ጨጓራ እና ‘ሙሉ በግ…’
እኔ የምለው…አንዳንዴ ግርም ይለኛል… ብዙ ነገሮችን ስታዩ ምንድነው መተሳሰባችንን እንዲህ ሙልጭ አድርጎ የወሰደብን አያስብላችሁም? እንዴ…ሥራ ፈላጊ ቢኖርም እኮ ጭማሪ ማግኘት ያለበት ጭማሪውን ለምን አያገኝም፡፡ ገና ለገና ‘ትርፍ ከፍ ለማድረግ’ እየተባለ የሠራ ሰው ለሥራው የሚመጥን ክፍያ ሳይሰጠው ሲቀር በጣም ቀሺም ነው፡፡
እንዴት ሰነበታችሁሳ!
የሆነ መሥሪያ ቤት ነው፡፡ እናላችሁ… “ስትረክቸር የሚሉት ነገር ተሠርቶ እየተበተነ ስለነበር ህዝቤ ሁሉ ቋምጦ እየጠበቀ ነው፡፡ “መቼም ዘንድሮ ኑሮ እንዲህ በተወደደበት በሽ ነው የሚያደርጉን…” እየተባለ…እንዲሁ ከመሬት ተነስቶ ሳቅ ሳቅ የሚላቸውም አይጠፉም፡፡
እንደውም አንዳንዶቹ “ይሄ ፍራንክ ሲመጣ ሎጅ የሚባለውን መዝናኛ ዘንድሮ ሄጄ ዓለም ዘጠኝ ካላልኩበትማ…” እያሉ ዕቅድ ሳያወጡ አይቀርም፡፡
በወንጀል ጉዳይ በስህተት የተሰጠ የመጨረሻ ፍርድ
አቶ አሰፋ ከሲቶ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር፣ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል የሥነምግባርና የጸረሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር እንዲሁም የፍትህ ቢሮ ሃላፊ እና የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ናቸው፡፡ በስህተት የተላለፈ የወንጀል ቅጣት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ የሰጡትን ቃለምልልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
የወንጀል ፍርድ በስህተት የሚሰጥበት አጋጣሚ አለ?
በቅድሚያ የወንጀል ፍትህ ሥርዓት ገጽታዎችን ማየት ጠቃሚ ነው፡፡ የወንጀል ሕግ ዓላማ የመንግሥትን፣ የሕዝቡንና የነዋሪውን ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት፣ መብት እና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡ የወንጀል ሕግ ግብ ደግሞ ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ሲሆን ወንጀል ተፈጽሞ ሲገኝ ወንጀል አድራጊዎችን ለሕግ በማቅረብና በማስቀጣት ሌላ ወንጀል ከመፈጸም እንዲቆጠቡ፣ ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑና እንዲታረሙ ማድረግ ነው፡፡
3ቱ የኑሮ ችግሮች
የኢህአዴግና የተቃዋሚዎች 3 የምርጫ አጀንዳዎች
የተመራቂዎች ሥራ አጥነት
በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተመራቂዎች ሥራ አጥ ሆነዋል፤ በየአመቱ ግማሽ ሚሊዮን ያህል ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ይመረቃሉ።
የኑሮ ውድነት ሸክም የዋጋ ንረት በአስር አመት በአምስት እጥፍ ጨምሯል። የደሞዝተኛ ሰራተኞች የኑሮ ደረጃ ደግሞ በግማሽ አሽቆልቁሏል።
የአነስተኛና ጥቃቅን ችግር
በሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች በገበያ እጦትና በመንግስት የተንዛዛ ቢሮክራሲ ሳቢያ ከስረዋል፤ የተበደሩትን ሳይመልሱ ጠፍተዋል
በመጪው ግንቦት የሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ምን አይነት መልክ ሊኖረው እንደሚችል ከወዲሁ መገመት ይከብዳል። በዚያው ጊዜ በመላ አገሪቱ በሚከናወኑት የወረዳና የቀበሌ ምርጫዎች፤ ከሞላ ጎደል ኢህአዴግና አጋሮቹ በዘጠና ምናምን ፐርሰንት እንደሚያሸንፉ አያጠራጥርም። የአዲስ አበባውም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ግን ላይሆንም ይችላል።
“አንድነት” በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ነገ ውይይት ያካሂዳል
የገዥው ፓርቲ አፈናና ጭቆና መባባሱና የተቃዋሚ ፓርቲዎች
..በውይይቱ ላይ የሚነሱ ነጥቦች ናቸው
የፓርቲው ልሳን “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ በአገሪቱ በየትኛውም ማተሚያ ቤት እንዳትታም መታገዷን ፓርቲው አስታወቀ
