Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ከ2 ሳምንት በኋላ 13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በደቡብ ኮርያዋ ዳጉ ውስጥ ሲካሄድ ኢትዮጵያን የሚሳተፉ አትሌቶች የነበረ ታሪካቸውን ለማስጠበቅ ከኬንያውያን ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ለመረዳት ተቻለ፡፡ በሻምፒዮናው የኢትዮጵያ ቡድን 53 አባላት ያሉበትን ልዑካን በመያዝ እንደሚሳተፍ ሲታወቅ ከ400 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ይካፈላል፡፡

አለም በህገወጥ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት ምን ያህል ሴቶችን አጥታለች ለሚለው ለጊዜው በእርግጠኝነት ይህን ያህል ማለት ባይቻልም ብዙዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ግን እውን ነው፡፡ እንደ World Health Organization, the Alan Guttmacher Institute, and Family Health International, እማኝነት ከሆነ በአለም Ÿ70,000 - 200,000 የሚሆኑ ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ምክንያት ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

ለ6ኛ ጊዜ የተካሄደው የ..ቢግ ብራዘርስ አፍሪካ.. አብሮ የመኖር ውድድር ባለፈው ሳምንት ሲጠናቀቅ የናይጀሪያዋ ኬረንና የዚምባቡዌዋ ዌንደል አሸናፊ ሆነው እያንዳንዳቸው 200ሺ ዶላር ተሸለሙ፡፡ ለ91 ቀናት በዘለቀው አብሮ የመኖር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ሃና መኩሪያ እስከ መጨረሻው ሳምንት በመዝለቅ ከሰባቱ ዕጩዎች ተርታ ከመግባቷም በላይ በ90 ቀን ቆይታ ለኢትዮጵያ ተሳታፊዎች አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባለች፡፡

የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር ነገ ጧት በብሔራዊ ትያትር ስቱዲዮ አዳራሽ የአመራር አባላት እንደሚመርጥ አሳወቀ፡፡ በደራሲ የምወድሽ በቀለ ፕሬዚዳንትነት የሚመራው የአሁኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር ለሁለተኛ ጊዜ መወዳደር እንደሚችልና የተጓደሉ አመራሮችን ለመምረጥም መታቀዱን ከማህበሩ የተገኘው መግለጫ ያስረዳል፡፡ ከምርጫው ሌላ መደበኛ የኪነጥበብ ዝግጅት እንደሚኖርም ማወቅ ተችሏል፡፡

በደራሲና ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሹምዬ ተፎ የተዘጋጀው ..የተሳሳተ ጥሪ.. ፊልም ከነሀሴ 7 ጀምሮ ለሕዝብ መቅረብ የሚጀምር ሲሆን ፊልሙ ነሀሴ 9 ቀን በብሔራዊ ትያትር ቤት እንደሚመረቅ ገበያኑ ኢንተርቴይመንት አስታወቀ፡፡ የ105 ደቂቃ ርዝመት ያለው ፊልም፤ ሰኞ ነሀሴ 9 ከቀኑ 11 ሲመረቅ የመግቢያ ትኬት ዋጋ 50 ብር መሆኑ ሲታወቅ በ833 የስልክ ሑፍ መልእክት ተመልካቾችን ለመሸለም የብሔራዊ ሎተሪ ፈቃድ ማግኘታቸውን ጠቁሟል፡፡

በቀድሞው ..የአዲስ ነገር.. ጋዜጠኛ መሐመድ ሰልማን የቀረቡ ልዩ ልዩ ወጎችና የጉዞ ማስታወሻዎችን የያዘ መጽሐፍ በቀጣዩ ሳምንት ለንባብ ይበቃል፡፡ ..ፒያሳ፣ ማሕሙድ ጋ ጠብቂኝ.. የሚል ርዕስ የተሰጠው ይህ መጽሕፍ በአመዛኙ በቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ቀርበው በስፋት የተነበቡ ወጎችና የጉዞ ማስታወሻዎችን ከአዳዲስ ስራዎች ጋር የያዘ ስብስብ ስራ ሲሆን 200 ገጾች አሉት፡፡

በጋዜጠኛ ተስፋዬ ሽመልስ የተዘጋጀው ..ሰማያዊ ዐይን.. የተሰኘው ትያትር መታየት የጀመረበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ነገ ከሰዓት በኋላ ክብረ በዓል እንደሚኖር አዘጋጁ ለአዲስ አድማስ ገልል፡፡ በቅርቡ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባዘጋጀው ውድድር ትያትሩ የተሸለመ ሲሆን ክብረ በዓሉ ይህንኑ በማስመልከት ጭምር እንደተዘጋጀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይኸው ትያትር ካሁን ቀደም በሲቪል ሰርቪስ  ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት እንዲሁም ለሌሎች ተመልካቾች በክፍለ ሀገር የታየ ሲሆን ከነገ ወዲያ ሰኞ ምሽት፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ በክፍያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይታያል፡፡

..መሰረታዊ ሳይንስ.. ለገበያ ቀረበ
ደራሲ እና የወግ ፀሐፊ መስፍን ኃብተማርያም ..ብልጧ ዝንጀሮ.. የሚል አዲስ የሕፃናት መሐፍ ለንባብ አብቅቷል፡፡ በጀርባ በኩል The Rich Man and The Singer የሚል ሌሎች የሕፃናት ታሪኮችን የያዘው መሐፍ ዋጋ 22 ብር ነው፡፡ በአማርኛው 27 በእንግሊዝኛውም የእነዚሁኑ ትርጉም የያዘው መሐፍ በአጠቃላይ 138 ገፆች አሉት፡፡
መስፍን ሃብተማርያም ካሁን ቀደም ..አውድ ዓመት.. እና ..የቡና ቤት ስእሎች.. በሚሉት የወግ መፃሕፍቱና በሌሎቹም ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡  
በሌላ በኩል ሃና ማንያዘዋልና ኢሳያስ ገብረክርስቶስ ያዘጋጁት ..መሠረታዊ ሳይንስ.. ከ1-4ኛ ክፍል አጋዥ መሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መሐፉ በ27 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

በሙሉ ስሙ ከርቲስ ጃክሰን ተብሎ የሚጠራው ጥቁር አሜሪካዊው ራፐርና የፊልም ተዋናይ 50 ሴንት፤ ..ሃብታም መሆኔ ነፃነት ሰጥቶኛል.. ሲል ለፋይናሻል ታይምስ መጽሔት ተናገረ፡፡ ..ቺታሪ ቪዥን.. የተባለ የፊልም ኩባንያ በ200 ሚሊዮን ዶላር ያቋቋመው ፊፍቲ ሴንት፤ ሙዚቃውን ወደ ጐን በመተው በፊልም ስራ መጠመዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሻጊ የሬጌ ሙዚቃ የዓለም የሙዚቃ  ገበያን ሰብሮ ለመግባት አልቻለም ሲል ተናገረ፡፡ ..ሰመር ኪንግስተን.. የተባለ አዲስ የሙዚቃ አልበሙን ከወር በፊት ለገበያ ያበቃው ሻጊ፤ ለሬጌ የሙዚቃ አልበሞች ገቢ ማነስ የስፖንሰሮች እጥረት ዋንኛው ምክንያት መሆኑን ለኤምቲቪ ኒውስ ተናግሯል፡፡