Saturday, 28 June 2014 10:45

20ኛው የዓለም ዋንጫ በጥሎ ማለፍ ይቀጥላል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(3 votes)

20ኛው ዓለም ዋንጫ ዛሬ  በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ ባለፉት 15 ቀናት በስምንቱ ምድቦች በተደረጉ 48

ጨዋታዎች ጎሎች 136 ጎሎች ከመረብ ያረፉ ሲሆን በየጨዋታው በአማካይ 2.83 ጎሎች ተመዝግበዋል፡፡ የኮከብ ግብ

አግቢነቱን ፉክክር በ4 ጎሎች 3 ተጨዋቾች የተያያዙበት ሲሆን  የብራዚሉ ኔይማር ፤ የአርጀንቲናው ሊዮኔል ሜሲና

የጀርመኑ ቶማስ ሙለር ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸው 3 ጎል በማስመዝገብ ፉክከሩን የሚከተሉ 6 ተጨዋቾች ደግሞ  

የኮሎምቢያው ጀምስ ሮድሪጌዝ፣ የኢኳደሩ ኢነር ቫሌንሽያ፣ የፈረንሳዩ ካሬም ቤንዜማ፣ የሆላንዶቹ ቫንፕርሲና ሮበን

እንዲሁም የስውዘርላንዱ ዤርዳን ሻኪሪ ናቸው፡፡በጥሎ ማለፉ ድልድል መሰረት ዛሬ  ብራዚል ከቺሊና ኮሎምቢያ

ከኡራጋይ ፤ ነገ ሆላንድ ከሜክሲኮ እና ኮስታሪካ ከግሪክ፤ ሰኞ ፈረንሳይ ከናይጄርያና  ጀርመን ከአልጄርያ  እንዲሁም

ማክሰኞ አርጀንቲና ከስዊዘርላንድና ቤልጅዬም ከአሜሪካ ይገናኛሉ፡፡
የዓለም ዋንጫው ሩብ ፍፃሜ የዛሬ ሳምንት ሲቀጥል ከፈረንሳይና ናይጄርያ የሚያሸንፈው ከጀርመንና አልጄርያ አሸናፊ

ጋር፤ ከብራዚልና ቺሊ የሚያሸንፈው ከኮሎምቢያ እና ኡራጋይ አሸናፊ ጋር፤ ከአርጀንቲናና ስዊዘርላንድ የሚያሸንፈው

ከአሜሪካና ቤልጅዬም አሸናፊ ጋር እንዲሁም ከሆላንድና ሜክሲኮ የሚያሸንፈው ከኮስታሪካ እና ግሪክ አሸናፊ ጋር

ተገናኝተው ወደ ግማሽ ፍፃሜ የሚያልፉት አራት ቡድኖች  ይታወቃሉ፡፡የምድብ ማጣርያው ተጠናቅቆ ወደ ጥሎ ማለፉ

ምዕራፍ ያለፉት 16ቱ ብሄራዊ ቡድኖች ከታወቁ በኋላ ከመካከላቸው ዓለም ዋንጫውን የማሸነፍ እድል ያላቸው 7

ቡድኖች እንደሆኑ  እየተገለፀ ነው፡፡ የተለያዩ ትንበያዎችና ግምቶች በማገናዘብ ለመረዳት እንደሚቻለው  ዓለም

ዋንጫውን ለማሸነፍ ብራዚል 36 በመቶ፤ አርጀንቲና 25 በመቶ፤ ጀርመን 15 በመቶ፤ ቺሊ 7 በመቶ፤ ሆላንድ 6 በመቶ፤

ኮሎምቢያ 5 በመቶ እንዲሁም ፈረንሳይ 5 በመቶ እድል አላቸው፡፡ በዓለም ዋንጫው ተከፋይ ከሆኑት 5 የፊፋ

ኮንፌደሬሽኖች በምድብ ጨዋታዎች ከብዛታቸው አንፃር ከፍተኛ ነጥብ በመሰብሰብ የሰሜንና መካከለኛው አሜሪካ

ቡድኖች 75 በመቶ ውጤታማ ነበሩ፡፡ ደቡብ አሜሪካን የወከሉ ቡድኖች 66.7 በመቶ ውጤታማነት ሲመዘገብላቸው

በምድብ ማጣርያው በየጨዋታው በአማካይ 2.33 ነጥብ ነበራቸው፡፡ የአውሮፓ ቡድኖች 30 በመቶ፤ የአፍሪካ ቡድኖች

26.7 በመቶ እንዲሁም የኤስያ ቡድኖች 16.7 በመቶ ውጤታማነት አሳይተዋል፡፡


ብራዚል ከቺሊ
በታሪካቸው በሁሉም ውድድሮች 70 ጨዋታዎችን አድርገዋል፡፡ ብራዚል 50 ስታሸንፍ ቺሊ 7 ጊዜ አሸንፋ በ13

ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል፡፡
ሴልሳኮ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ‹‹ሁላችሁም ተዘጋጁ፤ 6ኛው እየመጣ ነው›› የሚል

መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 467 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
ላሮጃ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የቺሊ ብሄራዊ ቡድን ‹‹ቺ ቺ ቺ፤ ሌ ሌ ሌ፤ ጎ ቺሊ›› የሚል መፈክር አለው፡፡

የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 143 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡


አርጀንቲና ከስዊዘርላንድ
በሁሉም ውድድሮች ስድስት ጨዋታዎች አድርገዋል። አርጀንቲና 4 ስታሸንፍ በቀሩት ሁለት ጨዋታዎች አቻ

ተለያይተዋል፡፡
አልባይሴላስቴ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ‹‹ቡድን ብቻ አይደለንም ፤እኛ አገር ነን››

የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 423.5 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
ዘስዊዘር ናቲ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የስዊዘርላንድ ብሄራዊ ቡድን ‹‹መጨረሻቻን የፍፃሜው ቀን ማራካኛ ላይ››

የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 171 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡


በምድብ 2 ኡራጋይ 1ለ0 በሆነ ውጤት ጣሊያን ባሸነፈችበት ጨዋታ በ80ኛው ደቂቃ  የጣሊያኑን ተከላካይ ጂዮርጂዮ

ቼሊኒ ትክሻ የነከሰው ሉዊስ ስዋሬዝ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር በተላለፈበት ቅጣት ከማንኛውም የእግር ኳስ

እንቅስቃሴ ለ4 ወራት ታገደ፡፡  በቅጣቱ መሰረት ስዋሬዝ  ከዓለም ዋንጫው እንዲባረር ከመወሰኑም በላይ  ለክለቡ

ሊቨርፑል በ13 ጨዋታዎች፤ ለብሄራዊ ቡድኑ 9 ጨዋታዎች አይሰለፍም፡፡ በተጨማሪም 65ሺ ፓውንድ የገንዘብ መቀጮ

ተጥሎበታል፡፡ የኡራጋይ እግር ኳስ ፌደሬሽን  በፊፋ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ እስከመጭው ሰኞ  እድል አለው፡፡

የ27 ዓመቱ ሊውስ ስዋሬዝ ከፊፋ የቅጣት ውሳኔ በኋላ ብራዚልን በመልቀቅ በቀጥታ ወደ ኡራጋይ ዋና ከተማ

ሞንትቪድዮ እንደተመለሰ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ስዋሬዝ ከንክሻው በኋላ ከስፖንሰሮቹ የሚያገኘው ገቢ ሊቀንስበት እና ከፍተኛ ኪሣራ ሊገጥመው  

ይችላል፡፡ የትጥቅ አምራቹ ኩባንያ አዲዳስ ከፊፋ ውሳኔ በኋላ ከተጨዋቹ ጋር ያለውን የውል ስምምነት ለማጤን

አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል፡፡ አዲዳስ ለስዋሬዝ በዓመት እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር ይከፍለው ነበር፡፡ ቦከር ብራንድ 888

የተባለ አቋማሪ ድርጅት ተጨዋቹን ባለፈው ወር አምባሳደር በማድረግ ቢሾመውም ከንክሻው በኋላ ይህን ሹመቱን

ለመሰረዝ ይወስናል ተብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ከተጨዋቹ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ

ደረጃ ክብሩ እየተበላሸ ቢሆንም የመሸጥ ፍላጐት እያሳየ አይደለም፡፡ ይሁንና በርካታ የእንግሊዝ ክለቦችና ሁለቱ የስፔን

ክለቦች ሪያልማድሪድና ባርሴሎና ተጨዋቹ ለመግዛት የዓለም ዋንጫውን መገባደድ ሲጠባበቁ ነበር፡፡ ኮንክሻው በኋላ

ግን ይህ ፍላጐት ቀንሷል። ሊቨርፑል ተጨዋቹን ለመሸጥ እስከ 100ሚሊዮን ዶላር እንደሚጠይቅ አንዳንድ ዘገባዎች

ቢያመለክቱም የዝውውሩ ሂሳብ በግማሽ ሊቀንስ እንደሚችል መረጃዎች አውስተዋል፡፡
ስዋሬዝን በኡራጋይ ‘˜el lunático que muerde todo’ብለው የሚጠሩት ሲሆን ትርጉሙም ሁሌ ተናካሹ ቀዌ

