Saturday, 09 November 2013 12:23

“ማሕበር ምውታን” የትግርኛ ልቦለድ ታተመ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

በደራሲና ጋዜጠኛ አዲስዓለም ሐጐስ የተደረሱ አስራ ሁለት አጫጭር ልቦለዶች የተካተቱበት “ማሕበር ምውታን” የትግርኛ ልቦለድ መፅሐፍ ታተመ። ነገ በመቀሌ ከተማ ለንባብ የሚበቃው መፅሐፍ፤ 110 ገፆች ያሉት ሲሆን በ40 ብር ለገበያ እንደቀረበ ታውቋል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ያሳተሟቸው “ወይዘሪት ኢትዮጵያ 2020” እና “ምወዳዕታ መአልቲ” የተሰኙ መፃህፍት ላይ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ሥነፅሁፍ ምሁራን የሚመራ ውይይት በመቀሌ ከተማ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

Read 1148 times