Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

አቶ እቁባይ “ገመና” የቴሌቪዥን ድራማ በማሰናዳትና በማቅረብ ይታወቃሉ
በኢህአዴግ ገንዘብ ከተቋቋሙት የንግድ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው ሜጋ ኢንተርፕራይዝ፣ የገቢ ግብር፣ የሰራተኞች ታክስ እንዲሁም ቫት ተሟልቶ አልተከፈለም በሚል በቀረቡ ሶስት ክሶች የቀድሞ ስራ አስኪያጅ አቶ እቁባይ በርሄ ትናንት ሃሙስ ጥፋተኛ ነህ ተብለው ታሰሩ።
ሜጋ ኢንተርፕራይ ወደ 40 ሺ የሚጠጋ የትርፍ ግብር ሳይከፍል እንደቀረና ይህም ገቢውን በማሳነስ የተፈፀመ እንደሆነ የሚገልፅ ነው አንደኛው ክስ። ሌላኛው ክስ፤ አራት መቶ ሺ ብር የቫት ክፍያን የሚመለከት ሲሆን፤ ሶስተኛው ክስ ከሜጋ ኪነጥበባት ማዕከል ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተገልጿል።

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት የ66 አመቱ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ ከሃላፊነት የለቀቅኩት በህመም ሳይሆን ስልጣን ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው አሉ፡፡
ለህክምና ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ተከትሎ ለህይወታቸው የሚያሰጋ ህመም እንደገጠማቸው፣ የደም ካንሠር እንደተገኘባቸው እና ሌሎች ወሬዎች ሲናፈሱ እንደቆዩ የጠቆሙት ዶ/ር ሀይሉ፤ ሁሉም ከእውነት የራቁ እንደሆኑና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለሚኖረው ተሳትፎ የብቃት መፈተሽያ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያዘጋጀው ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የወዳጅነት ጨዋታዎቹን ለማዘጋጀት የተለያዩ ጥረቶች ቢያደርግም ሳይሳካለት እንደቀረ የታወቀ ሲሆን አንድ የስፖርት ጋዜጠኛው በግሉ ባደረገው ጥረት ሦስት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ማስገኘት ችሏል፡፡ ጋዜጠኛው የወዳጅነት ጨዋታዎች የብሄራዊ ቡድኑን አቅም ለመፈተሽ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በማመን ከፍተኛ ጥረት ማድረጉን ገልፆ፤ ከተለያዩ ቡድኖች ጋር ለዝግጅት መጫወት የቡድኑን አቅም ያጠናክራል ብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት እሁድ በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል በተካሄደ የመፃህፍት ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ 12 መፃህፍት ተመረቁ፡፡ የመፃህፍቱ ደራሲ አበባ ሽታዬ እንደገለፀችው፤ አንደኛው “ብርቱ ሰልፍ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሲሆን አስራ አንዱ ደግሞ በአማርኛና በኦሮምኛ የተዘጋጁ የህፃናት የተረትና የትምህርት መርጃ መፃህፍት ናቸው፡፡ የግጥም መድበሉ በ20 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን የህፃናት መፃህፍቱ ከ10ብር-15ብር እየተሸጠ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተካሄደው የመፃህፍቱ ምረቃ ሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ በአምቦ ተመሳሳይ ምረቃ እንደተደረገ ደራሲዋ ተናግራለች፡፡

ላፎንቴን በሚል ስያሜ ከሙያ አጋሩ ከታደለ ሮባ ጋር አራት አልበሞችን ለአድማጭ ጆሮ ያደረሰው ድምፃዊ ብርሃኑ ተዘራ “ተበቺሳ” በሚል ርዕስ የሰራውን አዲስ የሙዚቃ አልበም የፊታችን ሰኞ ለገበያ እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ አልበሙ 14 ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን የሙዚቃ ቅንብሩን ካሙዙ ካሣ፣ ሔኖክ ነጋሽ፣ እዩኤል መሀሪ፣ ኤፍሬም ብርቅነህ፣ መኮንን ለማ እና መታፈርያ በቀለ እንደተሳተፉበት ተገልጿል፡፡ አልበሙን ያሳተመውና የሚያከፋፍለው ቮካል ሪከርድስ ነው፡፡ ድምፃዊው ከተለያዩ ነባርና ጀማሪ ድምፃውያን ጋር ነጠላ ዜማዎችን የሰራ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ “ኤሌያባ”፣ “ያምቡሌ” እና “አንበሳው አገሳ” የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

