የግጥም ጥግ
ልለምንህ ጣና - ልማጠንህ ዓባይ - አዋሽ እሺ በለኝአገሬ ተድራ - አገር ጠርቻለሁ - የአገር ድግስ አለኝ፤አገሩን የዳረ - አገር ህዝብ የጠራለአገር የጠመቀ - ለአገር የደገሰ፣መሬቱ እንጀራው ነው - ሀይቁም ወይንጠጁመች ይጨንቀውና - ደረሰ አልደረሰ፤ይኸው አገር መጣ!ይኸው አገር ወጣ!አገር ድግስ…
Read 8784 times
Published in
የግጥም ጥግ
እንደመግቢያክፍት የሥራ ቦታግጥም ፅፌ ፅፌ፣አላነብም ብሎ ሰዉ ቢያስቸግረኝ“ክፍት የሥራ ቦታ”፣ የሚል ከባድ ርዕስ-ያለው ግጥም ፃፍኩኝ!ማ ጮክ በል አለኝ?... ተሻማ ህዝብ ሁሉ፣ግጥሜን ገዛልኝ!በየቤቱ ሄዶ-ተስገብግቦ ጠግቦ፣ ዋለበት ቢመቸው-ሦስቴ አራቴ፣ አምስቴ፤ ደጋግሞ አነበበው-ግጥሙ እንዲህ አለቀ፡-“ውድ አንባቢዬ ሆይ በቢሮ፣ በቤትህ፣ በፍራሽ ላይ ያለህመንግስት ያላየውን፣…
Read 20401 times
Published in
የግጥም ጥግ
ፍቅር ሽልማት የለውም አንተ ግን ሽልማት አለህ!እንደ ትንቢት - ተናጋሪ፣ የነገን ዕውቀት አበጀህ!የእናት ያባት ዕውቀት ማለት፤ የልጅ ሽልማት ውብ ኩራት!!የራስህ ትምርት ትጋት የራስህ ትምርት ንጋት የዛሬህን ጐዶሎ፣በነገ ጥበብህ መሙላትይሄ ብቻ ነው ዓለምህ፣ የራስህ ፍቅር ጉልላት!!(ነ.መ፤ ኢዮብና አሥቴር ለፍቅር የትምህርት ድል)ሰኔ…
Read 4466 times
Published in
የግጥም ጥግ
አፈር-አፈር ይብላ፤ ለእግዜር እግዜር ይየው፤ እንዴት ነው የሣት ፍም በአፈር የሚቆየው እንዴት ነው ነበልባል - በእሣት የሚጋየው ኮከብ እንዴት ብሎ - ለአፈር ይገዛል? እንዴት ፀሐይ - ወርዶ መሬት ይያዛል?አፈር አፈር ብላ - አጥንቷ ይንሣህ ሥጋዋ ረፍት ይንሣህ ሀሣብዋ ይነቅንቅህ!መልክ አይሁንህ…
Read 3661 times
Published in
የግጥም ጥግ
ኩርማን መግቢያ እግዜር ከሞላው ኩሬ ውስጥ ፣ እስቲ እንዋኝ ብለን ገብተን ሳንጨርሰው ውሃው ደርቆ፣ መካከል ላይ ዋጋ ከፈልን!ለኩሬ ዋናው ተጥፈን በውቂያኖሱ ተቀጣን!***አለሥራችን ገብተን፣ አንጨቅጭቀው እግዜአብሔርን፤ ይቅርታ እንጠይቅ እንጂ፣ ስለመፈጠራችን፤ ለመኖሪያችንማ፣ “የቀን ውሎ - አበል” አልን!ተጠባባቂ ቤንች እንጂ፣ ቋሚ ተሰላፊ አደለን!የካምቦሎጆን…
Read 5001 times
Published in
የግጥም ጥግ
ትርጉም እያዛባ፣ቃል እያናናቀ፣ፍቺ እያጣረሰ፤ከበሽታ ሁሉ የደሃ ኩርፊያ ነውሃገር ያፈረሰ።እናንተ ብልሆች!ተስፋ−ተስፋ የሚሸት እቅድ ስታቅዱ፣ንቁ−ፍኩ እንዲሆን የለውጥ መንገዱ፤‘ካኮረፈ ደሃ’ ሃሳብ አትውሰዱ! የለቅሶ ቤት አዝማችተዝካር፣እዝን፣ድንኳን፣ንፍሮ፣ሰልስት፤12፣ 40፣ 80፣ ሙት−ዓመት፤“ጐጂ ነው!” አትበሉን አቦ እናልቅስበት!እናውቃለን እኮ!አዛኞች፣ አጽናኞች በሞሉባት አምባ፤‘ግማሽ ሳቅ’ ማለት ነው ሁሉ ያየው ዕንባ።
Read 5875 times
Published in
የግጥም ጥግ