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ነገ በጽ/ቤቱ ውይይት ሊያካሂድ ነው፡፡ ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ ሃሳቦች በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡ ፓርቲው የአገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ ለሚያደርገው ውይይት ይረዳል ተብሎ በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የሚቀርበውና ሶስት ዋና ዋና የፖለቲካ ነጥቦችን ስላካተተው የውይይት መነሻ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲናገሩ፤ “በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል፤ ይህንን ሁኔታም ለህዝቡ ለማሳወቅና በመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ለመነጋገር ውይይቱ ተጠርቷል፡፡” ብለዋል፡፡
የቅ/ላሊበላ ደብር ሒሳብ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር ተጠየቀ
የሁለቱን ሆቴሎች ባለቤትነት ወደ ገዳሙ ይዞታ የማዛወር ሂደት ተጀምሯል
በወጣው ዜና ‹‹ስሜ ጠፍቷል›› ያሉት የደብሩ አስተዳዳሪ ነዳያኑን ምግብ ከልክለዋል
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የቅዱስ ላሊበላ ደብረ ሮሃ ገዳም ሒሳብ በገለልተኛ የውጭ ኦዲተር እንዲመረመርና ‹‹ሀብቱን በሙስና እና ብኵንነት አጥፍተዋል፤ በካህናቱ፣ በሊቃውንቱና በሠራተኞቹ ላይ የአስተዳደር በደል አድርሰዋል፤ ምእመናንን እየዘለፉ ሕዝብንና መንግሥትን አጋጭተዋል›› የሚሉ አቤቱታዎች እየቀረቡባቸው የሚገኙት የገዳሙ አስተዳዳሪ መመህር አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን በሕግ እንዲጠየቁ የቅዱስ ላሊበላ ደብረ ሮሃ ገዳም አስጎብኚዎች ማኅበር፣ የገዳሙ ካህናት እና ምእመናን ጠየቁ፡፡
እወርካ ሥር የገደለ፣ ዘወትር እወርካ ሥራ ያደፍጣል!
አንድ የላቲን አሜሪካ ተረት እንዲህ ይላል፡-
የአንድ ሀገር ህልውና ሊደፈር ነው ተባለና መሪው ዋና ዋና ሰዎችንና ህዝቡን ሰብስቦ፤ “ጀግናው የሀገሬ ህዝብ ሆይ! አገራችን አደጋ ላይ ናት፡፡ የጎረቤት አገሮች ወራሪዎች ሊደፍሩን አሰፍስፈዋል፡፡ ምርጫችን ከሁለት አንድ ነው “እንዋጋ?” ወይስ አንዋጋ?” አንዱ እጁን አወጣና፤
“ምንም ምክክር አያስፈልግም፡፡ እንዋጋ!!” አለ፡፡
በ36ኛው የሴካፋ ሻምፒዮና ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል
በኡጋንዳ አዘጋጅነት ከሳምንት በኋላ እንደሚጀመር በሚጠበቀው የ2012 ሴካፋ ታስከር ቻሌንጅን ካፕ ለሻምፒዮናነት ከባድ ፉክክር እንደሚኖር ተጠበቀ፡፡ በታሪክ ለ36ኛ ጊዜ ለሚደረገው ሻምፒዮናው የምድብ ድልድል ባለፈው ሰኞ ሲወጣ የሞት ምድብ በተባለው ምድብ 1 የ12 ጊዜ ሻምፒዮኗ ኡጋንዳ፤ ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈችው ኢትዮጵያ ፤ ኬንያ እና አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን ተገናኝተዋል፡፡ በምድብ 2 ሱዳን፤ ታንዛኒያ፤ ብሩንዲ እና ሶማሊያ ሲደለደሉ በምድብ 3 ደግሞ ሩዋንዳ፤ ዛንዚባር፤ ኤርትራ እና ብቸኛዋ ተጋባዥ አገር ማላዊ ተመድበዋል፡፡ ከሶስቱ ምድቦች አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው የጨረሱት 6 አገሮች እና ከየምድቦቹ ጥሩ ሶስተኛ ደረጃ ያገኙት ሁለት አገራት ወደሩብ ፍፃሜ የሚያልፉ ይሆናል፡፡
ለዋልያዎቹ ዝግጅት ብሄራዊ ርብርብ ያስፈልጋል
ሳላዲን እየተወራለት ነው
በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሚሳተፉ መካከል 14 ብሄራዊ ቡድኖች በአፍሪካ፤ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ሰሞኑን ባደረጓቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በይፋ ዝግጅታቸውን ጀመሩ፡፡ ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የበቃችው ኢትዮጵያ እና ማላዊ ፊፋ ለወዳጅነት ጨዋታዎች ባወጣው ፕሮግራም የሉበትም፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ጋና ከኬፕቨርዴ በሊዝበን ፤ ረቡእ እለት ደግሞ በአሜሪካዋ ሚያሚ ናይጄርያ ከቬንዝዋላ ጋር እንዲሁም በጆሃንስበርግ አዘጋጇ ደቡብ አፍሪካ ከሻምፒዮኗ ዛምቢያ፤ አይቬሪኮስት ወደ አውሮፓ ተጉዛ ከኦስትሪያ ጋር ተጫውተዋል፡፡
ሜሲ 4ኛውን የወርቅ ኳስ ይወስዳል!?
ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ኮከብ ተጨዋችነት ለአራተኛ ጊዜ የወርቅ ኳሱን ሊሸለም እንደሚችል ከፍተኛ ግምት አገኘ፡፡እነፔሌ፤ ዲያጎ ማራዶና፤ ዮሃን ክሩፍ፤ ቤከንባወር ፤ ፕላቲኒ እና አልፍሬዶ ዴስትፋኖ በተጨዋችነት ዘመናቸው በኮከብ ተጨዋነት ያገኙአቸውን ክብሮች በመሰብሰብ እና የግብ ሪከርዶች በማሻሻል እና በመጋራት ታሪክ መስራቱን የቀጠለው የ25 ዓመቱ ሊዮኔል ሜሲ የምንግዜም ምርጥ ተጨዋች እየተባለም ነው፡፡ሊዮኔል ሜሲ በፊፋ እና ፍራንስ ፉትቦል መፅሄት የሚዘጋጀውን የወርቅ ኳስ ዘንድሮም ማሸነፍ ከተሳካለት በሽልማቱ ታሪክ 4 የወርቅ ኳሶችን በመውሰድ የመጀመርያው ተጨዋች ይሆናል፡፡ በ2013 የፊፋ የዓለም የእግር ኳስ ኮከቦች ምርጫ ላይ ለመፎካከር የቀረቡት 23 እጩዎች ከ2 ሳምንት በፊት ታውቀዋል፡፡
ተንቀሳቃሽ የኢትዮጵያ ቅርሶች ነን
እስቲ ከልጅነትህ እንጀምር…
የተወለድኩት እዚሁ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አካባቢ ነው፡፡ በፀሐይ ጮራ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትና በምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው የተማርኩት፡፡ የባህል ውዝዋዜና ዳንስ የጀመርኩት ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ሲሆን በቀበሌ ኪነት ውስጥም ነበርኩኝ፡፡ ዛሬ እንግዲህ 27 ዓመቴ ነው፡፡ ሽሮ ሜዳ (ቀበሌ 08) የባህል ቡድን ነበረ፡፡ እኔ ደግሞ በጣም ሙዚቃ እወድ ነበር፡፡ አንድ የሠፈር ጓደኛዬ ካልሄድን ብሎ ገፋፋኝና ሄድን፡፡ የእኔ ፍላጐት እንኳን ዳንስ ነበር፡፡ ልጆቹ ግን የወሎ፣ የጐንደር፣ የጐጃምና የሐረር ኦሮሞ የባህል ውዝዋዜ ነው የሚሰሩት፡፡ እኔ ደግሞ እነዚያን ውዝዋዜዎች አላውቃቸውም፡፡ እኔ መደነስ መጨፈር ነበር የምወደው፡፡ ሆኖም የባህል እንቅስቃሴውም አላስቸገረኝም፤ እንደውም ቶሎ ተዋሃደኝ፡፡ አርቲስት ሰለሞን መንግሥቴ የተባለ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት የሚሰራ ልጅ አውቅ ነበር፡፡ በሱ አማካኝነት ቲያትር ቤት የመሄድ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት እንድገባ የረዳኝ በኢቲቪ ይተላለፍ ለነበረ የህፃናት ፕሮግራም መታጨቴ ነው፡፡ “ትንሹ ሙዚቀኛ” በሚል ርዕስ ድራማ ሰርተናል፡፡