Saturday, 30 January 2016 12:47

“በደም የተፈረመ ቃል ኪዳን” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በምትኩ አዳነ ጎሽዬ ተፅፎ የተዘጋጀውና በፍቅርና በሳይንስ ዙሪያ የሚያጠነጥነው “በደም የተፈረመ ቃል ኪዳን” የተሰኘ መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መቼቱን አዲስ አበባ፣ ጎጃምና አሜሪካ ያደረገው መፅሀፉ፤ አንድ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሄደ ኢትዮጵያዊ፤ ወደ አዕምሮ ምርምር ውስጥ ገብቶ መጥፎ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች ጭንቅላት በማውጣት፣ በጥሩ አዕምሮ መተካት የሚል ሀሳብ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል። አስተያየት ሰጪዎች፤ ይህ የፈጠራ ምርምር ወደ እውነት ቢቀየር ዓለምን ይለውጣል ማለታቸው የተጠቆመ ሲሆን መፅሀፉ በ210 ገፆች ተቀንብቦ በ65 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2481 times