Saturday, 02 November 2013 12:12

“የኢትዮጵያ ኮከብ” እና “አፄ ምኒልክና የአድዋ ድል” ለንባብ በቁ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(1 Vote)

በአብነት ስሜ የተዘጋጀው “የኢትዮጵያ ኮከብ” የሥነ ከዋክብት መፅሐፍ ለንባብ በቃ። የአስትሮሎጂ መፅሐፉ በፋርኢስት ትሬዲንግ የታተመ ሲሆን በውስጡ የ500 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ታዋቂ ሰዎች “ኮከብ” ይዟል። ለማዘጋጀት ሰባት ዓመት የፈጀው መፅሐፍ፤ አምስት ክፍሎቹና አስራ ሰባት ምዕራፎች አሉት። ባለ 132 ገፁ መፅሐፍ፤ በ50 ብር ከ65 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
በሌላም በኩል “አፄ ምኒሊክ እና የአድዋ ድል” የሚል የታሪክ መፅሐፍ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ። “AFRICAN VICTORY IN THE AGE OF EMPIRE” የተሰኘውን የራይሞንድ ዮናስ መፅሐፍ የተረጐሙት ሙሉቀን ታሪኩ ናቸው፡፡ በኤችዋይ ኢንተርናሽናል ማተማያ ድርጅት የታተመው መፅሐፍ፤ በአፄ ቴዎድሮስ ላይ ከተደረገ ዘመቻ እስከ ሩሰያዊው የአፄ ምኒልክ አማካሪ ኒኮላይ ሊዎንታፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በጣሊያን እና ሌሎች ቁምነገሮችንም ይዟል፡፡ 263 ገፅ ያለው መፅሐፉ፤ በ70 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

Read 1541 times