
Administrator
Thursday, 17 July 2025 10:01
ኮካ ኮላ ባቀረብኩት ሃሳብ ተስማምቷል - ትራምፕ
የኮካ ኮላ ኩባንያ በአሜሪካ የኮላ ምርት ውስጥ እውነተኛ የሸንኮራ አገዳ ስኳር እንዲጠቀም እንዳሳመኑት ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡
"ይህ በጣም ጥሩ እርምጃ ነው" ሲሉም ኩባንያውን አመስግነዋል፡፡
የዳይት ኮክ አድናቂ የሆኑት ትራምፕ፤ ከኮካ ኮላ ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመው፤ ባቀረቡት ሃሳብ ኩባንያው መስማማቱን ገልጸዋል፡፡
ኮካ ኮላ ለሲቢኤስ ኒውስ በላከው ኢሜል፤ "ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለታዋቂው የኮካ ኮላ ብራንድ ያሳዩትን ጉጉት እናደንቃለን። በኮካ ኮላ ምርት ውስጥ ያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝሮች በቅርቡ ይጋራሉ።" ብሏል፡፡
ኮካ ኮላ ከአሜሪካ ውጭ በተለይም በሜክሲኮ የኮላ መጠጡን የሚያመርተው በሸንኮራ አገዳ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በአሜሪካ ግን መጠጡ ከፍተኛ-ፍሩክቶስ ባለው የበቆሎ ሲሮፕ የሚሰራ እንደሆነ በኮካኮላ ድረገጽ ላይ የሰፈረው መረጃ ይጠቁማል፡፡
"በኮካ ኮላ ኩባንያ ውስጥ ያሉትን ሃላፊዎች በሙሉ ማመስገን እፈልጋለሁ። በጣም ጥሩ እርምጃ ነው የወሰዱት፡፡ ታያላችሁ - የተሻለ ነው!" ሲሉ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ትላንት ረቡዕ የኮካ ኮላ አክሲዮን ሽያጭ፣ በ9 ሳንቲም ወይም 0.13 በመቶ በመቀነስ ወደ 69.27 ዶላር ዝቅ ማለቱ ተዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 17 July 2025 09:52
ከመነኮሳት ጋር ወሲብ ፈጽማ 11.9ሚ. ዶላር ተቀብላለች የተባለችው ግለሰብ ተያዘች
በታይላንድ ከቡድሂስት መነኮሳት ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ገንዘብ ለማግኘት በማስፈራሪያነት ተጠቅማ ከፍተኛ ሃብት አከማችታለች የተባለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፖሊስ "ሚስ ጎልፍ" በሚል ቅጽል ስም የጠራት ይህች ግለሰብ፣ ቢያንሰ ከዘጠኝ መነኮሳት ጋር ወሲብ መፈጸሟን ማክሰኞ ዕለት ፖሊስ በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ግለሰቧ በባለፉት ሦስት ዓመታት መነኮሳቱን አስፈራርታ 11.9 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘች ፖሊስ ያምናል።
ቤቷን የፈተሹ መርማሪዎች መነኮሳቱን ለማስፈራራት የተጠቀመችባቸውን ከ80 ሺህ በላይ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ማግኘታቸውን የፖሊስ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
በታይላንድ በቅድስና እና ክብር ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የቡድሂስት ተቋም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቅሌቶች መነከሩ እየተነገረ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ አደገኛ ዕጽ ዝውውር እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃቶች ናቸው። በቅርቡ የዚህች ግለሰብ ተግባር የእምነቱን ተቋም ያናጋ ሆኗል፤ ብሏል የቢቢሲ ዘገባ፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 17 July 2025 09:46
ሲያከራክር የቆየው የገቢ ግብር አዋጅ ሊጸድቅ ነው
ለተከታታይ ሳምንታት ከፍተኛ ክርክር ሲደረግበት የነበረው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ነገ በፓርላማው ሊጸድቅ መሆኑ ተገለጸ።
የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረ በኋላ፣ አዋጁን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ረቂቅ አዋጁ በተለይም በንግዱ ማህበረሰብና በተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ ሊጣል የታሰበው የግብር ምጣኔ ከፍተኛ ነው የሚል ቅሬታ ሲነሳበት እንደቆየ ካፒታል ዘግቧል፡፡
ከተለያዩ ወገኖች የቀረቡት አስተያየቶች፣ አሁን ካለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት አኳያ፣ እስከ 35 በመቶ የሚደርሰው የገቢ ግብር መጠን መቀነስ እንዳለበት ይጠቁማሉ።
