ልብ-ወለድ

Saturday, 04 September 2021 17:14

የምርቃናዎች ወግ

Written by
Rate this item
(5 votes)
በጫት ሳቢያ ከሥራ ተባርሬያለሁ፡ የምቅመው ለማንበብ ነው፡፡ ሰሞኑን የሊዮ ቶልስቶይን War and Peace በቶልስቶይ አይነት ተመስጦ እያነበብኩ ነው፡፡የመቃሚያ ብር የለኝም፡፡ እንዳልኩት የምቅመው ለማንበብ ነው፡፡ መቃሚያ ብር ስላልነበረኝ ግን War and Peace ን ሸጬ ወደ ጫት ቤት ሄድኩኝ፡፡እንግዲህ ጫት እዚህ ድረስ…
Rate this item
(4 votes)
...እስከ መቼ? እላለሁ። "እስከ መቼ እንደዚህ የተደጋገመ ጣዕም አልባ ኑሮ እኖራለሁ፤ እንኖራለን? ሰዎች ይወለዳሉ፤ ሰዎች ይወልዳሉ፤ ሰዎች በምቾትና በአግባብ የማያሳድጉትን ልጅ ይወልዳሉ፤ ሰዎች ይበደላሉ፤ ሰዎች ይበድላሉ፣ ጥፋተኞች የወንጀላቸውን ዋጋ አያገኙም። እንዴት ነው ነገሩ? ይሄን ሁላ እየታገስን የምንኖረው እስከ መቼ ነው?’…
Sunday, 22 August 2021 13:12

ቀስቶ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
(የአጭር አጭር ልብወለድ) ቀስቶ በስካር ካልናወዘ፣ እርቃኑን የሆነ ይመስለዋል፡፡ በተለይ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ ከብርሌ ጋር ተኳርፎ ብልጧን መጨበጥ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ፤ አዲስ ዓመል አውጥቷል፡፡ ጥቂት ከውሃው ከወሳሰደ፣ ምላሱ እንደ ቀትር እባብ ነው፤ የሚንቀለቀለው፡፡ ስካሩ፣ ትላንቱን እንደ መስታወት ወለል አድርጎ ያሳያዋል።…
Rate this item
(3 votes)
 አልተኛም...ከምወደው እንቅልፌ ከተኳረፍኩ ሰነባብቻለሁ...በርግጥ "ከምወደው እንቅልፌ.." የሚለው ማሽቋለጥ፣ እንቅልፋም መሆኔን የሚመሰክር አይነት በፍፁም አይደለም።ቀድሞም "ሰው ከሙሉ ቀኑ ከስድስት የሚዘለውን ሰዐት ጨፍኖ ማሳለፍ የለበትም... ኪሳራ ነው!" ብዬ ወገቤን ይዤ የምከራከር አይነት ነኝ።ቢሆንም ቢሆንም... ሩብ ቀኔን በሰላም የምተኛው ቆንጆ እንቅልፍ ነበረኝ። እና…
Rate this item
(5 votes)
በትልቁ መተላለፊያ መንገድ አካባቢ የተሰባሰቡ ሰዎች በተደጋጋሚ በማስጠንቀቂያ ድምጽ እያሰሙ ነበር፡፡ ‹‹ኦቬጆን! ኦቬጆን ይሆን እንዴ?›› ሆኖም የሚቦነውን አቧራ ወደ ወርቃማነት ከምትቀይረው ጸሐይ ጨረሮች በስተቀር በመንገዱ ላይ ምንም የሚታይ ነገር አልነበረም፡፡ማንም የእርሱን ውልብታ ተመልክቶ አያውቅም፡፡ እስካሁንም እርሱን በመፈለግ የጋለ ፍላጎት፣ ከዛኑታ…
Monday, 02 August 2021 20:43

ስድስተኛው ሃጢኣት

Written by
Rate this item
(4 votes)
የሆነ ስህተት ኣለ! ከእያንዳንዷ አላፊ ቅፅበት ህማምን ወይም ሃሴትን ማግኘት ነበረብኝ። ደቂቃዎችን ማቆም ወይም አብሬአቸው መብረር ነበረብኝ። ሹክሹክታቸውን ማድመጥ ወይም ህልሜን ማጋራት ነበረብኝ። ከቶም እንደሌለሁ ቆጥረው የረጉ ከመሰሉ ግን ችግር አለ። አሻራ እንኳ ሳይተውብኝ ጥለውኝ ከበረሩ ስህተት አለ። ለምን ሰለቸኝ?…
Page 12 of 67