ልብ-ወለድ

Rate this item
(4 votes)
ከላቦራቶሪው ውጤት ይልቅ የብሔራዊ ቡድኑ ውጤት ነው ያጓጓው፡፡ ጓደኞቹ ከስቴዲየም ደውለው ስለ ተመልካቹ ወረፋ አጋነው ነገሩት፡፡ ህዝቡ ለነገው ጨዋታ ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይዟል፡፡ ስጋት ገባው። እሱ ክሊኒክ ውስጥ ቁጭ ብሎ የምርመራ ውጤቱን ሲጠባበቅ፣ ስቴዲየሙ ሊሞላ ይችላል፡፡ የጓጓለትን የብሔራዊ ቡድኑን ጨዋታ…
Saturday, 22 June 2013 11:47

እምቢኝ!

Written by
Rate this item
(1 Vote)
በእኔና በእነሱ መካከል ያለው ድልድይ ገና ጨረታ አልወጣለትም፡፡ እኔ የተፈለቀቅሁት ከገዛ ጥጥ ማሳዬ ነው፡፡ እነሱ ሊያባዝቱኝ ከንቱ ይደክማሉ፡፡ አለም ደግሞ (ቁሌታም) እንዝርት ናት፤….ለሰበቃት ጭን ምትገልጥ!....እሷ……….እኔ………..እነ’ሱ…ሥጋት ላይ ተወዝቼ እሰማለሁ እኔ…(እሷ ጆሮ ዳባ ብላለች፡፡)እነሱ መች ያርፋሉ…ቅኝቱ እንደፈረሰ ሙዚቃ ጣም አጥተው፡፡ ***ከጆሮዬ ጥግ…
Saturday, 15 June 2013 11:18

ሕልምና ቅዠት

Written by
Rate this item
(0 votes)
እሷ ይኸ ሕይወትን በጅምላ የሚያስሮጠኝ ዕድሜ፣ ቀኔን እንደ ጉልት ሽንኩርት ሲቸርችረኝ ይውልና መኖሬን ሲያዝለው፣ የድካሜን ጣመን ልወጣ እተኛለሁ፡፡ እናም የተስፋዬን ምንጣፍ ነገዬን ዘርግቼ ተኛሁ፡፡ እንደተኛሁ ሰመመን ይመስል አንዴ ሲያሸልበኝ ወዲያው እየባነንኩ ጥቂት ከቆየሁ በኋላ ድካሜ በርትቶ ዕንቅልፌ ጭልጥ አድርጐ ወሰደኝ፡፡…
Saturday, 15 June 2013 11:12

ቀጠሮ

Written by
Rate this item
(1 Vote)
እንደ ማሰላሰያ አስታውሳለሁ፤ ድሮም እኔ ነበርኩ፡፡አሁንም እኔ ነኝ፡፡ እንደሌሎቹ “እኔ” ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ ድሮም አልነበርኩም፡፡ አሁንም አይደለሁ፤ ስጨርስም አልሆንም፡፡ “እና ታዲያ ምንድነው ችግሩ?” ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ ጠያቂው እራሴ፤ መልሱን ሳልመልስ ተመልሼ ዝም እላለሁ፡፡ ከድሮውም ፀሃፊ መሆንን እፈልጋለሁ ስል የሰማኝ ማንም የለም፡፡…
Saturday, 08 June 2013 08:37

እንጀራ ፈላጊ

Written by
Rate this item
(5 votes)
ጋዜጣ አዟሪ ነኝ፡፡ ካዛንቺስ፣ ሃናን ዳቦ ቤት አካባቢ ጋዜጦችን ታቅፌ ስዞር የምውል ጋዜጣ አዟሪ፡፡ ጋዜጦችን እሸጣለሁ፡፡ ጋዜጦችን አከራያለሁ፡፡ በመደዳ ከተሰደሩት ካፌዎች በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ሻይ ቡና ለሚሉ ተስተናጋጆች ጋዜጦችን አቀርባለሁ፡፡ አንዳንዶች ይገዙኛል። አንዳንዶች ገለጥ ገለጥ አድርገው አንብበው ሽልንግም፣ አንድ…
Saturday, 08 June 2013 08:22

የመግደል ጥበብ

Written by
Rate this item
(4 votes)
ካለፈው የቀጠለ ምዕራፍ አራት፡ - የድብርት ቀን አንድ ቀን አመመኝ ብዬ ከትምህርት ቀርቻለሁ፡፡ ማመም ሳይሆን በቃ የዚያን ቀን እንዲሁ ደብሮኛል። ያው እናቴ ነገሮችን ያለ ምክንያት እንደማላደርግ ስለምታውቅ እንድቀር ፈቀደችልኝ፡፡ “ግን ምንህን ነው ያመመህ?” አለችኝ፤ ሻሿን እያሰረች፡፡ “እውነቱን ልንገርሽ ጆርጌ?” እናቴን…