Monday, 25 November 2013 11:14

የነጭ ሪቫን ቀን በኪነጥበብ ይዘከራል

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(1 Vote)

የነጭ ሪቫን ቀንን በተለያዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እንደሚያከብር የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅት የሚፈፀሙ የተለያዩ የጾታ ጥቃቶችን ለማስቆም ቃል የሚገባበት ቀን የሚዘከረው በአዲስ አበባ ራስ ሆቴል ትልቁ አዳራሽ፣ የፊታችን ሰኞ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ሲሆን ፕሮግራሙ ወንድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በሚያቀርቧቸው የግጥም፣ የጭውውት፣ የመነባንብና የዘፈን ዝግጅቶች እንደሚከፈት ታውቋል፡፡ ማህበሩ የነጭ ሪቫንን ቀን ሁለቱንም ጾታዎች በማሳተፍ ሲያከብር የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

Read 3742 times