Saturday, 06 September 2014 11:46

“ዋናው ነገር ጤና” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ለ12 ዓመታት በፋርማሲ ባለሙያነት ሲሰራ የቆየው ፍትህ ቶላ ያዘጋጀው “ዋናው ነገር ጤና” የተሰኘ መፅሀፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሏል፡፡ በ324 ገፆች ተቀንብቦ በ20 ምዕራፎች ተዘጋጀው  መፅሀፉ፤ በሀገራችን በብዛት ስለሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎች፣ ስለበሽታዎች ምንነት፣ ስለሚዛመቱበት መንገድ፣ ስለምልክቶቻቸው፣ ስለመከላከያ መንገዶቹ፣ ስለህክምና መፍትሄዎቻቸውና መሰል ጉዳዮች ላይ መረጀና ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሲሆን በሽታዎቹ በብዛት ስለሚያጠቋቸው የሰውነት ክፍሎችም ይገልፃል ተብሏል፡፡
በመጽሐፉ በ80 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን አዘጋጁ ፍትህ ቶላ በሸገር ኤፍኤም 102.1 ሬዲዮ ላይ ከኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪ ጋር በመተባበር በሚያቀርበው “ዋናው ነገር ጤና” የተሰኘ የ20 ደቂቃ ፕሮግራሙ ይበልጥ ይታወቃል፡፡

Read 2022 times