Saturday, 05 October 2013 11:00

በመሰረታዊ የባሕል ውዝዋዜ የሠለጠኑ ነገ ይመረቃሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ከተለያዩ የሐገሪቱ ክፍሎች አሰባስቦ ለሁለት ወራት በመሠረታዊ የብሔረሰቦች የባሕል ውዝዋዜ ያሠለጠናቸውን ተወዛዋዦች፤ ነገ ከጧቱ 3 ሰዓት እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ ትያትር ቤቱ ሥልጠናውን አስመልክቶ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ፤ “በባሕል ውዝዋዜ ላይ ያለውን ሂስ በመሠረታዊ ደረጃ ቀስ በቀስ በትክክለኛ ገጽታው እንዲያንፀባርቁና ኢትዮጵያን በጥሩ ጎን እንዲያስጠሩ የታለመ ነው” ብሏል፡፡
ሰልጣኞቹ በዘንድሮ ስድስተኛው የሰንደቅ አላማ ቀን፣ ሙዚቃዊ ድራማ ያቀረቡ ሲሆን በአርቲስት ጌትነት እንየው ተደርሶ በተዘጋጀው የእንቁጣጣሽ “አዲስ ፀሐይ በኢትዮጵያ ሰማይ” ሙዚቃዊ ዳንስ ድራማም ተሳትፈዋል፡፡

Read 920 times