የጋዳፊ መጨረሻ አላማረም
ጋዳፊ አሁንም እየዛቱ ነው - አይጦችንና ከሃዲዎችን እንግደላቸው በማለት
አማፂዎቹ በቦርሳ ውስጥ የምትገባና 2 ኪሎ የማትመዝን ሄሊኮፕተር ተጠቅመዋል
ጋዳፊ ከቤተመንግስት ስር 4 ሚ. ሰዎችን አመት ሙሉ የሚቀልብ ምግብ አከማችተዋል
ተማርከዋል የተባሉት የጋዳፊ ልጆች እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም
ሲአይኤ እና የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት በየፊናቸው ሊቢያ ውስጥ ተወጥረዋልየጋዳፊ ቤተመንግስትና መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የወርቅ ሽጉጥና ወርቅ ቅብ ጋሪ በመሳሰሉአስገራሚ ነገሮች የተሞሉ ቢሆኑም፤ ከህንፃዎቹ በታች ምድር ስር የተገኙት ዘመናዊ ቤቶችና መጋዘኖች ግን ብዛታቸውና ውስብስብነታቸው ከተጠበቀው በላይ አስደናቂ ሆኗል፡፡
ቀነኒሳ ክብሩን ሊያስጠብቅ ነው
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺ ሜትር በዓለም ሻምፒዮና በመሳተፍ የያዘውን ክብር ለማስጠበቅ እንደወሰነ ታወቀ፡፡
ከሳምንት b|§ በኮርያዋ ከተማ ዳጉ በሚጀመረው በ13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአጭር ርቀት እስከ ማራቶን በሚካሄዱ ውድድሮች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የነበረውን የበላይነት ለማስጠበቅ ከኬንያ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ አትሌቶች ከባድ ትንቅንቅ ውስጥ ይገባል፡፡
የቶም ቆይታ በረጅም እቅድ ሊታይ ይገባል
የኢትዮጵያና ሶማሊያ ጨዋታ ጦርነት፤ ሰላምና ዓለም ዋንጫን ያገናኘ ተባለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓመቱ በዓመቱ መጨረሻና በዓዲሱ ዓመት መግቢያ ላይ 2 ቀሪ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያዎችን የሚያደርግ ሲሆን ለ20ኛው የዓለም ዋንጫ በቅድመ ማጣርያ ከሶማሊያ ጋር መገናኘቱ ትኩረት ሳበ፡፡ በቀሪዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያዎች የማለፍ ዕድሉ የተመናመነው ብሔራዊ ቡድኑ በተፎካካሪነት ከፍተኛ ልምድ እንደሚያገኝ ቢጠበቅም በፌዴሬሽኑ በኩል የወዳጅነት ጨዋታዎች እንዲያገኝና በረጅም እቅድ ሊታሰብለት አለመቻሉ ይስተዋላል፡፡ አሰልጣኝ ቶም ሴንትፌይት ወደ ቤልጅየም ለዕረፍት ተጉዘው ከተመለሱ በኋላ ላለፉት 4 ሳምንታት የተጠናከረ ልምምዱን በደብረ ዘይት ሲሰራ ለቆየው ብሔራዊ ቡድኑ በምክትል አሰልጣኝነት ሰውነት ቢሻው ተሹመዋል፡፡
ሉሲ ለለንደን ኦሎምፒክ 180 ደቂቃ ቀራቸው
በለንደን ኦሎምፒክ አፍሪካን ወክለው የሚሳተፉ ሁለት ብሄራዊ ቡድኖችን ለመለየት ከሳምንት በኋላ ደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ናይጄርያ ከካሜሮን ይገናኛሉ፡፡ አፍሪካን በመወከል በኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ የሚሳተፉትን 2 ብሄራዊ ቡድኖች ለመለየት በሚደረገው የመጨረሻ ግጥሚያ አራቱ ቡድኖች 4 የደርሶ መልስ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ፡፡ የዛሬ ሳምንት በጆሃንስበርግ የደቡብ አፍሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የኢትዮጵያ አቻውን ሲያስተናግድ አቡጃ ላይ ደግሞ ናይጄርያና ካሜሮን ይጫወታሉ፡፡
የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች አጀማመር ተቃውሷል
በአውሮፓ የእግር ኳስ ታላላቅ ሊጎች የ2011-12 የውድድር ዘመን አጀማመር ያማረ አልሆነም በእንግሊዝ በህዝባዊ አመጽ፣ በጣሊያንና በስፔን በተጨዋቾች ማህበራት የስራ ማቆም አድማዎች የየሊጐቹን አጀማመር አቃውሰዋል፡፡ 20ኛ ዓመቱን የያዘው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ባለፈው ሳምንት ሲጀመር በመላው አገሪቱ ተቀጣጥሎ የነበረው ህዝባዊ አመ እንዳያውከው ተሰግቶ ነበር፡፡ በእንግሊዝ ባለፈው ሰሞን በተቀሰቀሰው ዓመ መካሄድ የነበረባቸው ሶስት የካርሊንግ ካፕ ግጥሚያዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ስልጣን አገኘች
