Monday, 06 April 2015 09:33

ሉሲዎች በመልስ ጨዋታው ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ከሁለት ሳምንት በፊት ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ለማለፍ የደርሶ መልስ የመጀመርያ ጨዋታቸው ካሜሩንን በማስተናገድ 2ለ1 የተሸነፉት ሉሲዎች በመልስ ጨዋታው ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከሜዳቸው ውጭ በሚያደርጉት ጨዋታ የካሜሮን አቻቸውን በሁለት ንፁህ ጎሎች ልዩነት ማሸነፋቸው ያሳልፋቸዋል፡፡
በመጀመርያው ጨዋታ ሉሲዎቹ  በካሜሮን በሜዳቸው ከፍተኛ ብልጫ ተወስዶባቸው ነበር፡፡ በጨዋታው በሎዛ አበራ አማካኝነት በ15ኛው ደቂቃ ላይ ቀዳሚ ቢሆኑም የካሜሮን ሴት አናብስት በ83ኛውና በ87ኛው ደቂቃ ላይ ሁለት ጎሎች በማስቆጠር ከሜዳቸው ውጭ ለማለፍ የሚያስችላቸውን ጠንካራ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ 11ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በኮንጎ ብራዛቪል አዘጋጅነት የሚካሄድ ነው፡፡

Read 1814 times