በተጨማሪም፣ የገቢ ግብር መነሻው 2,000 ብር ተብሎ የተቀመጠው ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ይህ መጠን ከፍ ሊል እንደሚገባ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
ሌሎች የቀረቡ አስተያየቶች ደግሞ ለአካል ጉዳተኞች የግብር መጠኑ በተለየ መልኩ እንዲቀነስና ከተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንጻር የአዋጁ ድንጋጌዎች በደንብ ታይተው መስተካከል እንዳለባቸው አፅንኦት መስጠታቸው ይታወቃል።
ፓርላማዉ በነገው ዕለት የሚያፀድቀው ይህ ረቂቅ አዋጅ ላይ መንግስት ሲሰጥ የነበረዉ ማብራሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ የታክስ ፍትሀዊነትንና የኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም እድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅቷል ብሏል።
ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን በነገው አስቸኳይ ስብሰባው ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ካፒታል ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…

Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 17 July 2025 09:44
መምህርና ወላጅ የፈተና ወረቀት በመስረቅ ሙከራ ታሰሩ
በደቡብ ኮሪያ የፈተና ወረቀቶችን ለመስረቅ በምሽት ትምህርት ቤት ሰብረው የገቡት አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርና አንድ የተማሪ አባት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል፡፡
መምህርና ወላጅ የስርቆት ሙከራውን ያደረጉት ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም 6:20 ላይ ሲሆን፤ በሴኡል ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በምትገኘዋ በአንዶንግ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት መሆኑ ተዘግቧል፡፡
ሆኖም የትምህርት ቤቱ የአደጋ ጊዜ ደወል መጮሁን ተከትሎ፣ ሁለቱም በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉ ሲሆን፤ አስተማሪው ጉቦ በመቀበልና ስልጣንን በመተላለፍ ወንጀል ተከሷል።
ከአስተማሪው በተጨማሪ የት/ቤቱ የፋሲሊቲ ስራ አስኪያጅና ከሁለቱ ጋር አሲረዋል የተባለው ግለሰብም፣ በስርቆትና ሌላን ሰው በህገወጥ መንገድ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገባ በመፍቀዱ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የደቡብ ኮርያ ባለስልጣናት እንደተናገሩት፤ መምህሩ የታሰሩትን አባት ልጅ በግል አስተምሯል ብለዋል።
በደቡብ ኮሪያ ትምህርት ህግ መሰረት፣ በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በቋሚነት ተቀጥረው የሚሠሩ መምህራን በግል ልጆችን ማስጠናት ወይንም ቤት ሄዶ ማስተማር አይፈቀድላቸውምና አስተማሪው ሌላ የህግ ጥሰት መፈፀሙ ተጠቁሟል፡፡
ታድያ አሁን አባቱ በቁጥጥር ስር የዋለው ተማሪ፤ "በተከታታይ ከፍተኛ ውጤት ሲያስመዘግብ መቆየቱ" የተገለፀ ሲሆን፤ ነገር ግን ውጤቱ ከፈተና-ወረቀት ስርቆት ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ግልፅ አይደለም ተብሏል።
(ዳጉ- ጆርናል)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 17 July 2025 09:36
በአሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ አንድ አውሮፕላን መጠነኛ የመንሸራተት እክል እንዳጋጠመው ተገለፀ
• በመንገደኞች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የበረራ ቁጥሩ ET-298 የሆነ አውሮፕላን፣ በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ካረፈ በኋላ፣ ከመንደርደሪያው መጠነኛ የመንሸራተት እክል አጋጥሞታል ሲል ገልጿል።
አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜ ዝናብ እየዘነበ እደንነበር አየር መንገዱ ባወጣው አጭር መግለጫ ገልጿል።
በሁለት የበረራ ሰራተኞች ላይ መጠነኛ ጉዳት ማጋጠሙን የጠቆመው አየር መንገዱ፤ በመንገደኞች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱንና ከአውሮፕላኑ በሰላም እንዲወርዱ መደረጉን አመልክቷል፡፡
