Saturday, 02 August 2014 11:57

“ጥቁር እንግዳ” ፊልም ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በሚካኤል ታምሬ ተፅፎ የተዘጋጀው “ጥቁር እንግዳ” ፊልም የፊታችን ሰኞ ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር እንደሚመረቅ ተገለፀ፡፡
የድራማቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው ፊልሙ፤ 1፡40 የሚወስድ ሲሆን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት መውሰዱንም ደራሲና ዳይሬክተሩ ሚካኤል ታምሬ ተናግሯል፡፡ ከተባባሪ ፕሮዲዩሰሩ እስከዳር ግርማይ ጋር በመሆን ፊልሙን መስራቱን የተናገረው አርቲስቱ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ጁን 14 ቀን 2014 ዓ.ም ባህሬን በሚገኘውና በታዋቂው ሲፍሞል ሲኒማ በድምቀት መመረቁንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
በ“ሓላ” ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ፊልሙ፤ በአገራችንም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ በ11 ሰዓት የፊልም ባለሙያዎች ጋዜጠኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል ተብሏል። “በጥቁር እንግዳ” ፊልም ላይ ሚካኤል ታምሬ፣ አድማሱ ከበደ፣ ዝናህብዙ ፀጋዬ፣ ድርብወርቅ ሰይፉ፣ መኮንን ላዕከና ሌሎችም ወጣትና አንጋፋ አርቲስቶች ተሳትፈውበታል፡፡

Read 2529 times