Administrator

Administrator

እናት ፓርቲ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሐይማኖት አባቶችን መግደል ያልተጻፈ ሕግ ኾኗል ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ ከሷል።
ፓርቲው፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ሮቤ ወረዳ፣ የመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የ78 ዓመቱ መምሬ ንጉሤ ወልደ መድኅን በታጣቂዎች በግፍ መገደላቸውን ሰሞኑን ገልጿል።
በተለይ የአርሲ ዞን የደም መሬት ኾኗል ያለው ፓርቲው፣ የሐይማኖት አባቶች ግድያ ወደመለመድ ደረጃ ደርሷል ብሏል።
ዕሁድ'ለትም በቦሌ ክፍለ ከተማ የጎጆ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የድጓ መምህር አፈወርቅ አበባው በጥይት መገደላቸውን ፓርቲው ጠቅሷል።
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትም ይህንኑ ግድያ ማረጋገጡን ዋዜማ በዘገባዋ አመልክታለች፡፡
በኢትዮጵያ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ1.15 ሚሊዮን በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን የዓለም ባንክ አስታወቀ።
ከእነዚህ ውስጥ 915 ሺ የሚሆኑት የጊዜያዊ፣ 237 ሺ የሚሆኑት ደግሞ ቋሚ የስራ መደቦች ናቸው ብሏል።
ባንኩ አዲስ ባወጣው ሪፖርት፤ የኢትዮጵያ የከተማ ነዋሪ ቁጥር እ. ኤ. አ በ2012 ከነበረው 15 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችል ገልፆ፤ ይህም በመሰረተ ልማት፣ በአገልግሎት አቅርቦትና በስራ ዕድል ላይ ተግዳሮት ሊፈጥር እንደሚችል አመልክቷል።
የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፤ የተቋማትን አቅም ለማጠናከርና በመሰረተ ልማት አማካኝነት የስራ ዕድል ለመፍጠር በሀገሪቱ ባሉ 117 ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል ተብሏል።
እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት፣ ፕሮግራሙ የከተማ አስተዳደሮች ተቋማዊ ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በዚህም ምክንያት፣ ጠንካራ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ የአስተዳደር ሂደቶችን በማሻሻልና በጊዜው ኦዲት በማድረግ፣ ከተሞች በራሳቸው እድገት ላይ ቁጥጥር እንዲኖራቸው አስችሏል ማለቱን የዘገበው አዲስ ስታንዳርድ ነው፡፡
 
 
 
 
 
 
 
 
ከመምህራን ዝውውር ጋር ያለውን አሠራር ግልጽነት ለማስፈን የመምህራንን ዝውውርን በኦንላይን ይፋ እንደሚገረግ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከዚህ ቀደም መምህራን ከቦታ ቦታ ዝውውር ሲያደርጉ አሠራሩ ግልጸኝነት የጎደለው ነው።
በአዲሱ የትምህርት ዘመን ግን የኦንላይን ዝውውር አሠራርን በመፍጠር ግልፅ የሆነ ምክንያት በመጥቀስ እና የግምገማ ውጤት በማስቀመጥ ይከናወናል ብለዋል።
በሲስተሙ መሠረት ዝውውሩ ሲደረግም መምህራን በሞባይል ስልካቸው በግልፅ የሚመለከቱት አሠራር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መምህራንም ዝውውሩን በስልካቸው አማካኝነት በኦንላይን እንዲከታተሉ ሀላፊው ጠቁሟል።
በቢሊዮኖች ይታያል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቅ ክስተት ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም እሁድ ምሽት ላይ ይከሰታል፤ በዚህም ጨረቃ ደም መስላ ትታያለች ሲሉ የሥነ ፈለክ ተመራማሪው ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በመላው ኢትዮጵያ ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀው የጨረቃ ግርዶሹ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት፣ በእስያ እና በአውስትራሊያ እንደሚታይም ነው በተለይ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም የተናገሩት።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ዶ/ር ለገሰ ቱሉ አምባሳደር ተደርገው ተሾሙ፡፡
የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ናቸው ዶ/ር ለገሰ ቱሉን በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት የሾሙት፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የ2017 ዓ.ም አምስቱ የጳጉሜ ቀናት ስያሜዎችንና የአከባበር ሁኔታን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ የጳጉሜ ቀናት መታሰብ ዜጎች ለአዲስ ዓመት የግላቸውን መሻት እውን ለማድረግ ሲያቅዱ የመንግስት መነሳሳቶች፣ እቅድና አቅጣጫዎችን በእቅዳቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተገባደደው ዓመት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ማጠናቀቅ፣ የኮሪደር ልማት፣ የኢንደስትሪዎች አምራችንትን ማጠናከር፣ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችም ታላላቅ ሥራዎች የተከናወኑበት መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡
በመጪው አዲስ ዓመትም እነዚህን እመርታዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ዋዜማ የሆኑትን የጳጉሜ አምስት ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን አመላክተዋል፡፡ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት የተሰጣቸው ስያሜና መሪ ቃል እነሆ፡-
ጳጉሜ 1- "የፅናት ቀን"
መሪ ቃሉ -"ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር"
ጳጉሜ 2 - "የኅብር ቀን"
መሪ ቃሉ - “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ”
ጳጉሜ 3 - "የእምርታ ቀን"
መሪ ቃሉ - "እምርታ ለዘላቂ ከፍታ"
ጳጉሜ 4 - "የማንሰራራት ቀን"
መሪ ቃሉ - "ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት"
ጳጉሜ 5 - "የነገው ቀን"
መሪ ቃሉ - "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ"
May be an image of 1 person, newsroom, dais and text that says 'ግሥት nent Comn ኮለ ኮበመጌሽን ጌሽን cation Servi አገልግስ'
 
