Saturday, 02 November 2013 12:07

“የኢብሮ-አሜሪካ” ፊልም ፌስቲቫል ተጀመረ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

ከአውሮፓ የስፔን እና የፖርቱጋል፣ ከአሜሪካ ደግሞ የብራዚል፣ ኩባ፣ ቬኔዚዋላ፣ ሜክሲኮ እና አርጀንቲና ፊልሞች የሚታዩበት ስምንተኛው “የኢብሮ-አሜሪካ” ፊልም ፌስቲቫል ከትናንት በስቲያ ምሽት በጣልያን የባህል ተቋም ተጀመረ። ሐሙስ ምሽት፣ “ኤርማኖ” የተሰኘው የቬኔዙዋላ ፊልም ሲታይ፤ ትናንት “ኖሶድሮስ ሎስ ኖብልስ” የተሰኘው የሜክሲኮ ፊልም ታይቷል፡፡ “ፋዶስ” የተሰኘው የፖርቱጋል፣ “ፓርታ ደ ሄሬዶ1 የአርጀንቲና፣ “ሊን ሃ ደ ፓሴ” የብራዚል፣ “ሎስ ዲዮሰስ ሮቶስ” የኩባ እና “ኖ ሬሰት ፎር ዘ ዊክት” የስፔን ፊልሞች እንደየቅደም ተከተላቸው በእንግሊዝኛ መግለጫ ታጅበው ከዛሬ እስከ ረቡዕ በነፃ ይቀርባሉ፡፡

Read 1186 times