Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 November 2011 08:50

“የኛው ሰው በሶማሊያ እስር ቤት”

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ብዙ ሳልርቅ አንባቢ አንድ ነገር እንዲረዳ እፈልጋለሁ፡፡ ይህም… እስረኛውን ለመቅጣት ሁል ጊዜ ሰበብና ምክንያት አስፈላጊ አለመሆኑና እስረኛውም ቅጣቱ አይገባኝም ወይም ይቅለልልኝ ማለት አለመቻሉ ነው፡፡ (ለምሳሌ “በፊት ገጽታህ መንግሥቱ ኃ/ማርያምን ትመስላለህ” ብለው የያዙትን ዱላ በላዩ ላይ አነካክተው ሲጨርሱ፤ የተውት እስረኛ “እምይ የአራዳ ልጅ” አለ፡፡ በተመሳሳይ እንደገና “የመንግሥቱን አባት ኃ/ማርያምን አገኘነው” ብለውም አንዱን የህክምና ባለሙያ እስከሚበቃቸው ወግረውታል፡፡

በእልህና በእምቢተኝነት ሊያደርግ የሚችለውም ነገር የለም፡፡ የ”መብት” ጥያቄ ሆኖ ሳይሆን ጦሱን በማሰብና በመፍራት አንድ የሱን ሕይወት ብቻ ሳይሆን በጅምላ ከፍተኛ መዘዝ የሚያስከትል ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ባይሆንማ አንድ ለአንድ ማንም ለማንም አይሰንፍም ነበር፡፡ ለመኮንኖች ምግብ አብስሎ የሚያቀርብ እስረኛው ነው፡፡ ተንኮል ቢያስብ አንፈራግፍሮ ሊረፈርፍቸው በቻለ፡፡ ፀጉራቸውን የሚያስተካክል፣ ፂማቸውን የሚላጭ፣ መቀስና ቢላዋ (ምላጭ) የያዘ እስረኛ ነው፡፡ ብቻ ግዑዝ ሆኗል - እነሱም በግዑዝነቱ ንቀውታል፡፡ እንጂማ አንድ ጥሬ፣ ጭባና ገገማ ባላገር አደግ መደዴ የሶማሌ ምልምል ከፍተኛ ስልጠናና የረጅም ጊዜ ትምህርት ያለውን አንድ ኩሩ ባለኮከብ የሀበሻ መኮንንንን እንደ ልጅ ሊገርፈው ባልቻለ ነበር፡፡ አስተኝቶም ባልረገጠው፣ ምንም ያላደረጉት የቀራቸው ነገር የለም፡፡ ምናልባት እዘለንና በአምብርክክህ እሩጥ አላሉት ይሆናል፡፡
ሁልጊዜ እስረኛ መሆኑን እንዲያስብ ሆን ተብለው የሚደረጉ ቅጣቶች አሉ፡፡ እንዲያው ደርሶ ምንም በማይገናኝ ነገር “አንተኮ የመጣኸው ከጠላት አገር ነው፤ ለመሆኑ ስንት ሶማሌ ገድለሃል ሶማሌዎችን ስትረግጥና ስትጨቁን የኖርክ ሆዳም ነህ…” ወዘተ ሊባል ይችላል፡፡ ይህ ሰው ግን እንኳን ሰውን ኦጋዴንን ጨርሶ ረግጦ የማያውቅ ይሆናል፡፡
በተለይ ቋንቋቸውን የሚያውቅ ከሆነ የተለያየ ስም ይሰጠዋል፡፡ “ሰላይ ነበርክ” በፍፁም አይቀርለትም (ሁሉም እንደነሱ የሚያደርግ ነው የሚመስላቸው፡፡ የሌባ እናት ልጇን አታምንም አይነት) “እኛ እዚህ እንቀልባችኋለን” የናንተ መንግሥት የማረካቸውን በሙሉ ረሽኗል፡፡ ለሰላምና ዕርቅ ድርድር አልተመቸም፡፡ ደግሞ ምርኮኛ የለኝም ብሏል፡፡ እንደፈለግን ልናደርጋችሁ እንችላለን፡፡ ስለሆነም እዚሁ ነው የምናስቀራችሁ፡፡ መንደር መሰርተን እርስ በርስ ተጋብታችሁ ትኖራላችሁ፣ ሃይማኖት ይኖራችኋል (በነገራችን ላይ ሙስሊም ያልሆነ ሁሉ በነሱ አህዛብ “ጋል” ነው) ሶማሊያ የጥጋብ አገር ናት፡፡ ሩዝ (በሪስ) ትበላላችሁ፣ ጦርነቱ ደግሞ ቀጣይ ነው፡፡ መንግስታችሁ ጊዜያዊ ድል አግኝቷል፡፡ ኃይለማሪያምም ወንድ ነው (የቀድሞው የአገሪቷ መሪ) ለኛ መሸነፍ ምክንያት የሆኑት ግን እነዚያ ነጫጩባዎች ናቸው፡፡ (ሩሲያውያን ኪዩባውያን የመናውያን) ጊዜና ሁኔታ ጠብቀን እንነሳለን፡፡ ይህ አይቀርም እንዲያውም እናንተ በደህና ጊዜ እጃችን ገብታችኋል፡፡ እዚያ መሬት ለቀሩት ወዮላቸው፣ ሀገራችሁ ተበጣጥቃ ትቀራለች፡፡ አትጠራጠሩ ትበታተናለች፤ ይኸው እየተሰነጣጠቀች አይደል፡፡
(“የኛው ሰው በሶማሊያ እስር ቤት”
ከሚለው የጥላሁን አትሬሶ መጽሐፍ የተቀነጨበ)

=====================================
ለ”ወዳጄ”
በሄዋን ጉትጎታ፣ በለሷን ሲበላ
አዳም ቃሉን ሳተ፣ ካምላኩ ተጣላ፡፡
ወዳጅ ተብዬዋ፣ እመቤት ደሊላ
አስቀፈደደችው፣ ሶምሶምን በመላ፡፡
በመጠርጠር ነዶ፣ በቅናት ተቃጥሎ
ለውድቀት ሲዳረግ፣ ሲሳሳት ኦቴሎ
ወዳጅ የተባለው፣ ኢያጎ ነበረ
ስንት ጉድ ያፈላው፣ እሣት እየጫረ፡፡
እያልኩኝ ስከትብ፣ ለመግለፅ ስሞክር
የወዳጅን መዘዝ፣ የወዳጅን ጣጣ
ያቋርጠኝ ጀመር
የወዳጄ ምሥል፣ በሐሳቤ እየመጣ፡፡
ዳዊት ፀሐይ


=============================================



ወንድምህን ታደከው
ጽፈኸው . . . ገልፀኸው
አልኸው . . . አልከውና፤
ለፍቅር፣ ለህብር፣ ለክብር ሮጥክና
በሕይወትህ ጐዳና . . .
ድንገት ሲጋፈጥህ የመኖር የመሞት የወገን ፈተና፤
ጭንቀቱ እንቅልፍ ነስቶህ ጣሩ ታየህና፤
ቃልህን ጠበቅከው ቃል ዕዳ ነውና፤
እንደ ዳንኤል አምላክ ፈጥነህ ደረስክና፡፡
ያሉት ከሚጠፋ ብለህ እንዳወጅከው
ፍቅርን አዚመህ በተግባር ገለጥከው፤
ካላሰበው ሞት ወንድምክን ታደከው
ለቴዲ አፍሮ - በጐነት የተገጠመ
ጋሩማ ሁንዴ - ከሳሪስ

 

Read 4724 times Last modified on Saturday, 12 November 2011 09:00