“ማስታወሻ” በሚል ርዕስ በደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ ተዘጋጅቶ በ1993 ዓ.ም በታተመውና የደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔርን የሕይወትና የሥራ ታሪክ በሚያስቃኘው መጽሐፍ “ነጂና ተነጂ” በሚለው ምዕራፍ ላይ፣ ስለ ቀድሞ ዘመን ሥራ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያኖች የሚነገር ታሪክ አለ፡፡ አንደኛው የደራሲ ስብሐት ጓደኛ ነው፤ አቶ ደረጀ ይልማ ይባላል፡፡ ለገንዘብ ግድ የለውም፡፡ ከፈለገም በቀላሉ ሠርቶ ያገኘዋል፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም በቀላሉ ገንዘብ ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ ይችላል፡፡ 

ግጥም የማይወድ ሰው ስለ ግጥም አስተያየት መስጠት የለበትም ይላሉ- የስነጽሁፍ ምሁራን፡፡
ምክንያቱም ግጥምን ጠለቅ ብሎ ለማየት የተሳለና የተሞረደ ልብ ይፈልጋልና፡፡
ለምሳሌ ልጆች ዜማ ስለሚወድዱ ዋነኞቹ ሃያስያን ህጻናት ናቸው የሚሉት ደግሞ ቆየት ያሉት ደራሲ ኢ. ኤ. ግሪኒንግ ላምቦርን ናቸው፡፡
“Children are naturally good critics of poetry,for they are akin to the poet,who is the child of the race..” ግጥም የማይወድ ሰው ግጥም ላይ አስተያየት ይስጥ ማለት፣ ወይን የማይወድ ሰው ስለ ወይን አስተያየት ይስጥ እንደማለት ነው የሚሉት ታላቁ የሥነ ግጥም ተመራማሪ ፔሬኔ ናቸው፡፡ የመዳኘት አቅም ለማግኘት፣ጥሩና መጥፎውን አንገዋሎ ፣ ከፊል ጥሩና-ጥሩን ለመለየት ፍቅር፣ ዕውቀትና ልምምድ ይጠይቃል-ባይ ናቸው ባለሙያው፡፡እንደኛው በአገራቸው ላይ ከሚታተሙት ግጥሞች ጥቂቶቹ ብቻ ነፍስ ያላቸው እንደሆኑ የሚናገሩት ምሁሩ፤ ከመንጋው ውስጥ ጥቂቱን መዝዞ ማውጣት ጥሩ መሆኑን ያምናሉ፡፡ ለመመዘንም ልክ ሬክታንግል ስፋት ጎንና ርዝመቱን ለክተን እንደምናገኝ ሁሉ የምንለካቸው ነገሮች አሉ፤ግን የሬክታንግሉን ያህል ቀላል አይደለም፡፡

Saturday, 22 December 2012 10:47

ምርኮ

ለማን ያካፍል ሚስጥሩን? ደግሞስ ምን ብሎ ነው የሚያካፍለው? ለምንም የማይመች ነው ነገሩ፡፡
ምንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ማድረግ የተገደደውን ግን አደረገ፡፡ ለአንድ ሺ አንድ ጊዜኛ የቀኝ እጁን መዳፍ ተመለከተ፡፡ አዲስ ድንጋጤ/ያየውን ነገር ሊለምደው አልቻለም፡፡ ልቡ እንደሚበጠር ጤፍ ሳሳበት፣ ለዝናብ እንደተጋለጠ አሸዋ ተሸረሸረበት፡፡
ደጋግሞ ስለተመለከታቸው ነው መሰል ትኩረት የሰጣቸው የመዳፉ መስመሮች ጐልተው ታዩት፡፡
አንዳንዶቹ ለዘመናት የጅረት መውረጃ ሆነው ያገለገሉ ያህል ጉልህ ናቸው፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ጉንዳን የሄደበትን መንገድ የመፈለግ ያህል አስቸጋሪ ይሆናሉ፡፡ ዋናው ነገር፣ እነዚህን መስመሮች ከተለያየ አቅጣጫ በመመርመር ስለራሱ አንድ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንደሚቻል ተምሮአል፤ ደርሶአልም፡፡

በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት በተጋጋለበት በ1984 ዓ.ም ነበር የእስራኤል ጦር ሃይልና የስለላ ድርጅቱ ሞሳድ አስር ሺ የሚሆኑ ቤተእስራኤላውያንን፣ በሱዳን በኩል በአውሮፕላን በማጓጓዝ የዘመናት ተስፋና ጉጉታቸውን እውን ያደረጉላቸው፡፡ ይህንን ወደ ተስፋይቱ አገር የተደረገ ጉዞ (አሊያህ) ቤተእስራኤሎቹም ሆኑ የእስራኤል መንግስት “ዘመቻ ሙሴ” በሚል ስያሜ እስከዛሬ ድረስ ከፍ ባለ አድናቆት ያስታውሱታል፡፡ የእስራኤል የጦር ሀይልና የደህንነት ጐበዛዝት በ“ዘመቻ ሙሴ” አስር ሺ የሚሆኑትን ቤተእስራኤላውያን ወደ ቅድስቲቱ የተስፋዋ ሀገራቸው ማጓጓዝ ቢችሉም ልባቸው ገና ጨርሶ አላረፈም ነበር፡፡ ምነው ቢባል ዘመቻውን እያካሄዱት የነበረው የአረብ ሊግ አባል፣ እስላማዊና እንደ እስራኤል “ጠላት” ሀገር ተደርጋ በምትቆጠረው በሱዳን ውስጥ ስለነበር ነው፡፡ በዚህ የተነሳ እስራኤል ውስብስቡን “ዘመቻ ሙሴ”ን በተቻላት አቅም ሁሉ ለማፋጠን ብትሞክርም አጥብቃ የፈራችውን ነገር ማስቀረት አልቻለችም፡፡ 

በሶስት አህጉራት ተዘዋውሮ እግር ኳስን በፕሮፌሽናል ደረጃ በመጫወት ትልቅ ስም ያተረፈው ኢትዮጵያዊው ፍቅሩ ተፈራ ለሜሳ ማክሰኞ ዕለት ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዟል፡፡ የ26 ዓመቱ ፍቅሩ በደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ክለብ ለመጫወት ወደዚያው አገር ሲሄድ የሰሞኑ ለ3ኛ ጊዜው ሲሆን ዋናው ምክንያት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመካተት በ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ወደ አውሮፓ ክለቦች የሚዛወርበትን እድል ለማመቻቸት ነው፡፡ እግር ኳስ በክለብ ደረጃ በአዳማ ከነማ በመጫወት የጀመረው እና አሁን 26ኛ ዓመቱን የያዘው ፍቅሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከ8 ዓመታት በፊት ለሁለት የውድድር ዘመናት 55 ጨዋታዎች አድርጎ 26 ጎሎች ከማግባቱም በላይ ከክለቡ ጋር ሁለት የፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫዎች እና አንድ የሱፕር ካፕ ድልን አጣጥሟል፡፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 25 ጨዋታዎችን በማድረግ ሰባት ጎሎችን በስሙ ያስመዘገበው ፍቅሩ ተፈራ በእግር ኳስ ተጨዋችነት ኢትዮጵያን በተለያየ የዓለም ክፍል ለማስጠራት መብቃቱን እንደከፍተኛ ስኬት ይቆጥረዋል፡፡ ፍቅሩ ተፈራ ከስፖርት አድማስ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በደቡብ አፍሪካ ክለቦች ስለነበረው ቆይታ፤ በአውሮፓ በቼክ እና ፊንላንድ ክለቦች እንዲሁም በኤስያ በቬትናም ክለብ ስላሳለፈው ልምድ ይናገራል፡፡ በቅርብ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ የነዋሪነት መታወቂያውን ያገኘው ፍቅሩ በጆሃንስበርግ ከተማ መኖርያውን ገዝቷል፡፡ ስለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የ29ኛው አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እና ዝግጅት እና በተያያዥ ጉዳዮች የሰጣቸው ምላሾች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

Page 5 of 163