Saturday, 28 December 2013 10:22

የኮካ ኮላ ሁለተኛ ዙር “የተሰጥኦ ውድድር” ተጀመረ

Written by  መልካሙ ተክሌ
Rate this item
(0 votes)

የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት የተዘጋጀለት የኮካ ኮላ ሱፐር ስታርስ ሁለተኛ ዙር “የተሰጥኦ ውድድር” መጀመሩ ተገለፀ፡፡ የኮካ ኮላ ብራንድ ማኔጀር አቶ ምስክር ሙሉጌታ ባለፈው ሐሙስ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ እንደተናገሩት፤ ውድድሩ ከ13-29 አመት እድሜ ያላቸውን የሚያሳትፍ ሲሆን አዲስ አበባን ጨምሮ በዘጠኝ የአገሪቱ ከተሞች ያሉ ባለ ተሰጥኦዎች ይወዳደሩበታል፡፡ “ተተኪን ፍለጋ” በሚል መርህ የሚካሄደው የኮካ ኮላ ሱፐር ስታርስ የተሰጥኦ ውድድር፣ በድምፅና በቡድን ውዝዋዜ ዘርፍ የሚካሄድ ሲሆን ለአሸናፊዎቹ የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት ያከፋፍላል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የተሰጥኦ ውድድር ከአይጃ ኢንተርቴይመንት ጋር በኦሮሚያ ቴሌቪዥንና በኢቢኤስ ለ10 ወራት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ለአምስት ወራት እንደሚዘልቅ ተገልጿል፡፡

Read 1391 times