ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ መንግሥትን ለዜጎች ረሃብ ተጠያቂ አደረጉ
ርቅ ምክንያት ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች ከአምናው በእጥፍ መጨመሩ አሳሳቢ እንደሆነ የገለ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት፤ ለረሃብተኞቹ አስቸኳይ እርዳታ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በመጥቀስ ለረሃቡ መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡በአምስት ዓመታት የእርሻ ምርት በ40 በመቶ እንደጨመረ የሚገልው መንግሥት፤ በድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ 4.5 ሚ. ሰዎች ከመጠባበቂያ ክምችት እርዳታ እየተከፋፈለ እንደሆነ ገልል፡፡
የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ መጽሐፍ ወጣ
በኢህአዴግ መታለላቸው እንደሚቆጫቸው ይናገራሉ
• ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ለፕሬዚዳንትነት ታጭተው ነበር
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ህይወት የሚተርከው ..የነጋሶ መንገድ.. የተሰኘ አዲስ መሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ በኢህአዴግ ለ10 ዓመት መታላለቸው እንዳስቆጫቸው በመሐፉ የተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ፤ ..ኢህአዴግ ሶሻሊዝምን ጠረጴዛ ሥር የከተትነው በ84 ዓ.ም ነው፤ የምንመራው በነጭ ካፒታሊዝም ነው.. ማለቱ ዱብ ዕዳ ሆኖባቸው እንደነበር ገልዋል - ከፓርቲው የወጡበት ዋናው ምክንያትም ይሄው እንደሆነ በመጠቆም፡፡
ዛሬ ደራሲ አዳም ረታ ከአንባቢዎቹ ጋር ይወያያል
ዛሬ በሀገር ፍቅር ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ከጠዋቱ 3 ሰዓት አንስቶ ደራሲ አዳም ረታ ከአንባቢዎቹ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ የማህሌት አሳታሚ ድርጅት ባስተባበረው በዚህ ዝግጅት ላይ ደራሲው ከሚያደርገው ውይይት በተጨማሪ ሁለት ምሁራን በአዳም ረታ ሥራዎች ላይ ጥናት ያቀርባሉ፡፡
የህገወጥ ፊልሞች ኪሳራ በዝቷል
በህገጥ መንገድ ከኢንተርኔት ተሰርቀው በዓለም ዙሪያ ለገበያ የሚሰራጩ የፊልም ስራዎችና የሙዚቃ አልበሞች በዓለም የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያስከተሉት ኪሣራ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ መድረሱን ..ዩ ኤስ ኤ ቱዴይ.. አስታወቀ፡፡ ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያገኘናቸው ሪፖርቶች እንዳመለከቱት፤ በዓለም ዙሪያ በሚከናወነው የህገወጥ ፊልሞች የገበያ ስርጭት ሆሊዉድ በዓመት 25 ቢሊዮን ዶላር እየከሰረ ነው፡፡
ጆኒ ዲፕ በ..ፓይሬትስ.. ፊልሞቹ ገቢው 350 ሚ.ዶላር ደረሰ
ጆኒ ዲፕ ..የፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያንን.. 5ኛ ክፍል ለመስራት ስምምነት ማድረጉን ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር አስታወቀ፡፡ የፊልሙ 4ኛ ክፍል ..ፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያን ስትሬንጅ ኦፍ ታይድስ.. በዓለም ዙሪያ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት የዓመቱን ከፍተኛ የገበያ ስኬት አስመዝግቧል፡፡ ጆኒ ዲፕ ከ..ፓይሬትስ ኦፍ ካራቢያን.. 5ኛ ክፍል ፊልም የሚያገኘው የገቢ ድርሻ 350 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ተነግሯል፡፡