 
 
 
 
• ዕውቅናው ተማሪዎች በያዙት ድግሪ ብቻ በውጭ ሀገር ስራ እንዲያገኙ ያስችላል
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ተማሪዎች ያላቸውን ድግሪ ተጠቅመው ያለምንም ሌላ መመዘኛ የውጭ ሀገር ስራ እንዲያገኙ ለማድረግ ዕውቅና ማግኘቱን አስታወቀ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደረጃ እንግዳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ዩኒቨርሲቲው በአፕላይድ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ማለትም በባይዮ ቴክኖሎጂ፣ በምግብ ሳይንስና በአመጋገብ ስርዓት፤ በኬሚካል ኢንዱስትሪና በጂኦሎጂ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አግኝቷል።
ዩኒቨርሲቲው ያገኘው ዕውቅና በተለያዩ መርሃግብሮች የተመረቁ ተማሪዎች ያለምንምን መመዘኛ በውጭ ሀገራት ስራ እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል።
ተማሪዎች የተመረቁበትን ድግሪ ይዘው በውጭ ሀገር ስራ መቀጠር አይችሉም ነበር፤ ከዚህ በፊት በሚቀጠሩበት ሀገር መመዘኛ መፈተን ግዴታ ነበር፤ አሁን የተገኘው ዕውቅና በድግሪያቸው ቀጥታ ስራ እንዲቀጠሩ የሚያደርግ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
የተማሪዎቻችን ድግሪ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን ያገኘ ባለመሆኑ የውጭ ሀገር ኢንዱስትሪዎች ወደ ሀገር ውሰጥ ሲገቡ የራሳቸውን የተማረ የሰው ሀይል ይዘው ነው የሚመጡት፤ ዕውቅናው ይህንን ችግር ይፈታል ሲሉ ገልጸዋል።
ዕውቅናው እ.ኤ.አ በ2023 ዓ.ም የተመረቁትንም እንዳሚያጠቃልል ተጠቁሟል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ እንደገለፁት፤ የግድቡ መጠናቀቅን ተከትሎ ህብረተሰቡ አጭር የደስታና የመልካም ምኞት መልእክቱን በ8120 በመጠቀም ማስተላለፍ የሚችልበት ፕሮጀክት ይፋ የተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
«የትውልድ አሻራ - ዲጂታል የብስራት መልዕክትና ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት" የሚል ስያሜ የተሰጠው መሆኑንም ገልፀዋል።
ዓላማውም ህዝቡ ለግድቡ እውን መሆን ሲያደርግ የነበረው ርብርብና ተሳትፎ በተመለከተ ያለውን ስሜት፣ የድል ብስራትና ተስፋ በአጭር መልዕክት እንዲገልጽ የሚያችል መሆኑን ጠቅሰዋል።
መልዕክቱ አሻራውን ለታሪክ መዘክርነት እንዲያስቀመጥ ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል።
መርሐግብሩ ከዛሬ ነሀሴ 27 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 የሚተገበር መሆኑም ተነግሯል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመልካም ምኞት መልዕክቱን በ8120 ላይ በመላክ፤ 1 ቁጥር "በህብረት ችለናል!" መልዕክት ሲጫን 5 ብር ድጋፍ፤ 2 ቁጥር “ህዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ›› መልዕክት ሲጫን 10 ብር ድጋፍ፤ 3 ቁጥር “ግድባችን የአሸናፊነት ድል አክሊል” መልዕክት ሲጫን 15 ብር ድጋፍ፣ 4 ቁጥር ግድባችን እና የአባይ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ሰንደቅ” መልዕክት ሲጫን 100 ብር ድጋፍ እንዲሁም ላኪው የመረጠውን መልዕክት ሲልክ 20 ብር ብቻ ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
በሱዳን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ1ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ለተከታታይ ሰዓታት የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሙሉ መንደር አጥፍቷል ነው የተባለው፡፡
ከተማይቱን የሚያስተዳድረው ሱዳን ሊበሬሽን ፍሮንት የተባለው ታጣቂ ቡድን ባወጣው መግለጫ፤ ማራ የተሰኘው ተራራ አካባቢ የደረሰው አደጋ በቀዳሚው ቀናት በከተማይቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት እንደተከሰተ አመልክቷል።
በአደጋው ከተማይቱ ሙሉ ለሙሉ መውደሟንና 1 ሺህ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን ያመለከተው መግለጫው፤ በሕይወት የተረፈው አንድ ሰው ብቻ እንደሆነም ጠቅሷል።
አዲሱ የሳይቤሪያ 2 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ወደ ሥራ ሊገባ ነው።
ይህን ተከትሎ በሥራ ላይ ካለው የሳይቤሪያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና እየተገነባ ባለው የሩቅ ምስራቅ መስመር የኃይል አቅርቦቶች ይጨምራሉ።
ሁሉም ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ከሩሲያ ወደ ቻይና በኃይል ማስተላለፊያ የሚገባው የጋዝ አቅርቦት መጠን 106 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይደርሳል።
ይህም ሩሲያ እያደገ ላለው የእስያ ኢኮኖሚ ቁልፍ የኃይል አጋርነት ሚናዋን የሚያጠናክርና የወጪ ንግዷን አማራጭ የሚያሰፋው እንደሚሆን ስፑትኒክ ዘግቧል።