Saturday, 19 August 2023 20:16

ከቡዳፔስት በፊት የኢትዮጵያ ውጤት በዓለም አትሌቲክስ የስታትስቲክስ ሰነድ

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(1 Vote)

95 ሜዳልያዎች (33 የወርቅ፣ 34 የብርና 28 የነሐስ)
• በወንዶች 45 ሜዳልያዎች (16 ወርቅ፣ 21 የብርና 11 የነሐስ)
• በሴቶች 47 ሜዳልያዎች (17 የወርቅ፣ 13 ብርና፣ 17 የነሐስ)



የዓለም አትሌቲክስ ማህበር ከዓለም ሻምፒዮናው በፊት በሚል WCH 23 BUDPEST STASTICAL BOOKLET ርእስ በ200 ገፅ ልዩ የስታትቲክስ መፅሃፍ በማዘጋጀት በልዮ እትም ያሰራጫል፡፡
በዚሁ የታሪክ ሰነድ ላይ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ውጤት ከሚጠቀሱ 10 የዓለም አገራት አንዷ መሆኗን መገንዘብ ይቻላል። ከቡዳፔስት በፊት ከተካሄዱት 18 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች በአስራ ሰባቱ የተሳተፈችው ኢትዮጵያ በድምሩ 95 ሜዳልያዎች (33 የወርቅ፤ 34 የብርና 28 የነሐስ) ሰብስባለች። በተጨማሪ 4ኛ ደረጃ 26 ጊዜ፤ 5ኛ ደረጃ 21 ጊዜ፤ 6ኛ ደረጃ  18 ጊዜ፤ 7ኛ ደረጃ 20 ጊዜ እንዲሁም 8ኛ ደረጃ 20 ጊዜ ያስመዘገበች ሲሆን ከሜዳሊያዎቹ ጋር በ998 ነጥብ ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ የያዘችበት ነው፡፡  
ከቡዳፔስት በፊት ኢትዮጵያ በወንዶች በድምሩ 48 ሜዳልያዎች (16 የወርቅ፤ 21 የብርና 11 የነሐስ) የሰበሰበች ሲሆን፤ 4ኛ ደረጃ  12 ጊዜ፤ 5ኛ ደረጃ 10 ጊዜ፤ 6ኛ ደረጃ  9 ጊዜ፤ 7ኛ ደረጃ 14 ጊዜ እንዲሁም 8ኛ ደረጃ 11 ጊዜ በማስመዝገብ በ507 ነጥብ ከዓለም ስምንተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡   በሴቶች ደግሞ በድምሩ 47 ሜዳልያዎች (17 የወርቅ፤ 13 የብርና 17 የነሐስ) የገኘ ሲሆን፤ 4ኛ ደረጃ 14 ጊዜ፤ 5ኛ ደረጃ 11 ጊዜ፤ 6ኛ ደረጃ  9 ጊዜ፤ 7ኛ ደረጃ  6 ጊዜ እንዲሁም 8ኛ ደረጃ 9 ጊዜ በመያዝ በ491 ነጥብ ከዓለም ስምንተኛ ደረጃ ላይ ናት፡፡  
በዓለም አትሌቲክ ማህበር የስታትቲክስ ሰነድ መሰረት በሻምፒዮናው ታሪክ የባለብዙ ሜዳልያዎች የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከዓለም ስምንተኛ ደረጃ በመያዝ የሚጠቀሰው 7 ሜዳልያዎች (4 የወርቅ 2 የብርና 1 የነሐስ) የተጎናጸፈው ኃይሌ ገብረስላሴ ነው፡፡ ቀነኒሳ በ6 ሜዳልያዎች (5 የወርቅና 1 የነሐስ) በማግኘት ከዓለም 11ኛ ደረጃ  ላይ ተቀምጧል። በሴቶች ምድብ ለኢትዮጵያ ትልቁን የሜዳልያ ስኬት ያስመዘገበችውና ከዓለም በ16ኛ ደረጃ የተቀመጠችው ደግሞ ጥሩነሽ ዲባባ  በ6 ሜዳልያዎች (5 የወርቅና 1 የብር ) ነው፡፡
ከዚህ በታች የቀረበው ከቡዳፔስት በፊት ባለፉት 18 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች በሁለቱም ፆታዎች ለኢትዮጵያ  95 ሜዳሊያዎችን የሰበሰቡ 50 አትሌቶች ዝርዝር ነው። (እንደ ኤሮፓ አቆጣጠር ነው)
በወንዶች
ኃይሌ ገብረስላሴ - በ5000m ብር 1993 ፤ በ10,000m 4 ወርቅ  1993,1995,1997 እና 1999 ነሐስ 2001 ብር 2003
