Saturday, 06 February 2016 11:30

“ህይወት በጠንቋዩ ቤት ውስጥ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

    ለሁለት ዓመታት ተኩል በጠንቋይ ቤት ውስጥ ስላሳለፈው ኤርሚያስ ጌታሁን የህይወት ውጣ ውረድና በአገራችን ውስጥ ስለሚካሄዱ የጥንቆላ ስነ - ስርዓቶች በስፋት የሚያትተው የኤርሚያስ ጌታሁን “ህይወት በጠንቋዩ ቤት ውስጥ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በመክብብ አበበ ተጽፎ የተዘጋጀው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው መጽሐፉ፤ የአገራችን ጠንቋዮችና የጥንቆላ ስርዓታቸው ምን እንደሚመስል፣ ጥንቆላና ዓለም አቀፋዊነቱ፣ የአገራችን ጠንቋዮችና ጥንቆላ ከሌላው ዓለም ስለሚለይበትና በባለታሪኩ ኤርሚያስ ጌታሁን የጥንቆላ ቤት ቆይታ ላይ ሰፊ ትንታኔ ሰጥቷል፡፡ ለብዙዎች ትምህርት ይሰጣል የተባለው ይህ መጽሐፍ፤ በ170 ገፅ ተመጥኖ በ48 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 4841 times