የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር፤ከመላው አገሪቱ አሰባስቦ በመሰረታዊ የስነ ፅሁፍ ትምህርት ላሰለጠናቸው ሰልጣኞች ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በቤተመዘክር እውቅና እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ ማህበሩ ዘንድሮ ለሶስተኛ ዙር ከሐምሌ 6 ቀን እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2007 ዓ.ም ለሁለት ወራት መሰረታዊ የሥነ ፅሁፍ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ከተቋቋመበት መሰረታዊ አላማዎች አንዱ ተተኪ ፀሀፍትን ማፍራት ሲሆን በየዓመቱ ከመላው አገሪቱ አሰባስቦ ስልጠና መስጠቱም የተነሳበትን አላማ ለማሳካት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
Saturday, 19 September 2015 09:22
መሰረታዊ የስነ-ፅሁፍ ስልጠና የወሰዱ ዛሬ እውቅና ያገኛሉ
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና