Saturday, 09 November 2013 12:26

“ገዳይ ሲያረፋፍድ” ፊልም ሰኞ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(2 votes)

በስለሹ አምባው ተደርሶ በናኦድ ለማ የተዘጋጀው “ገዳይ ሲያረፋፍድ” ፊልም ሰኞ በብሄራዊ ቴአትር በ11፡00 ሰዓት ይመረቃል፡፡ ፊልሙ ሙሉ በሙሉ የተቀረፀው ቆራጣ በተሰኘው የደቡብ ጐንደር የገጠር ቀበሌ ሲሆን በአንድ ሽፍታና በአንድ አባወራ መካከል ያለን የህይወት ትግል እንደሚያሳይ የፊልሙ ፕሮዲዩሰር የ“ጣና ኢንተርቴይንመንት” ባለቤት አቶ ጋሻው ሞላ ተናግረዋል። ፊልሙ በአካባቢው ያለውን የባህል ትውፊት እንደሚያሳይና የዘጠና ደቂቃ ርዝመት እንዳለው ተገልጿል፡፡ ነገ በሁሉም የአዲስ አበባ የግል ሲኒማ ቤቶች የሚታይ ሲሆን የዛሬ ሳምንት በባህርዳር ሙሉአለም አዳራሽ እንዲሁም ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም በሁሉም የመንግሥት ሲኒማ ቤቶች እንደሚታይ ታውቋል፡፡ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ አንድ አመት ከስድስት ወር የፈጀው ፊልሙ፤ በአካባቢው ልጆች የተሰራ እንደሆነ ፕሮዱዩሰሩ ተናግረዋል፡፡

Read 1277 times