
Administrator
1242.pdf addisadmassnews
የቴአትር እና የቴሌቪዥን ፌስቲቫል እየተካሄደ ነዉ
አትሌት ታምራት ቶላ የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተላት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጠውን የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተላት።
ሽልማቱ የተበረከተላት በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለው የስፖርት ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ላደረገችው አስተዋጽኦ መሆኑም ተገልጿል።
አትሌት ደራርቱ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሺንዞ አቤ በፈረንጆቹ 2014 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር እንዲወያዩ እድርጋ እንደነበር ተመላክቷል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2019 ላይም ደራርቱ የጃፓን ስፖርት ኤጀንሲ ኮሚሽነር ከሆኑት ሱዙኪ ዳይቺን እና የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሃላፊ ሃሺሞቶ ሴይኮ ጋር በመምከር የልምድ ልውውጥ ማድረጓ ተገልጿል፡፡
ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተሰጠው ይህ እውቅናና ሽልማት እኤአ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች በጃፓን መንግስት የሚሰጥ አንጋፋ የክብር ሽልማት መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።
ይህ ሽልማት የውጭ ሀገር ዜጎች በጃፓን እና በሌሎች ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሚሰጥ ሲሆን፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉም ይህን ከፍተኛ የክብር ሽልማት በማገኝት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።
አንጋፋውና ገናናው አርቲስት ስዩም ተፈራ የምስጋና ሽልማት ተሰጠው
አዲስ ዘመን ድሮ
ታሪክ ማንበብ ያ ል ኖ ሩ በ ት ን ዘመን ያስኖራል››
ይባላል።ይህ ማለት እኛ ባልነበርንበት ዘመን የነበረውን ሁነት ይነግረናል ማለት ነው።አዲስ ዘመን ጋዜጣ የተለያዩ ዘመናት የየዕለት ሁነት ሰንዶ ያስቀመጠ የ82 ዓመታት ታሪክ ነው።ጋዜጣው በሰነዳቸው መረጃዎቹ ያልነበርንበትን ዘመን እንድንኖረው ያደርገናል።በዚያ ዘመን፤ የመንግስት አስተዳደር እና የማህበረሰቡ ሥነ ልቦና ምን ይመስል እንደነበር፣ ምን ነውር ምንስ አስገራሚ እንደሚሆን፣ በዘመኑ የነበሩ ህግና
ደንቦች፣ የኑሮ ሁኔታ እና የመሳሰሉትን ያሳየናል።በማስታወቂያዎች፤ በዘመኑ የነበረውን የገበያ፣ የቅጥር፣ የሚከለከሉና የሚፈቀዱ ነገሮችን ይጠቁመናል።በዜናዎች ደግሞ የዘመኑን ክስተቶች ያሳየናል።እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል።በዘመኑ ጋዜጣ ላይ ይወጡ የነበሩ ዘገባዎችን፣ ማስታወቂያዎችን፣ ወዘተ. ዛሬ ላይ ሆነን ስናነባቸውና ስንመለከታቸው ‹‹አሁን ይሄ ዜና ይሆን ነበር? ጋዜጣ ላይ መውጣት ነበረበት?›› የሚያሰኙ ነገሮችን እናገኛለን።ይህ ሲያጋጥመን ልብ ማለት ያለብን የዘመኑን ባህሪ ነው።ያኔ እንደዛሬው የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች እንዲሁም ተፎካካሪ ጋዜጦችና መጽሔቶች አልነበሩም፡፡
እናም ከአፋልጉኝ ማስታወቂያ ጀምሮ የጠጅ ቤት እና የአረቄ ቤት ወሬዎች ሳይቀር በጋዜጣው ላይ ልናገኝ እንችላለን።ምክንያቱም በወቅቱ አስገራሚ ከነበሩ ከዚህ ጋዜጣ ውጭ ሌላ መታያ አማራጭ አልነበራቸውም። ለዛሬው በጥቅምት ወር በጋዜጣው ላይ የወጡትን
እናያለን ።ፋንቱ ያለሰፈሯ ሌሊት ስትዞር ተይዛ ታሰረች ጥቅምት 7 ቀን 1963 ዓ.ምወይዘሮ ፋንቱ ወንደማርያም የተባለች በንፋስ ስልክ አካባቢ የምትኖር ሴት ያለሰፈሯ ከሌሊቱ በ10 ሰዓት በየካቲት 12 አደባባይ ስትዘዋወር በመገኘቷ ተይዛ የሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የአንድ ወር እስራት የቀጣት መሆኑን አስታውቋል።
ስትዘዋወር መገኘቷንና ተላላፊ መኪናዎችንም አድርሱኝ በማለት ማስቸገሯን ፖሊሶች
