Saturday, 04 November 2023 00:00

ራሴ ነኝ ያበቀልኩት…

Written by  ዮሃንስ ሰ
Rate this item
(2 votes)

• የማንነት ኩራት በምን ምክንያት?
• ቲማቲምና ፀጉር በማብቀል?
• ድፎ ዳቦ በመጋገርና በብሔረሰብ ማንነት?

ድፎ ዳቦ ለእንግዶቿ እያቀረበች ነበር። ግብዣዋ በዝምታ አልታለፈም። “ምርጥ ዳቦ ነው” የሚል አድናቆትና ምስጋና ቀርቦላታል።
ዳቦው ከላይ አላረረም። ከውስጥ ደግሞበደንብ በስሏል። ያው ድፎ ዳቦ የሚያዘጋጁ ሙያተኞች ሁልጊዜ የሚገጥማቸው አንዱ ፈተና ይሄው አይደል? እንዳያርባቸው ሲጨነቁ፣ ውስጡ ሊጥ ይሆናል። ውስጡ እንዲበስል ምድጃ ውስጥ ካቆዩት ወይም እሳት ካበዙበት ደግሞ፣ ማረር ይኖራል።በዚያ ላይ፣ ዛሬ ዛሬ የድፎ ዳቦ ሊጥ ስኳርና ወተት ተጨምሮበት ነው የሚዘጋጀው። በትንሽ እሳት ያርባቸዋል። ሳያሳርሩ በደንብ ማብሰል መቻል፣ የጥሩ ባለሙያ ምልክት ነው። መቼም የዕድል ጉዳይ ሊሆን አይችልም።

ለዚያም ነው ከምስጋና በተጨማሪ አድናቆት አስፈላጊ የሚሆነው።“ልጄ ናት ያዘጋጀችውም፤ የጋገረችውም” አለች ጋባዣችንና አስተናጋጃችን። የ15 ዓመት ልጅ፣ ለዚያውም በአዲስ አበባ ዘመነኛ አኗኗር ውስጥ ያደገች፣ ውድ ትምህርት ቤት ውስጥ የምትማር፣ ድፎ ዳቦ አሳምራ ማዘጋጀትና መጋገር ከቻለች… ግሩም ነው። አድናቆት ይገባታል።ጋባዣችንም ይህን በመረዳት ነው፣ “ልጄ ናት ያዘጋጀችውም፣ የጋገረችውም” ብላ የነገረችን።

ተገቢው አድናቆት ለተገቢው ሰው እንድንገልጽ ነው ነው። ከዚህ ጎን ለጎን፣… “የኔ ልጅ አሪፍ ናት” የሚል ስሜትም ሊኖረው ይችላል።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ “እኔም አለሁበት፤ ሙያ አስተምሬያታለሁ፤ ሥራ ወዳድ እንድትሆን አርአያ ሆኛታለሁ” የሚል የአድናቆትና የኩራት ተጋሪ የመሆን መንፈስም አለው።እንግዲህ ነገሩን በትነንና አበጥረን እንየውና እንደገና ጠቅለል አድርገን እንግለጸው ከተባለ፣… ነገሩ ቀላል ይመስላል እንጂ፣ የብዙ ነገሮች ጥምረት ነው። ከምስጋና፣ ከአድናቆትና ከአክብሮት የተሰራ ጥልፍ ነው ማለት ይቻላል።መልካም ነገር ማየታችንንና መደሰታችንን የምንገልፅበት አጋጣሚ ይኖራል። ጥዋት 12 ሰዓት ገና ፀሓይዋ በግላጭ ሳትወጣ በፊት፣ እየመጣች መሆኗን ለማብሰር፣ ኃያልነቷን ከወዲሁ ለማሳየት ይመስላል… ዓለም ሁሉ እንዴት ወገግ እንደሚል አይታችኋል?በምስራቅ በኩል የሌሊቱ ጨለማ የፀሓይዋን ጉልበት ገና ከሩቁ ፈርቶ የሚሸሽ ይመስላል። ምድርና ሰማይ በወርቃማ ትኩስ አድማስ ይሳሳማሉ።

ይደምቃሉ። ድንቅ ነው።ይሄ የመደነቅ ጉዳይ ነው። ገና አድናቆት አልተጨመረበትም። ለአድናቆት ድንቅ ነገር ብቻ በቂ አይደለም።ድንቅ ነገር የሚሠራ አካል ሲኖር ነው፤ አድናቆት የሚኖረው። በሌላ አነጋገር፣ የሰው ሥራ ነው፣ የአድናቆት መነሻ። በሰውዬው አቅምና በሥራው ልክ ይደነቃል። እንደ ዕድሜው፣ እንደዘመኑ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ደረጃ፣ እንደሁኔታ አመቺነት፣ አገናዝበት፣ ስሌት ውስጥ አስገብተን፣ ሳናሳንስ ሳናጋንን ማድነቅ ይኖርብናል። ለምን?

ያው ለእውነታ ታማኝ የመሆን ጉዳይ ነው። አይተን እንዳላየን እንሁን ወይም ሽምጥጥ አድርገን እንካድ ካልተባለ በቀር፤ ወይም ያላየነውንና ያተሠራውን ነገር እንዳየንና እንደተሠራ አድርገን በውሸት እንመስከር ካልተባለ በቀር፣… ተገቢውን አድናቆት መስጠት የሥነ ምግባር ኃላፊነታችን ነው - ሳናጎድል ሳንጨማምር። ለእውነት መታመን የመጀመሪያው የሥነምግባር ኃላፊነት ነውና።ከኑሮና ከመንፈሳዊ የሰው ባሕርያት አንጻር እንዘርዝረው ከተባለስ? የሰውን ጥረትና ሥራ፣ እንደ ዓላማው መልካምነትና የልዕልና ደረጃው፣ እንደ ጥበቡና እንደ
ትጋቱ፣ እንደ ፋይዳውና እንደ ውጤቱ ልክ፣ ጠቃሚነቱንና ጉዳቱን የመገንዘብ፣ በዚያው መጠን ዋጋ የመስጠት የሐቅ ሚዛን ሊኖረን ይገባል።
የሠሪውን ብቃትና ልሕቀት አገናዝቦ መዳኘትና… በዚያው ልክ የሚመጥነው አድናቆትና ክብር መገለጽም፣ ትክክለኛ ዳኝነት የመስጠትና ፍትሐዊነትን የማሟላት

Read 739 times