Saturday, 09 November 2013 12:27

የሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ “ንግሥ” ሐሙስ ይከፈታል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(1 Vote)

የታዋቂው ሰዓሊ መዝገቡ ተሰማ “ንግሥ” የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን የፊታችን ሐሙስ ከምሽቱ 12 ሰዓት አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም እንደሚከፈት ተገለፀ፡፡ ኤግዚቢሽኑ እስከ ህዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ከአዲስ አበባ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት በስዕል ትምህርት ዲፕሎማውን ያገኘው ሰዓሊው፤ በቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት (ሩሲያ) 300 ዓመት ገደማ ባስቆጠረው የሥዕል አካዳሚ ገብቶ የማስተርስ ዲግሪውን ተቀብሏል። ሰዓሊው ከዚህ ቀደም በግልና በቡድን በአገር ውስጥና በውጭ አገራት በርካታ ኤግዚቢሽኖችን ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ጀርመንና ሌሎች አገራት ይገኙበታል፡፡ በእውነታዊነት (Realistic) የአሳሳል ዘይቤው የሚታወቀው ሰዓሊ መዝገቡ በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነጥበብ ት/ቤት በመምህርነት እያገለገለ ይገኛል፡፡

Read 1928 times