የበረራ ሰራተኞቹ ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም ተወስደው ከታከሙ በኋላ ወደ ሆቴል እንዲሄዱ ተደርገዋል ተብሏል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ ጠይቆ ተጨማሪ መረጃ ሲኖር የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።
ባሳለፍነው አመት ጥር ወር የአየር መንገዱ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መጠነኛ አደጋ እንዳጋጠመው አዲስ ስታንዳርድ በዘገባው አስታውሷል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 17 July 2025 09:37
ሩሲያ ከጃፓን ኢኮኖሚ ጋር የነበራትን ልዩነት በእጥፍ አሳደገች
• ከዓለም ታላላቅ ኢኮኖሚዎች በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች
የሩሲያ ኢኮኖሚ በግዢ አቅም ስሌት በ2023 ከነበረበት 6.45 ትሪሊየን ዶላር፤ ባለፈው ዓመት ወደ 6.92 ትሪሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በዚህም ሀገሪቱ ከዓለም ታላላቅ ኢኮኖሚዎች መካከል በአራተኛ ደረጃ ላይ መቆየት እንደቻለች ዓለም ባንክ ያወጣው መረጃና የስፑትኒክ ስሌት አረጋግጧል፡፡
እ.ኤ.አ 2023 የነበረውን 6.25 ትሪሊዮን ዶላር አጠቃላይ ምርት በ2024 ወደ 6.4 ትሪሊየን ዶላር ከፍ ያደረገችው ጃፓን፤ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ በሩሲያና በጃፓን አጠቃላይ ምርት መካከል የነበረው ልዩነት ባለፈው ዓመት በእጥፍ ጨምሮ በ2023 ከነበረበት 264 ቢሊየን ዶላር ወደ 514 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል።
ቻይና በ38.2 ትሪሊየን ዶላር መሪነቷን ይዛ የቀጠለች ሲሆን፤ አሜሪካ በ29.2 ትሪሊየን ዶላር፤ ህንድ ደግሞ በ16.2 ትሪሊየን ዶላር ይከተላሉ።
ጀርመን በ6 ትሪሊየን ዶላር፣ ብራዚል በ4.7 ትሪሊየን ዶላር፣ ኢንዶኔዥያ በ4.7 ትሪሊየን ዶላር፣ ፈረንሳይ በ4.2 ትሪሊየን ዶላር እና እንግሊዝ በ4.2 ትሪሊየን ዶላር ከአስሩ ታላላቅ ኢኮኖሚዎች ውስጥ መካተታቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:05
ከ200 ሺ ብር እስከ 100 ሺ ብር የሚያሸልም የወጣቶች ውድድር!!
የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር (Youth in Agroecology Startup Competition) ምንድነው?
ኢትዮጵያን ሰስተኔብል ፉድ ሲስተምስ ኤንድ አግሮኢኮሎጂ ኮንሶርቲየም (ESFSAC) ከአፍሪካን ፉድ ሶቨርኒቲ አሊያንስ (AFSA) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ ወጣቶች ያዘጋጀው ውድድር ነው። ዓላማውም ለምግብ ሉዓላዊነት፣ ለዘላቂነት (sustainability) እና ለማህበረሰብ ደህንነት ሀገር-በቀል መፍትሔዎችን ማበርከትና ወጣቶች አግሮኢኮሎጂን እና አገር በቀል ምግቦችን በማስተዋወቅ ረገድ የመሪነትን ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል ነው።
ሁለት የመወዳደሪያ ጭብጦች ተቀምጠዋል፦ የመጀመሪያው አግሮኢኮሎጂካል እርሻ እና ፈጠራ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጤናማ እና የሀገር በቀል ምግቦች ላይ በመስራት እና በማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው። ከሁለቱ በአንዱ ላይ የተሰማሩ (startup) የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣቶች መወዳደር ይችላሉ።
ይህ ውድድር የ“My Food is African / My Food is Ethiopian” ዘመቻ አካል ነው።
ማመልከት የሚችለው ማነው?
በአዲስ አበባ የሚገኙ እድሜያቸው ከ18-35 ዓመት የሆኑ፣ አግሮኢኮሎጂን ወይም ጤናማ እና የሀገር በቀል ምግብ ሥርዓቶችን የማሳደግ ተነሳሽነትን የሚደግፉ ሥራዎችን እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች ማመልከት ይችላሉ።
ከአሁን በፊት በተመሳሳይ ውድድር ተሳትፈው ያላሸነፉ ወጣቶች በዚህ ውድድር ማመልከትና መወዳደር ይችላሉ። ነገር ግን በሌላ ውድድር ላይ አሸናፊ የነበሩ ወጣቶች በዚህ ውድድር መሳተፍ አይችሉም።
ከሴቶች እና በቂ ውክልና ከሌላቸው ማህበረሰብ አባላት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችን አጥብቀን እናበረታታለን።
ከማመልከቻዎ ጋር ስራዎን ወይም የምርት ናሙናዎን የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ አያይዞ ማቅረብ ይኖርብዎታል።
የምዝገባ ቀን መቼ ነው?
