የግጥም ጥግ
በወርኃ የካቲት የሚካኤል ለታትልቅ ጠብ ተነስቶ መሬት ተቆጥታቆስሎ ግራዚያኒ ሰበብ ሆናው ደሙብዙ ሰው ታረደ ተናወጸ አለሙ፡፡በየቤቱ ለቅሶ ጩኸት በየሜዳይሰማል ይታያል በዚህ በዚያ ፍዳ፡፡የሰው ልጅ እንደ ከብት ወድቆ እየታረደሶስት ለሊት ሶስት መዓልት ከተማው ነደደ፡፡ሽንትም እንደውኃ ተሸጠ በገንዘብብልህ የሆነ ሰው ይህንን ይገንዘብ፡፡ኢዮብ…
Read 3208 times
Published in
የግጥም ጥግ
ከጠንካራው ልብሷከውስጥ ከመንፈሷውጪ ተስፈንጥሮ ከጉንጮቿ የኖረጥቁር ምልክት ከፊቷ ነበረከዛጎል ልቧ ላይከሴትነቷ ላይየማጣትን ሸማ እየፈታተለወጣትነት አልፎ እርጅና አየለይኸው ምልክቷየትላንት ጉዞዋን፣ በግልጽ የሚናገርያለፈውን ሁሉ፣ በመዳፍ የሚሰፍርከአይኖቿ በታች፣ ጥቁር ጽህፈት አለመለያ ምልክት፣ ይኸው እየመሰለማድያት አኑሮ፣ ውበቷን ሰውሮከማጣት ሀሳቧ፣ ዛጎል ልቧን ትቶካዘነው ልቧ ጋር፣…
Read 3312 times
Published in
የግጥም ጥግ
ናፍቆትሰማዩ ቀልጦይንጠባጠባልብርሀን አፍሮ ይሽኮረመማል፣ጨለማ ሆኗል፤ውኃ ተገርፎ እሳት ያነባል፣የምድር ገላ ይገሸለጣል፤ጽልመት ጎምርቶ፣ፍሬ ያፈራል የመርገምት እጽ ያጎነቁላል፤አንቺ ሳትኖሪ፣ይህን ይመስላል፡፡(ሳሙኤል በለጠ-ባማ)
Read 3252 times
Published in
የግጥም ጥግ
ጭንቅላት ዓለም ነው።ዕድል ደግሞ እንደአንገት፣ስንዞር የሚታይ…ባግራሞት፣ በድንገት።ካንገት በታች ያለው…ትውልድ የሚያስቀጥል…ዕድሜ የሚባለው የመኖሪያ ዘመን፣ሕይወት ነው ይባላል…አካል አጠቃላይ አንድ ላይ ሲተመን።(ከበቃሉ ሙሉ “እኔ እና ክርስቶስ”)
Read 3628 times
Published in
የግጥም ጥግ
ያንቺን ድምፅ ብቻ፣ ሲያቃጭል የኖረየቆለፍሺው ጆሮ፣ በምን ተሰበረ?ይኸው ብዙ ድምፆችከየትም እየመጡ፣ ይሰሙኝ ጀመረ።የዘጋሽው ልቤ!የቆለፍሽው ልቤ!የተሰባበረውእንዴት ሰው አማረው?። ። ።ልረሣሽ ነው መሠል፣ ወይ ደግሞልትመጪይሰማኝ ጀመረያውደኝ ጀመረይታየኝ ጀመረ፣ ሕይወት ካንቺ ውጪ።(በላይ በቀለ ወያ)__________________ የዕድሜ ልክ ደብዳቤይድረስ ለምወድሽ…ዓለም ያክል ሐሳብ የተሸከመ ሰው፣ዕረፍት አያገኝም…
Read 3255 times
Published in
የግጥም ጥግ
ምፀትየዘንድሮው እግዜር የኦሪቱ አይደለም፣ጥፋት ስታጠፋ- ከገነት አውጥቶአያባርርህም፤የዘንድሮ እግዜር-ኃጢአንን ሲቆጣ፤ፓርላማ ይሰዳል-ህሊናውን ትቶ እጁንእንዲያወጣእየጠበኳት ነውእየጠበኳት ነው- በሰው ሁሉ መሃልእንደይረጋግጧት ብዬ- የኔን ውብሀመልማል፤እየጠበኳት ነው -እንዳትጠፋ ድንገትመና ሆና እንድትኖር-ሳለ እርጅና ሞት፤እየጠበኳት ነው - እንዳትጠፋ ጭራሽየኔን ገጸ ጸዳይ፤ የሕመሜን ፈዋሽእየጠበኳት ነው-ከሰው ከአራዊቱ፣እስከ ነፃነት ቀን- እስኪነጋ…
Read 3159 times
Published in
የግጥም ጥግ