በሸገር FM 102.1 የለዛ ፕሮግራም፣ የአድማጮች የዓመቱ ምርጥ ኪነ ጥበባዊ ስራዎችና ጥበበኞች ሽልማት በመጪው መስከረም 20 የሚካሄድ ሲሆን አሸናፊዎች በሂልተን ሆቴል በሚደረግ ሥነ - ስርዓት ይሸለማሉ፡፡ ለ1 ወር ከ15 ቀን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በተካሄደው የአድማጮች ምርጫ ለመጨረሻ ውድድር የደረሱት እጩዎች መታወቃቸውን የሽልማቱ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው የሽልማት ሥነ - ስርዓት ላይ ከያንያንና የጥበብ ስራዎች በ9 ዘርፎች ተወዳድረው እንደሚሸልሙ ታውቋል፡፡
ጋዜጠኛ ብርሃኑ ድጋፌ እንደተናገረው፤ የሽልማት ሥነ - ሥርዓቱን ጃኖ ባንድን ጨምሮ ሚካኤል በላይነህ ለመጀመሪያ ጊዜ ፒያኖ እየተጫወተ በመዝፈን ያደምቁታል፡፡
በየዘርፉ ለመጨረሻው ውድድር የበቁት የጥበብ ሥራዎችና ከያኒያን ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
ተዋናይ - የዓመቱ ምርጥ
አዚዛ መሐመድ - ሰኔ 30
ሊዲያ ሞገስ - ላምባ
መሠረት መብራቴ - ሃርየት
ሮማን በፍቃዱ - አዲናስ
ብርቱካን በፍቃዱ - ዘጠኝ ሞት
ሠላም ተስፋዬ - ጥለፈኝ
ሄለን በድሉ - በመንገዴ ላይ
የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ
ግሩም ኤርሚያስ - ላምባ
ግሩም ዘነበ - ኃረየት
ሰለሞን ቦጋለ - ስለ እናት ልጅ
መሳይ ግርማ - ፍቅርና ገንዘብ
አለማየሁ ታደሠ - ያነገስከኝ
ሽመልስ አበራ - ሰኔ 30
ሰለሞን ሙሄ - የገጠር ልጅ
የዓመቱ ምርጥ ፊልም
ላምባ
ሰኔ 30
አዲናስ
ሼፉ 2
ኃየረየት
ዘጠኝ ሞት
ፍቅርና ገንዘብ 2
የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ አልበም
ማዲንጎ አፈወርቅ - ስወድላት
አብነት አጎናፍር - አስታራቂ
ዮሴፍ ገብሬ - መቼ ነው
ዳን አድማሱ - ዘበናይ
ፀሐዬ ዮሐንስ - የኔታ
ብሩክታይት ጌታሁን - ማነው ፍፁም
የዓመቱ ምርጥ ኦሪጅናል የፊልም ማጀቢያ ዘፈን
ሀርየት - ፀደኒያ ገ/ማርቆስ
ላምባ - አንተነህ ምናሉ
ያየ ይፍረደው - ማቲያስ ይልማ
ሼፉ 2 - ካሳሁን እሸቱ
ፍቅርና ገንዘብ 2 - ኤልያስ ሁሴን
ዘጠኝ ሞት - ሀይሉ መርጋ
የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) - በሰባ ደረጃ (ታን ታራራም)
የኛ - ስደት
ዘሪቱ ከበደ - ሰይፍህን አንሳ
ጃኪ ጎሲ - አልሰማም
ጎሳዬ ተስፋዬ - አለቃዬ
አብነት አጎናፍር - Maal Naa Wayaa (አሮምኛ)
መሀሙድ አህመድ - ሀገሬ
ፀደኒያ ገ/ማርቆስ - የፍቅር ግርማ
የሕይወት ዘመን ተሸላሚ
ማሪቱ ለገሰ
አለማየሁ እሸቴ
ባህታ ገ/ህይወት
ዳዊት ይፍሩ
ግርማ በየነ
ግርማ ነጋሽ
ዮሀንስ አፈወርቅ
አዲስ ድምፃዊ
ዳን አድማሱ - ዘበናይ
ሀና ግርማ - እውነት
ብሩክታይት ጌታሁን - ማነው ፍፁም
ራስ ዮሐንስ (ጆኒ) - ሰላምታ
ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ
ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ) - ሽክ ብለሽ (ፊቸሪንግ ጃሉድ)
አብነት አጎናፍር - አስታራቂ
ማዲንጎ አፈወርቅ - ታንጉት
አብነት አጐናፍር - ማነው ያለው
ቤቲ ጂ - ና ና ደማዬ
ፀሐይ ዮሐንስ - የኔታ
ታምራት ደስታ - ከዛ ሰፈር
Monday, 24 August 2015 10:03
የለዛ ፕሮግራም የኪነ ጥበብ ሽልማት በመስከረም ይካሄዳል
Written by ማህሌት ኪዳነወልድ
Published in
ጥበብ