Monday, 16 March 2015 09:56

በወዜ ወ ባዋዜ” የግጥም መድበል ለንባብ በቃ

Written by  በገጣሚ ደመረ ብርሃኑ የተፃፉ የግጥም ስብስቦች የተካተቱበት “በወዜ ወ ባዋዜ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ ግጥሞቹ በማህበራዊ፣ መንፈሳዊ፣ በፍቅርና ስነልቦና ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ አፍሪካዊ መሆኑ ለግጥሞቹ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ማግኘት እንዳስቻለው በመጽሐፉ ማስታወሻ ላይ የገለጸው ገጣሚው፤አውሮፓዊ ቢሆን ስለቴክኖሎጂ ግጥም መፃፍ ስሜት ስለማይሰጥ “ገጣጣ” ይሆ
Rate this item
(1 Vote)

በገጣሚ ደመረ ብርሃኑ የተፃፉ የግጥም ስብስቦች የተካተቱበት “በወዜ ወ ባዋዜ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ ግጥሞቹ በማህበራዊ፣ መንፈሳዊ፣ በፍቅርና ስነልቦና ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ አፍሪካዊ መሆኑ ለግጥሞቹ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ማግኘት እንዳስቻለው በመጽሐፉ ማስታወሻ ላይ የገለጸው ገጣሚው፤አውሮፓዊ ቢሆን ስለቴክኖሎጂ ግጥም መፃፍ ስሜት ስለማይሰጥ “ገጣጣ” ይሆን እንደነበር ጠቁሞ ቻይናዊ ሆኖ ቢፈጠር ደግሞ ከገጣሚነት ይልቅ የባቡር ገጣጣሚ ለመሆን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣ እንደነበር ገልጿል፡፡ መፅሃፉ፤ 74 ግጥሞችን ያካተተ ሲሆን ለአገር ውስጥ በ30 ብር፣ለውጭ በ15 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ገጣሚ ደመረ ብርሃኑ የአዲስ አድማስ 15ኛ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ በተካሄደ የግጥም ውድድር ሁለተኛ ወጥቶ ባለፈው ሰኞ ዘመናዊ የZTE ሞባይል ተሸልሟል፡፡

Read 1298 times