ቀነኒሳ በቀለ - በ5000m ነሐስ 2003 ወርቅ 2009፤ በ10,000m 4 ወርቅ 2003,2005, 2007 እና 2009
ሙክታር ኢድሪስ- በ5000m 2 ወርቅ 2017 እና 2019
ታምራት ቶላ - በማራቶን ብር 2017 ወርቅ 2022
ሌሊሳ ዴሲሳ - በማራቶን ብር 2013 ወርቅ  2019
ኢብራሂም ጀይለን - በ10,000m ወርቅ 2011 ብር 2013
ገዛኸኝ አበራ - በማራቶን ወርቅ 2001
መሐመድ አማን በ800m ወርቅ 2013
ስለሺ ስህን - በ5000m ብር 2005 ፤በ10,000m ነሐስ 2003 2 ብር 2005 እና 2007
ሞስነት ገረመው - በማራቶን 2 ብር   በ2019 እና  2022
ለሜቻ ግርማ - በ3000m መሠናክል 2 ብር 2019 እና 2022
የማነ ፀጋዬ - በማራቶን ብር  2015
አሰፋ መዝገቡ - በ10,000m ነሐስ 1999 ብር 2001
ፊጣ ባይሳ - በ5000m ብር 1991 ነሐስ 1993
ሐጎስ ገብረሕይወት - በ5000m ብር 2013 ነሐስ 2015
ከበደ ባልቻ - በማራቶን ብር 1983
ደረሰ መኮንን - በ1500m ብር 2009
ሰለሞን ባረጋ - በ5000m ብር 2019
ዮሚፍ ቀጀልቻ - በ10,000m ብር 2019
ሚሊዮን ወልዴ - በ5000m ብር 2001
ፀጋዬ ከበደ - በማራቶን ነሐስ 2009
ፈይሳ ሌሊሳ - በማራቶን ነሐስ 2011
ታደሰ ቶላ - በማራቶን ነሐስ 2013
ኢማና መርጋ - በ10,000m ነሐስ 2011
ደጀን ገብረመስቀል - በ5000m ነሐስ 2011
***
በሴቶች
ጥሩነሽ ዳባባ - በ5000m 2 ወርቅ 2003 እና 2005፤ በ10,000m 3 ወርቅ 2005,2007 እና 2013 ብር 2017
መሠረት ደፋር - በ5000m ብር 2005 2 ወርቅ 2007, 2013 2 ነሐስ 2009 እና 2011
አልማዝ አያና - በ5000m ነሐስ 2013 ወርቅ 2015 ብር 2017፤ በ10,000m ወርቅ 2017
ብርሐኔ አደሬ - በ10,000m 2 ብር 2001 2005፤ ወርቅ  2003
ጉዳፍ ፀጋይ - በ1500m ነሐስ 2019 ብር 2022 ፤በ5000m ወርቅ 2022
ደራርቱ ቱሉ - በ10,000m ብር 1995 ወርቅ 2001
ለተሰንበት ግደይ - በ10,000m ብር 2019 ወርቅ 2022
ጌጤ ዋሚ - በ10,000m ወርቅ 1999 ነሐስ 2001
ገንዘቤ ዲባባ - በ1500m ወርቅ 2015 ፤ በ5000m ነሐስ 2015
ማሬ ዲባባ - በማራቶን ወርቅ 2015
ጓይተቶም ገብረስላሴ - በማራቶን ወርቅ 2022
ወርቅውሐ ጌታቸው - በ3000m መሠናክል ብር  2022
ወርቅነሽ ኪዳኔ - በ10,000m ብር 2003
መሠለች መልካሙ - በ10,000m ብር 2009
ገለቴ ቡርቃ - በ10,000m ብር 2015
ሰንበሬ ተፈሪ - በ5000m ብር 2015
እጅጋየሁ ዲባባ - በ5000m ነሐስ 2005፤ በ10,000m ነሐስ 2005
አየለች ወርቁ - በ5000m 2 ነሐስ 1999 እና 2001
አሰለፈች መርጊያ - በማራቶን ነሐስ 2009
በላይነሽ ኦልጂራ - በ10,000m ነሐስ 2013
ውዴ አያሌው - በ10,000m ነሐስ 2009
ዳዊት ስዮም - በ5000m ነሐስ 2022
መቅደስ አበበ - በ3000m መሠናክል ነሐስ 2022
ሶፍያ አሰፋ- በ3000m መሠናክል ነሐስ  2013
ቁጥሬ ዱለቻ - በ1500m ነሐስ 1999







Read 487 times