተገበር ቀርቷል ብሏል። መግለጫው፣ “አብዛኞቹ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ አልተደረጉም፤ተፈናቃዮች ሳይመለሱ ቀርተዋል፣ የተያዙ ቦታዎችም አልተለቀቁም። አደጋው እየከፋ ሄዶ በዝምታ ውስጥ እየተፈጸመ ያለ ዘር ማጥፋት ቀጥሏል” ሲል አክሏል።
በተጨማሪም ፓርቲው፣ ዋስትና ሰጪዎቹ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለመቻላቸውንም በማውገዝ፤ “የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር፣ ኃይሎች ከያዙት ቦታዎች አስቸኳይ ለቀው እንዲወጡና ተፈናቃዮች በሰላም እንዲመለሱ” ጠይቋል።
አስ-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
May be an image of text
 
 
 
 
ኢትዮጵያ ምርቶቿን ከቀረጥ ነጻ በሆነ ሥርዓት ወደ አፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አባል ሀገራት መላክ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፤ መስከረም 29 ኢትዮጵያ አህጉራዊ ነፃ የሸቀጦች ንግድ ትግበራን በይፋ ታስጀምራለች ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ አባል ሀገራት ለመጀመሪያ ጊዜ ምርቷን ከቀረጥ ነፃ መላክ ትጀምራለች ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የንግድ ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር ተናግረዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ትግበራ፣ ከንግድ ቀጠናነት ባሻገር የአፍሪካ ዘላቂ ዕድገትን ለማረጋገጥ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል፡፡
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የውሃ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ፣ ሰሞኑን በሱዳን የተከሠተው ጎርፍ ከሕዳሴ ግድብ ጋር የተያያዘ አይደለም ማለታቸውን አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፣ አንዳንድ የግብጽ የውሃ ባለሙያዎች፣ የሱዳኑን ጎርፍ በሕዳሴ ግድብ ምክንያት የተከሠተ መኾኑን መግለጣቸውን ተከትሎ እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል።
ጎርፉ የኋይት ናይል ወንዝ ሙላት የፈጠረው ሊሆን ይችላል ያሉት አቶ ሐብታሙ፣ ግድቡ ባይኖር የጎርፍ አደጋው እጅግ የከፋ ሊሆን ይችል ነበር ብለዋል ተብሏል።
ግድቡ እንዲያውም ጎርፉ ከፍተኛ ውድመት እንዳያደርስ በመከላከል ረገድ ቁልፍ አስተዋጽዖ ማድረጉን ሚኒስትሩ መግለጣቸውንም ዘገባው አመልክቷል።
ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከግድቡ ትርፍ ውሃ አለመልቀቋንም ተናግረዋል ተብሏል።
ዋዜማ-
ቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በኢትዮጵያ ሀገራዊ የኤችአይቪ ስርጭቱ ካላፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም፣ ከክልል ክልል፣ ከከተማ ከተማ የስርጭቱ መጠን እንደሚለያይ ተነግሯል።
በተለይ በወጣቶችና ለኤችአይቪ እጅግ ተጋላጭ ተብለው የተለዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የመያዝ እድሉ በመጨመሩ መዘናጋት እንዳያስከትል ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት በኤድስ ሄልዝ ኬር ፋውንዴሽን (AHF) ኢትዮጵያ የኤችአይቪ መከላከልና ምክር አገልግሎት አስተባባሪ እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ቢኒያም ባዩ ናቸው።
በጠቅላላው የማህበረሰብ ክፍል ውስጥ ያለው የስርጭት መጠን ከዚህ ቀደም ከ 1 በመቶ በላይ ተሻግሮ የነበረውን በትብብር በመሰራቱ የስርጭቱ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ቢመጣም፣ በተለይም በስራቸውና በጾታቸው ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑንም አቶ ቢኒያም ይናገራሉ።
በወጣቶች በኩል የኤችአይቪ የመያዝ ቁጥርም ከፍተኛ ነው የሚሉት ባለሙያው፤ በኤችአይቪ መከላከል ላይ የሚሰሩ አዳዲስ ጥናቶች ወጣቶች ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
በቅርብ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱዩት በሰጠው መረጃ መሰረት፤ በወጣቶች ላይ ያለው የኤች አይቪ የስርጭት ሁኔታ 1.7 በመቶ እንደሚጠጋ የተነገረ ሲሆን፤ ከትምህርት ቤት ውጪ ባሉ ወጣቶች 2.2 በመቶና በትምህርት ቤት ባሉት ደግሞ 1.3 በመቶ ነው ተብሏል።
በአጠቃላይ ወጣቶችን ስንመለከት ካለው የኤችአይቪ ስርጭት ሁኔታ ከፍ ያለ መሆኑንና ከሌላው የማህበረሰብ ክፍል በተለየ ሁኔታ ከ10 እስከ 24 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ በቅርብ ጊዜ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ባለሙያው መጥቀሳቸውን ሸገር ዘግቧል፡፡
Page 10 of 794