መመስከራቸውን አስታውቋል።ተከሳሿም ፍርድ ቤት ቀርባ በተጠየቀች ጊዜ በአድራጎቷ ጥፋተኛ መሆኗን ስላመነች ፍርዱ ተሻሽሎላት በ30 ብር መቀጫ ወይም በአንድ ወር እስራት እንድትቀጣ ተደርጎ መቀጫውን መክፈል ስላልቻለች አንድ ወር እንድትታሰር ወደ ወህኒ ወርዳለች ሲል ከአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘ ዜና ያስረዳል።ማስታወቂያጥቅምት 8 ቀን 1934 ዓ.ምበተፈሪ መኮንን ትምህርትቤት ገብተው
ለመማርለሚፈልጉ ልጆች ሁሉተማሪ ቤት ከመግባታቸው በፊት ጤናቸውን መመርመር ፈንጣጣ መከተብና ማናቸውንም የተማሪ ቤቱን ደንብፈጽመው በተማሪ ቤቱመዝገብ እንዲጻፉ የሚያስፈልጋቸውስለሆነ ይህንኑ ለመፈጸምከሚመጣው ማክሰኞ ጥቅምት11
ቀን ጀምሮ እስከጥቅምት 18 ቀንድረስ ጧት ከ3ሰዓት እስከ 7 ሰዓትእንዲሁም ከ9 ሰዓትእስከ 11 ሰዓትከተፈሪ መኮንን ተማሪቤት ድረስ እንዲሰበሰቡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስት የትምህርትና የጥበብሚኒስቴር ያስታውቃል፡፡
የእስረኞች ሱቅ የሰረቀው በእስራት ተቀጣ ጥቅምት 10 ቀን 1972 ዓ.ምየግቢ አውራጃ ወህኒቤት ባልደረባ የነበረውተሾመ አያና የወህኒቤቱ የህግ እስረኞችዕቃ የሚሸጡበት ሱቅውስጥ ሌሊት ገብቶከሁለት ሺ 232 ብርበላይ መስረቁ ስለተረጋገጠበትበሰባት ዓመት ጽኑእስራት እንዲቀጣ የአውራጃውፍርድ
ቤት ባለፈውሳምንት ውስጥ በዋለው ችሎት በይኖበታል።በተያያዘም በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር የጎፋ አውራጃ የርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ
ኮሚሽን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ባልደረባ የሆነው አሰግድ አስፋው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሔ ማካሄጃ እንዲውል በኃላፊነት ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ ሶስት ሺ 147 ብር ከ45 ሳንቲም አጉድሎ ለግል ጥቅሙ አውሏል በመባል ተከሶ አድራጎቱ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ሰሞኑን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የጎፋ አውራጃ ፍርድ ቤት ወስኖበታል።
ሊሰርቅ የሄደው ሌባ ጠጅ አስክሮት ተያዘ ጥቅምት 10 ቀን 1959 ዓ.ምአባዲ ተስፋዬ መስከረም10 ቀን 1959 ዓ.ም ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ላይ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ የአቶ ካህሳይን ቤት ለመስረቅ ሄዶ ከዚያም ሲደርሱ በሩ ስለተዘጋባቸው በዕድሜና በሰውነት ያነሰው አባዲ በአጥር ተንጠልጥሎ ገባ።
አባዲ የቤቱን በር ከፍቶ እንደገባ እያማረጠ ለመስረቅ ጥሩ ጊዜ ሆነለት።በዚህ ሁኔታ የተሰረቀውን ዕቃ እያማረጠ እያጋዘ በማመላለስ እውጭ ካስቀመጠ በኋላ ጠጅ ጠጅ ሸተተው።ወደኋላው መለስ ቢል ጠጅ የሞላው በርሜል አየ።ጎንበስ ቢል የውሃ መቅጃ ቆርቆሮ አገኘ።ከዚህ በኋላ ምን ይጠየቃል ራሱን በራሱ ጋባዥ ሆነ።ከዚያ በኋላ ስካር ተጫጭኖት ስለተሸነፈ አባዲ ከወደቀበት ሥፍራ ሳይነሳ በዚያው ተኝቶ አደረ፡፡በማግስቱ ጠዋት ባለቤቶቹ ከእንቅልፋቸው ተነስተው ቤት ሊጠርጉ ሲሉ አባዲ ተጋድሞ አገኙት።ወዲያው በፖሊስ አስያዙት።ከዚያም ወደ ማረፊያ ቤት ተወስዶ በወታደር ደስታ በቃኸኝ አማካኝነት ቃሉን ሲሰጥ ‹‹ለመስረቅ
ሔጄ ጠጅ አስክሮኝ በዚያው ተኛሁ›› ሲል አረጋግጧል ብለው ሻለቃ ጌራ ወርቅ ገልጠዋል።
በትግሬ ግዛት የኢትዮጵያ የወሬ ምንጭ
ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት
ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም
በዛሬዋ_ዕለት
ከ 93 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ ፤ የታላቁ ንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ የተመረቀበት ዕለት ነበር።
የዳግማዊ አጤ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት የቆመው/የተተከለው ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር፡፡
ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ የአባታቸውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክን ስራና ውለታ ቀጣዩ ትውልድ ያስበውና ይዘክረው ዘንድ … ማስታወሻ የሚሆን የመታሰቢያ ሐውልት ለማሰራት አሰቡ፡፡
ሐውልቱንም በጀርመናዊው መሃንዲስ ሙሴ ሄንትል አማካኝነት አስጠንተው፤ ከጀርመን ተቀርፆ እንዲመጣ አዘዙ፡፡ ሀውልቱ የተመደበለት ቦታ ተደልድሎ ከተዘጋጀ በኋላ ገና ሳይተከል/ሳይቆም ንግሥቲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡
በመሆኑም የንግሥቲቱን እረፍት ተከትሎ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን እየተዘጋጁ የነበሩት አልጋ ወራሽ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን፣ ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት (ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም) ሐውልቱ በታላቅ ክብረ በዓል እንዲተከል አደረጉ፡፡
በሐውልቱ ላይ አፄ ምኒልክ ካባ እንደለበሱ አንባር አጥልቀው በእጃቸው ጣምራ ጦር ይዘው በፈረሳቸው በ‹አባ ዳኘው› ላይ ተቀምጠው በግርማ ሞገስ ይታያሉ፡፡ የሐውልቱ ቁመት ከተፈጥሮ አካላዊ መጠን በላይ ሲሆን ‹አባ ዳኘው› ፊቱን ወደ ሰሜን መልሶ በኋላ እግሮቹ ቆሞ፣ የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ ይታያል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በ 1929 ዓ.ም ወድቆ/ፈርሶ ነበር፡፡
የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት
ብርሃኑ ድንቄ የ 5ቱን የመከራ ዓመታት አጭር ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው ጣሊያኖች የአፄ ምኒልክን ሐውልት እንዴት እንዳፈረሱት እንደሚከተለው ገልፀውታል፡፡ …በቅድሚያ ሐውልቱ ያለበትን አካባቢ ረጅም እንጨት እየማገሩ በቆርቆሮ ሲያጥሩ ሰነበቱ….ይህንን ያየው የአዲስ አበባ ሕዝብ ሊያፈርሱት ነው ብሎ እርስ በእርሱ በሐዘን መነጋገሩን ቢሰሙ ‹‹ልናድስ›› ነው ብለው አስወሩ፡፡ ሁሉንም ነገር ካመቻቹ በኋላ ግን በየበሩ በታንክ ጭምር ጥበቃ አጠናክረው… ወደ ማታ የአራዳን አካባቢ በታንክ አጥረው በባውዛ ሌሊቱን ከተማውን እየተቆጣጠሩ በሌላ ኃይል ደግሞ ሐውልቱን ሲያፈርሱ አድረው ሲነጋጋ ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው ቀበሩት፡፡ ሕዝቡ እድሜና ፆታ ሳያግደው ሐዘኑን ይገልጽ እንደነበር አዛውንቶች ይመሰክራሉ።
በጊዜው የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበረው የሃንጋሪው ዶክተር ላዲ ስላስ ላቫ እንደፃፈው፣ ሐውልቱ ከፈረሰበት ቦታ ቆመው ያለቅሱ የነበሩትን ሰዎች የጣሊያን ወታደሮች በኃይል ይበትኑ እንደነበር ገልጿል፡፡
በሌላ ዘገባ ደግሞ አንድ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ ጣሊያኖች ደርሰው ለምን እንደሚያለቅስ ቢጠይቁት ‹‹የንጉሱን ምልክት ስላወረዳችሁ ነው›› ብሎ እንደመለሰላቸውና ጣሊያኖችም ከሙሶሊኒ ሌላ ንጉሥ እንደሌለው በመንገር ልጁን ገርፈው እንዳባረሩት ተገልጿል፡፡ ጣሊያኖች ሐውልቱን ካፈረሱ በኋላ ሰው ሳያይ ሸፍነው በመውሰድ በታላቁ ቤተ-መንግሥት አዳራሽ ጀርባ ቀበሩት…
የወራሪው ኃይል ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላም ሐውልቱ ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ሚያዝያ 27/ 1934 ዓ.ም ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንዲቆም ተደረገ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ በ 1988 ዓ.ም የአድዋ ድል መቶኛ ዓመት ሲከበር ሐውልቱ ጥገና ተደርጎለት እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ታሪክን_ወደኋላ
????የእንጆሪ የጤና ጥቅሞች | Health Benefits Of Strawberries
????የእንጆሪ የጤና ጥቅሞች | Health Benefits Of Strawberries
????????????