..የእኔ ጀግኖች.. የስዕል አውደ-ርዕይ አርብ ይከፈታል
በሰዓሊና መምህር ኃይሉ ክፍሌ የተዘጋጁ ከ60 በላይ ስዕሎች የሚቀርቡበት ..የእኔ ጀግኖች.. የስዕል አውደ ርዕይ በመጪው አርብ 5 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዘክር አዳራሽ ይከፈታል፡፡ k3000-50,000 ብር የሚያወጡ ስዕሎች ለገበያው የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ፤ እስከ ሐምሌ 22 በነጻ ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
ስውር መንገደኞች.. ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ዛሬ ይጀመራል
..የሶስት ወር ምርኮኛ.. ቴአትር ይመረቃል
አልሳቤጥ መላኩ ወደ ትወናው ተመለሰች
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በርካታ መጣጥፎችን በመጻፍ የሚታወቀው አንተነህ ይግዛው የጻፈው ..ስውር መንገደኞች.. የሬድዮ ድራማ፤ ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት በፋና FM 98.1 እና በክልል FM ጣቢያዎች መደመጥ ይጀምራል፡፡ ዘካርያስ ብርሃኑ ባዘጋጀውና ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ፕሮዲዩስ ባደረገው የ52 ሳምንት ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ከ6 ዓመት በላይ ከትወና መድረክ ርቃ የነበረችው ተዋናይት አልሳቤጥ መላኩ ከሰባት ዋነኛ ተዋናይ አንዷ በመሆን ትተውናለች፡፡
1/2 ሌሊት - 1001 ትዝታ
..ኧረ መርሳ በለኝ!.. እያለ ትንሹ ትልቁ ደረሳው ወልዩ በፍቅር የሚወዳት የአባትዬዋን መንበር፤ የሸህ ሚዕዋን መንደር-መርሳን ከተማዬ ሃብሩን ወረዳዬ እያልኩ መኖር ከጀመርኩ አምስት ወር እንኳን አልሞላኝም፡፡ እኔ አንዷንም ሳላቃት የእሷ አድርጋኝ ከወዳጆቿ ቀላቅላ በዱአዋ እቅፍ ድግፍ አድርጋ አቀማጥላ የያችኝ ሃብሩ፤ አንዳንዶች እንደተረኩልኝ ስፋቷ የአንድ ጠቅላይ ግዛት ያህል ቢገዝፍብኝም፤ ጓዳ ጐድጓዳዋን አብጠርጥሬ ላውቀው ምኞቴ ነበር፡፡
ኦባማና ግራ የተጋባው የአፍሪካ ፖሊሲያቸው
ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ሥልጣን በመጡበት ወቅት፣ በአፍሪካ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ለመደገፍ ከአፍሪካ ጐን እንደሚቆሙ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በርካታ አፍሪካዊያንም በኦባማ የአስተዳደር ዘመን፣ በአሜሪካ ከእርሳቸው በፊት ከነበሩት መሪዎች በተሻለ ጠንካራ ግንኙነት እንደሚኖር ጠብቀው ነበር፡፡ በተለይም የአባታቸው የትውልድ አገር ኬንያ መሆኗ አፍሪካዊያን ለዲሞክራሲ ሥርዓት በሚያደርጉት ትግል የላቀ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉም ተገምቶ ነበር፡፡
1የቤተክህነትና የገዳሙ ውዝግብ
የዛሬ አርባ ዓመት የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የልጅ ልጅ ልዕልት ሂሩት ደስታ ለቅዱስ ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አስተዳዳሪዎች የሚያስደስት መልዕክት ያዘለ ደብዳቤ ላኩ፡፡ደብዳቤው ልዕልቷ በደብሩ አውደምህረት ሥር ባሉት ቤተ አማኑኤል እና መድሐኒያለም ቤተKRStEÃN መካከል በ1956 ዓ.ም ያሠሩትን ..ሰባት ወይራ ሆቴል.. ላሊበላ ቤተKRStEÃN በስጦታነት ማበርከታቸውን የሚያበስር ነበር፡፡ገዳሙ ስጦታውን ከተቀበለ አራት ድፍን ዓመታትን እንኳን በቅጡ ሳይቆጠር በደርግ ከተወረሱት በርካታ ቤቶች መካከል አንዱ ሆነና በጊዮን ሆቴሎች አስተዳደር ድርጅት እጅ ወደቀ፡፡