ከሐምሌ 14-25/2017 (ጁላይ 21 - ኦገስት 1, 2025)።
ይመዝገቡ፣ ይወዳደሩ፣ይሸለሙ።
ሽልማቱ ምንድነው?
በዳኞች ለተመረጡት አስር ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ ጠቃሚ የሆኑ ሥልጠናዎችን ያገኛሉ፤ የአያንዳንዳቸውን ሥራዎች (በቪዲዮ፣ በፎቶ እና በጽሁፍ) ለሌሎች የሥራ አጋሮቻችን በማጋራት ሥራዎቻቸውን እና እራሳቸውን አንዲያስተዋውቁ ይደረጋል። በተጨማሪም አብረው መስራት ከሚፈልጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር እናገናኛቸዋለን።
አንደኛ ለምትወጣው/ለሚወጣው 200,000 ብር
ሁለተኛ ለምትወጣው/ለሚወጣው 150,000 ብር
ሦስተኛ ለምትወጣው/ለሚወጣው 100,000 ብር
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይከተሉ:-
እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የESFSAC ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ፦
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:03
በማሳቹሴትስ በአፓርትመንት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በማሳቹሴትስ ግዛት በፎል ሪቨር ከተማ ባለ 3 ፎቅ የመኖሪያ አፓርትመንት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለሲኤንኤን ተናግረዋል።
በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ በ30 በሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።
እሳቱ በመኖሪያ አፓርትመንቱ መግቢያ መውጢያ ላይ በመበርታቱ ምክንያት አብዛኞቹ ተጎጂዎች ከእሳቱ ለማምለጥ በመስኮት ለመዝለል መሞከራቸው አደጋውን አባብሶታል ተብሏል።
የከተማዋ አስተዳደር በደረሰው አደጋ ማዘኑን ገልጾ፤ አባሎቻቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:01
"ከዩክሬን ጋር ስምምነት ካልተደረሰ አሜሪካ
በሩሲያ ላይ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ ትጥላለች"
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኔቶ ሃላፊ ማርክ ሩተ ጋር በዛሬው ዕለት በዋይት ሃውስ ተገናኝተው በተለያዩ ዓለማቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ዓለማቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ ስፑትኒክ ከውይይቱ የተጨመቁ ቁልፍ ነጥቦችን እንደሚከተለው አጠናክሯቸዋል፡፡






የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 14 July 2025 20:00
ሩሲያ በማዕከላዊ አፍሪካ የአልማዝ ማዕድን ለማውጣት ተፈቀደላት
ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የሩሲያ ኩባንያዎች የአልማዝ ማዕድን እንዲያወጡ ፈቃድ መስጠቷን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ዓመት የአልማዝ የወጪ ንግድ እገዳ ሙሉ በሙሉ መነሳቱ ለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው፤ የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቴሪ ፓትሪክ አኮሎዛ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
"ምክንያቱም ያለ ማዕቀብ ሀገሪቱ የማልማትና የማዕድን ምርቶቿን በመሸጥ ጥሩ ገቢ የማግኘት እድል አላት” በማለት አዲሱ ነጻነት የሚሰጠውን ኢኮኖሚያዊ አቅም አጉልተው ማሳየታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
እ.ኤ.አ ሕዳር 21 ቀን 2024 ዓ.ም ለአልማዝ ንግድ ዓለም አቀፍ እውቅና የሚሰጠውና ተቆጣጣሪ አካል የሆነው ‘የኪምበርሊ ሂደት’ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ አልማዝ ወደ ውጭ እንዳትልክ ጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል፡፡ እቀባው በግጭት ስጋት ምክንያት መጀመሪያ የተጣለባት በፈረንጆቹ 2013 ነበር፡፡
በ2016 እግዱ በከፊል መነሳቱን ተከትሎ ከግጭት ነጻ ከተባሉ አምስት ቀጠናዎች አልማዝ ወደ ውጭ እንድትልክ አስችሏታል፡፡ የማዕቀቡ ሙሉ በሙሉ መነሳት ደግሞ ለሰፊ የማዕድን ሥራዎችና ለዓለም አቀፍ አጋርነት መንገድ ከፍቷል ተብሏል።
የሩሲያ የማዕድን ኩባንያዎች በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ ማዕድን በማውጣት ሥራ እንዲሰማሩ ፈቃድ ማግኘታቸው ሰሞኑን ተዘግቧል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under