Saturday, 06 September 2014 11:47

“ሁሉ አዲስ” የመዝናኛ ፕሮግራም ሰሞኑን ይጀምራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

“ሁሉ አዲስ” የመዝናኛ ፕሮግራም በአዲሱ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬዲዮ ጣቢያ የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት  በልዩ የመክፈቻ ፕሮግራም እንደሚጀመር አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡
 በመጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ በ “ሰው ለሰው” ድራማ የአባት ገፀባህርይን ተላብሶ የተወነው ዝናብዙ ፀጋዬ እና አርቲስት ስለሺ ደምሴ እንዲሁም እስከ ዝግጅቱ ዕለት ስሙ የማይጠቀስ ታዋቂ የኪነጥበብ ሰው በእንግድነት እንደተጋበዙ ታውቋል፡፡
 በማርቭል ፕሮሞሽንና ኮሚኒኬሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር እየተዘጋጀ የሚቀርበው “ሁሉ አዲስ” በሳምንት ለሶስት ቀናት የ6 ሰዓት የአየር ጊዜ ይኖረዋል፡፡
ማክሰኞና ሃሙስ ከ10 እስከ 12 ሰዓት፤ አርብ ከ8 እስከ 10 የሚቀርበው ኪነጥበባዊ ዝግጅት፤ በሙዚቃ፣ ሲኒማና ተያያዥ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኩራል ተብሏል፡፡
የመዝናኛ ፕሮግራሙን ሲሳይ ጫንያለው፣ ስዩም ፍቃዱና ብስራት ከፈለኝ የሚያዘጋጁት ሲሆን ጋዜጠኞቹ ከዚህ በፊት በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 የተለያዩ ፕሮግራሞችን ያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Read 3021 times