እንደማለት ነው፡፡ የኡራጋይ ፕሬዝዳንት ጆሴ ሙጂካ ለአገሬው ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት እርግጫ እና የጉልበት

ጨዋታ በበዛበት ግጥሚያ  አንድ ንክሻ መጋነኑ ተገቢ አይደለም ብለዋል።



ሆላንድ ከሜክሲኮ
በታሪካቸው 6 ጨዋታ አድርገዋል፡፡ ሆላንድ 2 ስታሸንፍ ሜክሲኮ 3 አሸንፋ በአንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ብርቱካናማዎቹ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የሆላንድ ብሄራዊ ቡድን ‹‹እውነተኛ ወንዶች ብርቱካናማ ይለብሳሉ››

የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት   97.5 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
ኤል ትራይ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የሜክሲኮ ብሄራዊ ቡድን  ‹‹ሁሌም በህብረት ሁሌም አዝቴካዎች›› የሚል

መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት  39.3 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡


በመኪኖች ሰብሳቢነት ኤቶን የሚስተካከል የለም ፤ ውዷ መኪና ግን የክርስትያኖ ሮናልዶ ናት
ተጨዋቾች ላምበርጊኒ፤ ፖርሽ፤ ፌራሪ ይነዳሉ
ምርጥ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ከሚኖራቸው ከፍተኛ ገቢ በወጭ ደረጃ ብዙ የሚያፈሱት ለመኪኖቻቸው ነው፡፡ በዓለም

ዋንጫው የተሳተፉት ተጨዋቾች የመኪና ምርጫዎቻቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ ሁሉም ግን በዋጋቸው ውድነት እና

በወቅታዊ ምርት ግዢያቸው ይመሳሰላሉ፡፡ በእግር ኳስ ተጨዋችነት እስከ 95 ሚሊዮን ዶላር ሃብት ማፍራቱ

የሚነገርለት ካሜሮናዊው ሳሙኤል ኤቶ እስከ 5 ሚሊዮን ዩሮ በማውጣት ውድ መኪኖች አሰባስቧል፡፡
ከስብስቦቹ መካከል  ሁለት የአሽተን ማርቲን፤ ቡጋቲ ቫይሮንና ሜይባች የተባሉት የመኪና ምርቶች ይገኙበታል፡፡

ክርስትያኖ ሮናልዶ ደግሞ ባለው የሚኖች ስብስብ ብዛት እና ውዷን መኪና በመንዳት ቀዳሚ ነው፡፡ ሮናልዶ

በማንችስተር ዩናይትድ መጫወት ከጀመረ እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር ወጭ አድርጎ 19 መኪኖችን አሰባስቧል፡፡ ከመኪኖቹ

መካከል ቢኤም ደብሊው፤ መርሴዲስ ቤንዝ፤ ቤንትሌይ፤ ፖርሽ፤ ፌራሪ፤ አውዲ እና ሮልስ ሮይስ ፤ አሽተን ማሪን እና

ላምበርጊኒ ብራንዶች ሲገኙበት በዋጋዋ ውድነት ከእግር ኳስ ተጨዋቾች አንደኛ ደረጃ የሚሰጣት መኪናው 1.7 ሚሊዮን

ዶላር የገዛት ቡጋቲ ቬዬሮን ናት፡፡ ብዙዎቹ ተጨዋቾች ከሁለት በላይ መኪኖችን በንብረትነት የያዙ ሲሆን ባላቶሊ ባለ

318ሺ ዶላር ፌራሪ ኤፍ12፤ ሩኒ ባለ 280ሺ ዶላር አሽተን ማርቲን፤ ኔይማር ባለ2 50ሺ ዶላር አውዲ አር8 ፤ቫንፒርሲ

ባለ 230ሺ ዶላር ፖርሽ፤ ሊዮኔል ሜሲ ባለ 181ሺ ዶላር ማሴራቲ መኪኖቻቸውን አዘውትረው ይነዳሉ፡፡


የዳኞች ገቢ
የዓለም ዋንጫ ዳኞች አብዛኛዎቹ ደሞዛቸው ከ30 እስከ 40ሺ ዶላር ነው፡፡ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው እና በተለይ የጥሎ

