Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62

ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(0 votes)
የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በለጠ “የጥበባት ጉባዔ” የተሰኘ ባለ 466 ገጽ መጽሐፍ ለንባብ አበቁ፡፡ በአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት የቀረበው መጽሐፍ በኢትዮጵያ 75 ብር ከኢትዮጵያ ውጪ ደግሞ በ50 ዶላር እየተሸጠ ነው፡፡ በቋንቋ ሰብአዊ ገጽታ ላይ ያተኮረው መጽሐፍ ለደራሲው አምስተኛ…
Rate this item
(0 votes)
በአሜሪካዊው ሳም ሼፓርድ የተፃፈውና በለዓለም ብርሃኑ ተተርጉሞ የተዘጋጀው “ቦምቡ ፍቅርሽ” የተሰኘ የኮሜዲ ትያትር የፊታችን ማክሰኞ በሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ይመረቃል፡፡ ትያትሩን ፕሮዲዩስ ያደረገው ጂ አዲ የኪነጥበብ ፕሮሞሽንና ቴአትር ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡ በትያትሩ ሞገስ ወልደ ዮሃንስ፣ ዕታገኝ መልካ፣ ተስፋዬ ማሞ፣ መስፍን ጋሻው…
Rate this item
(0 votes)
በገጣሚ ኤፍሬም ስዩም የተዘጋጀውና ቮካል ሬከርድስ ያሳተመው የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም “ሙዚቃል” የግጥም ሲዲ በተለምዶ ቺቺንያ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው H2O ክለብ በመጪው ሃሙስ ምሽት ይመረቃል፡፡ ሙሉ የሙዚቃ ቡድን በመጠቀም በተዘጋጀው የሲዲ ግጥም ላይ ዶር. ሔራን ሠረቀብርሃን፣ አበጋዙ ክብረወርክ ሺዎታ፣ ሄኖክ ተመስገን፣…
Rate this item
(0 votes)
“ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይዘከራል” በሻሸመኔ ከተማ ኪነጥበብ አፍቃሪዎች የተቋቋመው “ከአድማስ ፊት” የኪነጥበብ ማህበር ነገ ከሰዓት በኋላ በሻሸመኔ ሁለገብ አዳራሽ የጥበብ ዝግጅቱን ያቀርባል፡፡ አርቲስት ጥላሁን ዘውገና አርቲስት አለልኝ መኳንንት የክብር እንግዶች ሲሆኑ ባለፈው ሳምንት ሕይወቱ ያለፈውና የዝግጅቱ የአንድ ወቅት…
Rate this item
(0 votes)
በሁለት ወጣት ባለሃብቶች ተቋቁሞ በቅርቡ ሥራ የጀመረው ሲኒማ ሴፍ ነገ እንደሚመረቅ ሲኒማ ቤቱ አስታወቀ፡፡ በፊንፊኔ ዙርያ ልዩ የኦሮሚያ ዞን ቡራዩ ከተማ ቡራዩ ማርያም ፍቅሩ ሕንፃ የሚገኘው ሲኒማ ቤት ሲመረቅ በወጣት ፊልም ሰሪዎች መካከል የአጫጭር ፊልሞች ውድድር ይካሄል፡፡
Rate this item
(0 votes)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስልክ ማውጫ በመጪው ማክሰኞ ምሽት በሸራተን ሆቴል እንደሚመረቅ አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ አኒፖል ሊሚትድ ኩባንያ (አፍሪካን ፎንቡክ) ያዘጋጀው ማውጫ በድረ ገፅ ብቻ በወር 20 ሚሊየን ጎብኚ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የተዘጋጀውን ማውጫ ድርጅቱ ያዘጋጀው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በገባው…