የሸራተን የስዕል አውደ ርእይ አርብ ይከፈታል
በየዓመቱ ሲካሄድ የቆየው የሸራተን የስዕል አውደ ርእይ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በመቀጠል ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የተሰበሰቡ የአርባ ሦስት ኢትዮጵያውያን ሥራዎች እንደሚቀርቡበት ተገለፀ፡፡ በመጪው አርብ ጧት በሆቴሉ በሚከፈተው የአራት ቀናት አውደ ርእይ ዋጋቸው ከአንድ ሺህ እስከ 100 ብር እና ከዚያም በላይ የሆኑ 400 ሥዕሎች ለሕዝብ ይቀርባሉ፡፡ የዛሬ አራት አመት በስምንት አርቲስቶች የስዕል ሥራዎች የተጀመረው አውደ ርእይ አምና የ40 ሰዓሊዎች፣ አቻምና የ30 ሰዓሊዎች ሥራዎች ቀርበውበታል፡፡
.የሸረሪት ድር.. ፊልም ነገ ይመረቃል
በመዋዕል ታደሰ ተፎ የተዘጋጀው ..የሸረሪት ድር.. የአማርኛ ፊልም ነገ ከቀኑ 8 ሰዓት በዋነኝነት በሐርመኒ ሆቴል የሚመረቅ ሲሆን በአዲስ አበባ ፊልም ቤቶችና በሌሎች ከተሞች በተመሳሳይ ዕለት እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡ የ100 ደቂቃ ልብ አንጠልጣይ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት እንደፈጀ አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ አሸባሪነትን ብጡ በማድረግ በተሰራው ፊልም አርቲስት ችሮታው ከልካይ፣ እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ፣ አልማዝ ኃይሌ፣ ጃንክሎዝ ሮዜል፣ ሰብለ ተፈራ፣ ታጠቅ መለሰና ሌሎችም ተውነዋል፡፡
የ..ንሥር ዐይን.. ከ10 ዓመት በኋላ ታተመ
ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የዛሬ 10 ዓመት አሳትሞት የነበረውን ..የንስር ዐይን.. የተሰኘ ም ልብወለድ መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ አሳትሞ ለገበያ አቀረበ፡፡ በማህሌት አሳታሚነት የታተመው ይሄ መጽሐፍ በ35 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ የኬምስትሪ መምህር የነበረው ደራሲ ፍቅረ ማርቆስ፤ ..ከቡስካ በስተጀርባ..፣ ..ኢቫንጋዲ..፣ ..የዘርሲዎች ፍቅር.. እና ..አቻሜ.. በተሰኙት የልብወለድ ሥራዎቹ እንዲሁም Land of The Yello Bull በተሰኘው የከቡስካ በስተጀርባ ትርጉም መጽሐፍ እንዲሁም፡፡ በሌላ በኩል የኦሾ መጽሐፍ በቴዎድሮስ ካሬ እና በይልቃል አያሌው ..የመኖር ጥበብ.. በሚል ርዕስ ለንባብ በቃ፡፡ የመጽሐፉ ዋጋ 27 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡
..የራስ ምታት.. ነገ ይመረቃል
በአቶ አስመሮም ወልደጊዮርጊስ የተጻፈው ..የራስ ምታት.. የሳይንስ ልቦለድ መጽሐፍ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል በሩሲያ ሳይንስ እና ባህል ማዕከል እንደሚመረቅ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር አስታወቀ፡፡ማህበር ከዚህም ሌላ በተመሳሳይ ስፍራ ትናንትና የሥነ ጽሑፍ ምሽት አቅርቧል፡፡ በምሽቱ አንጋፋና ወጣት ፀሐፍት ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
የአጭር ፊልም አሸናፊዎች ይሸለማሉ
ብሉ ናይል ፊልም እና ቴሌቪዢን አካዳሚ፣ ከስዊዘርላንድ ኤምባሲ እና ከጀርመን የባህል ተቋም (ጎተ) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአጭር ፊልም ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን አሸናፊዎች በመጪው ረቡዕ በጎተ በሚከናወነው ሥነ ሥርዓት የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ፡፡ የአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ኃይሌ በተለይ ለአዲስ አድማስ እንደገለት፤ ለአሸናፊዎቹ ከ3 እስከ 10ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ይደረጋል፡፡