Saturday, 30 January 2016 11:39

የግድቡ አማካሪዎች የቴክኒክ ሃሳባቸውን በጥቂት ቀናት ያቀርባሉ

Written by 
Rate this item
(10 votes)

• የግብጽና ሱዳን ሚኒስትሮች ልዩ ዝግጅት ለማድረግ መክረዋል
• የሶስቱ አገራት መሪዎች በአ/አ በግድቡ ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል

    የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በታችኛው የተፋሰሱ አገራት የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በማጥናት ላይ የሚገኙት አለማቀፍ አማካሪ ተቋማት፤ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የቴክኒክ ሃሳቦቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና የግብጽ የመስኖና የውሃ ሃብቶች ሚኒስትር ሆሳም ሞጋዚና የሱዳኑ አቻቸው ሞአታዝ ሙሳም፣ አገራቱ አማካሪዎቹ ለሚያቀርቧቸው ሃሳቦች ማድረግ የሚገባቸውን ልዩ ዝግጅቶች በተመለከተ መምከራቸውን የግብጽ መንግስት የኢንፎርሜሽን አገልግሎት ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
ሁለቱ ሚኒስትሮች በቀጣዩ የሁለቱ አገራት የጋራ ከፍተኛ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይፈረማል ተብሎ በሚጠበቀው የአገራቱ የውሃ ሃብቶች ትብብር የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ መወያየታቸውን የጠቆመው መረጃው፣ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በሚመለከቱ ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውንም ገልጧል፡፡ የግብጹ አሃራም ድረገጽ በበኩሉ፤  የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በዛሬው እለት በተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸውን ጠቁሞ፣ በግድቡ ዙሪያ ከኢትዮጵና ከሱዳን አቻቸው ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘግቧል፡፡




Read 4462 times