Saturday, 05 October 2013 11:01

የፑቲን ልደት በፎቶ ዓውደርዕይ ይከበራል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ልደት የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ በሚከፈት የፎቶ ዓውደርእይ እንደሚከበር የሩስያ ሳይንስና ባሕል ማእከል አስታወቀ፡፡ በእለቱ ከሰዓት በኋላ በ10፡30 በሚከፈተው አውደርእይ “ፕሬዚዳንታችን ፑቲን” በሚል ርእስ የፕሬዚዳንቱ የተለያዩ ፎቶግራፎች ለእይታ የሚቀርቡ ሲሆን፤ አውደርእዩ ጧት ከ3-6 ሰዓት፣ ከቀትር በኋላ ከ7-11 ሰዓት እየታየ እስከ ሕዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
በዚሁ ዕለት ከቀኑ 11፡30 የሩስያዊ ደራሲ ሚካኤል ሌርሞንቶቭ መታሰቢያ ዝግጅት እንደሚቀርብ ማዕከሉ አስታውቋል፡፡ ሌርሞንቾቭ እንደ ፑሽኪን ያለ ታላቅ ገጣሚ እንደነበር የጠቆመው ማእከሉ፣ በሩስያ ሮማንቲሲዝም ትልቅ ቦታ እንዳለው አመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል ማእከሉ የዓለም መምሕራን ቀንን አስመልክቶ ዛሬ ልዩ ዝግጅት የሚያቀርብ ሲሆን፤ ዝግጅቱ በሩስያ ፊልም እና ሙዚቃዎች እንደሚታጀብ ታውቋል፡፡

Read 950 times