Monday, 03 November 2014 08:28

የፍቅር ደብዳቤ አውደርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

     አቶ ስዩም ገ/ፃዲቅ ለተከታታይ ስድስት ዓመታት በአረብ አገር ለነበረችው ፍቅረኛቸው የጻፏቸውና በፍቅረኛቸው ምላሽ የተሰጠባቸው ከ200 በላይ የፍቅር ደብዳቤዎች ለእይታ በቁ፡፡ ደብዳቤዎቹ የተለያየ ይዘት፣ መጠንና ቅርፅ ያላቸው ሲሆኑ የአንድ ሰው መዳፍ ግማሽ የምታህል ባለ ልብ ቅርፅ ደብዳቤ ትጠቀሳለች፡፡ ትልቁ ባለ መቶ ገፅ ደብዳቤ ሲሆን በስኮችቴፕ የተቀጣጠለ 3 ሜትር ርዝመት ያለው ወረቀት ላይ የተፃፈ አንድ ወጥ ደብዳቤም በአውደ ርዕዩ ቀርቧል፡፡
ደብዳቤዎቹ ከ1988 ዓ.ም እስከ 1994 ዓ.ም ለስድስት ዓመታት የተፃፉ ሲሆን የተላኩባቸው ፖስታዎች፣ ቴምብሮች፣ የተላላኳቸው ፖስት ካርዶችና የፍቅረኞቹ ፎቶግራፎችም ተካተዋል፡፡
ፍቅረኞቹ የተዋወቁበትን 20ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በቅርቡ የተከፈተው አውደርዕይ፤ ላልተወሰነ ጊዜ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ አውደ ርዕዩ ከሆላንድ ኤምባሲ ወደ ቀራኒዮ በሚወስደው መንገድ ከአይመን ህንፃ ገባ ብሎ በጥንዶቹ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የተዘጋጀ ሲሆን ምሁራን፣ ተማሪዎች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ደራሲያን እየጎበኙት ነው ተብሏል፡፡

Read 4487 times