????????የደም ግፊታችንን ያመጣጥናል፡፡
????????የቅድመ-ወሊድ ጤናን ይጨምራል፡፡
????????በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ወይም አቅምን ይጨምራል፡፡
????????የአይናችንን ጤና ያሻሽላል፡፡
????????መጥፎ ኮሌስትሮልን ይዋጋል፡፡
????????ፀረ-ኢንፍላሜሽን ነው ወይም ኢንፍላሜሽንን ይካላከላል።
???????? ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪ አለው ወይም ባክቴሪያን ይከላከላል።
???????? ፀረ-ካንሰር ባህሪ አለው ወይም ካንሰርን ይከላከላል።
???????? ፀረ-ቫይረስ ባህሪ አለው ወይም ቫይረስን ይከላከላል።
???????? ፀረ-እርጅና ባህሪ አለው ወይም እርጅናን ይከላከላል።
የኢትዮጵያ ኤልክትሪካል መሃንዲሶች ማሀበር 25ኛ አመቱን በታላቅ ድምቀት ያከብራል
ከ100 ሺ በላይ ጎብኝዎች የሚታደሙበት ሃይል ቁጠባ አረንጓዴ አፍሪካ የተሰኘ የኤሌክትሪሲቲ ኤግዚብሽን ሊካሄድ ነው።
3A ኤቨንትስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል መሃንዲሶች ማህበር ጋር በመተባበር " ሃይል ቁጠባ አረንጓዴ አፍሪካ " በሚል መሪ ቃል 4ኛውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ኤግዚብሽን ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ድረስ በታላቅ ድምቀት በሚልንየም አዳራሽ ለማካሄድ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤልክትሪካል መሃንዲሶች ማሀበር 25ኛ አመቱን በታላቅ ድምቀት ያከብራል ተብሏል።
በኤግዚቢሽኑ ከ 300 በላይ የሚሆኑ በሃገር ውስጥ ያሉና ከውጭ የሚመጡ በኤሌክትሪሲቲ ዘርፍ
፣ላይ የተሰማሩ አምራቾች አስመጪዎችና አቅራቢዎች ከ100,000 በላይ የሚሆኑ ጎብኚዎች የሚሳተፉ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ሲምፖዚየሞች፣ ሴሚናሮች እና ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርቡበታል ተብሏል።
የ3A ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልፈታህ አሊ እንደገለጹት በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት የሚያሳዩበት፣ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማግኘት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፤ ለቀጣይ ስራ አጋርነት ለመፍጠር እንደሚያስችል እና እንደሚረዳ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኤልክትሪካል መሃንዲሶች ማሀበር 25ኛ አመቱን በታላቅ ድምቀት ያከብራል
ከ100 ሺ በላይ ጎብኝዎች የሚታደሙበት ሃይል ቁጠባ አረንጓዴ አፍሪካ የተሰኘ የኤሌክትሪሲቲ ኤግዚብሽን ሊካሄድ ነው።
3A ኤቨንትስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል መሃንዲሶች ማህበር ጋር በመተባበር " ሃይል ቁጠባ አረንጓዴ አፍሪካ " በሚል መሪ ቃል 4ኛውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ኤግዚብሽን ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ድረስ በታላቅ ድምቀት በሚልንየም አዳራሽ ለማካሄድ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ አስታወቁ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤልክትሪካል መሃንዲሶች ማሀበር 25ኛ አመቱን በታላቅ ድምቀት ያከብራል ተብሏል።
በኤግዚቢሽኑ ከ 300 በላይ የሚሆኑ በሃገር ውስጥ ያሉና ከውጭ የሚመጡ በኤሌክትሪሲቲ ዘርፍ
፣ላይ የተሰማሩ አምራቾች አስመጪዎችና አቅራቢዎች ከ100,000 በላይ የሚሆኑ ጎብኚዎች የሚሳተፉ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ሲምፖዚየሞች፣ ሴሚናሮች እና ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርቡበታል ተብሏል።
የ3A ኢቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልፈታህ አሊ እንደገለጹት በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት የሚያሳዩበት፣ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማግኘት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፤ ለቀጣይ ስራ አጋርነት ለመፍጠር እንደሚያስችል እና እንደሚረዳ ገልጸዋል።