Saturday, 19 December 2015 09:46

የዘላለም ጥግ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

(ስለ ሰላም)

• መጀመሪያ ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤
ከዚያ በኋላ ለሌሎች ሰላምን ማምጣት
ትችላለህ፡፡
ቶማስ ኤ ኬምፒስ
• ዓይን ላጠፋ ዓይኑን ማጥፋት የሚለው ህግ
መጨረሻው መላውን ዓለም ዓይነስውር
ማድረግ ነው፡፡
ማሃትማ ጋንዲ
• ሰላም በሃይል ሊጠበቅ አ ይችልም፤ ሰላም
ሊሰፍን የሚችለው በመግባባት ብቻ ነው፡፡
አልበርት አነስታይን
• ሰላም የግጭት አለመኖር አይደለም፤
ግጭትን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት
አቅም ነው፡፡
ሮናልድ ሬገን
• በሰላም አምናለሁ፤ በይቅርባይነት
አምናለሁ፡፡
ማላላ ዩሳፍዛይ
• ከራሷ ጋር ሰላም የፈጠረች አፍሪካን
አልማለሁ፡፡
ኔልሰን ማንዴላ
• ሁላችንም በሰላም እንኖር ዘንድ ሁላችንም
ሰላምን መፍጠር አለብን፡፡
ዣን በርትራንድ አሪስቲዴ
• መላዕክት የሚዘምሩት የመጀመሪያ ነገር
ሰላምን ነው፡፡
ጆን ኬብሌ
• የሰው ልጅ ማስታወስ ያለበት ሰላም
እግዚአብሔር ለፍጡራኑ የሚያበረክተው
ስጦታ አለመሆኑን ነው፤ ሰላም አንዳችን
ለሌላችን የምናበረክተው ስጦታ ነው፡፡
ኢሊ ዊስል
• ሰላምና ፍትህ የአንድ ሳንቲም ሁለት
ገጽታዎች ናቸው፡፡
ድዋይት ዲ. ኢዘንሃወር
• ጦርነትን ማወጅ የለብንም ማለት ብቻ
በቂ አይደለም፤ ሰላምን መውደድና
መስዋዕትነት መክፈልም ይናርብናል፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ
• ሰላምን እናፈቅራለን፤ ነገር ግን በማንኛውም
ዋጋ የተገኘ ሰላምን አይደለም፡፡
ዳግላስ ዊሊያም ዴሮልድ
• ተስፋ ልክ እንደ ሰላም ነው።
ከእግዚአብሔር የሚበረክትልን
ስጦታ አይደለም፡፡ አንዳችን ለሌላችን
የምናበረክተው ስጦታ ነው፡፡
ኢሊ ዊስል
• ከጦርነት አውድማ ወደ ሰላም ጠረጴዛ
ለመድረስ ረዥም መንገድ ተጉዣለሁ፡፡
ሞሼ ዳያን

Read 1029 times