ማለፍ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች እስከ 50ሺ ዶላር ይከፈላቸዋል፡፡


ኮሎምቢያ  ከኡራጋይ
በታሪካቸው 40 ጨዋታዎችን አድርገዋል፡፡ በ19 ኡራጋይ ስታሸንፍ ኮሎምቢያ 13 አሸንፋ በ8 ጨዋታዎች አቻ

ተለያይተዋል፡፡
ዘኮፊ ግሮወርስ  በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የኮሎምቢያ ብሄራዊ ቡድን ‹‹ወደዚህ የመጣው አገር ነው። ቡድን ብቻ

አይደለም›› የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 194.6 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
ላሴላስቴ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የኡራጋይ ብሄራዊ ቡድን ‹‹ 3 ሚሊዮን ህልሞች ወደፊት ኡራጋይ›› የሚል

መፈክር አለው፡፡  የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 155 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡

ጀርመን ከአልጄርያ
በታሪካቸው ሁለት ጊዜ ተገናኝተው ሁለቱንም ያሸነፈው የአልጄርያ ቡድን ነው፡፡
ዘ ማንሻፍትስ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ‹‹አንድ አገር አንድ ቡድን አንድ ህልም›› የሚል

መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 638 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
የበረሃ ቀበሮዎች/ጦረኞች በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ‹‹የበረሃዎቹ ጦረኞች በብራዚል››

የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 54 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡


ኮስታሪካ ከግሪክ  
ሁለቱም አገራት ተገናኝተው አያውቁም፡፡
ሎስቲኮስ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የኮስታሪካ ብሄራዊ ቡድን ‹‹የምንወደው እግር ኳስን፤ ጥንካሬያችን ህዝባችን ፤

ኩራታችን ኮስታሪካ›› የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 32 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
የፓይረስ መርከብ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የግሪክ ብሄራዊ ቡድን ‹‹የጀግኖች ጨዋታ እንደግሪኮች ነው›› የሚል

መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 80.4 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡


አሜሪካ  ከቤልጅዬም
በታሪካቸው 5 ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡ 4 አሜሪካ ስታሸንፍ ቤልጅዬም አንዱን አሸንፋለች፡፡
ስታር ኤንድ ስትራይክስ በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ‹‹በቡድን አንድ ነን፤ በወኔ እንነሳለን››

የሚል መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 28.8 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡
ቀይ ሰይጣኖች  በሚል ቅል ስም የሚታወቀው የቤልጅዬም ብሄራዊ ቡድን ‹‹የማይቻለው እንደሚቻል ጠብቁ›› የሚል

መፈክር አለው፡፡ የቡድን ስብስቡ የዋጋ ግምት 357 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡



በምድብ 2 ኡራጋይ 1ለ0 በሆነ ውጤት ጣሊያን ባሸነፈችበት ጨዋታ በ80ኛው ደቂቃ  የጣሊያኑን ተከላካይ ጂዮርጂዮ

ቼሊኒ ትክሻ የነከሰው ሉዊስ ስዋሬዝ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር በተላለፈበት ቅጣት ከማንኛውም የእግር ኳስ

እንቅስቃሴ ለ4 ወራት ታገደ፡፡  በቅጣቱ መሰረት ስዋሬዝ  ከዓለም ዋንጫው እንዲባረር ከመወሰኑም በላይ  ለክለቡ

ሊቨርፑል በ13 ጨዋታዎች፤ ለብሄራዊ ቡድኑ 9 ጨዋታዎች አይሰለፍም፡፡ በተጨማሪም 65ሺ ፓውንድ የገንዘብ መቀጮ

ተጥሎበታል፡፡ የኡራጋይ እግር ኳስ ፌደሬሽን  በፊፋ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ እስከመጭው ሰኞ  እድል አለው፡፡

የ27 ዓመቱ ሊውስ ስዋሬዝ ከፊፋ የቅጣት ውሳኔ በኋላ ብራዚልን በመልቀቅ በቀጥታ ወደ ኡራጋይ ዋና ከተማ

ሞንትቪድዮ እንደተመለሰ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ስዋሬዝ ከንክሻው በኋላ ከስፖንሰሮቹ የሚያገኘው ገቢ ሊቀንስበት እና ከፍተኛ ኪሣራ ሊገጥመው  

ይችላል፡፡ የትጥቅ አምራቹ ኩባንያ አዲዳስ ከፊፋ ውሳኔ በኋላ ከተጨዋቹ ጋር ያለውን የውል ስምምነት ለማጤን

አስቸኳይ ስብሰባ አድርጓል፡፡ አዲዳስ ለስዋሬዝ በዓመት እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር ይከፍለው ነበር፡፡ ቦከር ብራንድ 888

የተባለ አቋማሪ ድርጅት ተጨዋቹን ባለፈው ወር አምባሳደር በማድረግ ቢሾመውም ከንክሻው በኋላ ይህን ሹመቱን

ለመሰረዝ ይወስናል ተብሏል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ከተጨዋቹ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ

ደረጃ ክብሩ እየተበላሸ ቢሆንም የመሸጥ ፍላጐት እያሳየ አይደለም፡፡ ይሁንና በርካታ የእንግሊዝ ክለቦችና ሁለቱ የስፔን

ክለቦች ሪያልማድሪድና ባርሴሎና ተጨዋቹ ለመግዛት የዓለም ዋንጫውን መገባደድ ሲጠባበቁ ነበር፡፡ ኮንክሻው በኋላ

ግን ይህ ፍላጐት ቀንሷል። ሊቨርፑል ተጨዋቹን ለመሸጥ እስከ 100ሚሊዮን ዶላር እንደሚጠይቅ አንዳንድ ዘገባዎች

ቢያመለክቱም የዝውውሩ ሂሳብ በግማሽ ሊቀንስ እንደሚችል መረጃዎች አውስተዋል፡፡
ስዋሬዝን በኡራጋይ ‘˜el lunático que muerde todo’ብለው የሚጠሩት ሲሆን ትርጉሙም ሁሌ ተናካሹ ቀዌ

እንደማለት ነው፡፡ የኡራጋይ ፕሬዝዳንት ጆሴ ሙጂካ ለአገሬው ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት እርግጫ እና የጉልበት

ጨዋታ በበዛበት ግጥሚያ  አንድ ንክሻ መጋነኑ ተገቢ አይደለም ብለዋል።


ከዚህ በታች የቀረቡትን የተጨዋቾችን ዓመታዊ ገቢና የሃብት ደረጃዎች በዓለም ዋንጫ ሰሞን ይፋ ያደረገው  ዌልዝ

ኤክስ የተባለ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ነው፡፡ የታዋቂ ሰዎችን ሃብት በመሰለል እና መረጃዎችን በማስላት በየጊዜው

በሚሰራቸው ጥናቶች ደረጃዎችን የሚሰጠው እና መረጃዎችን በድረገፁ የሚያሰራጨው ተቋሙ ዴሊዮቴ ቢዝነስ ግሩፕና

የታዋቂውን የቢዝነስ መፅሄት ፎርብስ ዓመታዊ እና ወቅታዊ ሪፖርቶችም ይዳስሳል፡፡ የብዙዎቹ የዓለም ዋንጫ ተጨዋቾች

በተለይ በትልልቅ ብሄራዊ ቡድኖች ያሉት የሃብታቸው መጠን ከ40 እስከ 60 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን የዌልዝ ኤክስ

ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በ20ኛው ዓለም ዋንጫ ተሳታፊ በሆኑ 32 ብሄራዊ ቡድኖች ከተያዙት 736 ተጨዋቾች በ2014

አጠቃላይ ገቢያቸው ከ1 እስከ 5 ደረጃ የሚያገኙት ተጨዋቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡
የ2014 ገቢ (በሚሊዮን ዶላር )
ክርስትያኖ ሮናልዶ ጠቅላላ ገቢ 80 ሚ. ዶላር (በደሞዝ 52 ፤ በስፖንሰርና ንግድ 28)
ሊዮኔል ሜሲ 64.7 (41.7 ፤23)
ኔይማር 33.6 (17.6 ፤16)
ዋይን ሩኒ 23.4 (18.4፤ 5)
ያያ ቱሬ 21.7 (19.2፤ 2.5)
በሃብት ደረጃ
በሚሊዮን ዶላር
ክርስትያኖ ሮናልዶ 250 ሚሊዮን ዶላር
ሊዮኔል ሜሲ 180
ዋይ ሩኒ 125
ፊሊፕ ላሃም 100
ዲድዬር ድሮግባ 90


Read 3433 times