Saturday, 27 February 2016 12:17

“50 ሎሚ” ፊልም ከነገ በስቲያ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

     በደራሲና ዳይሬክተር ረዲ በረካ ተፅፎ የተዘጋጀውና በስፖትስ ፊልም ፕሮዲዩስ ተደርጎ የቀረበው “50 ሎሚ” ፊልም፤ ከነገ በስቲያ ሰኞ በብሄራዊ ቴአትር ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርአት ይመረቃል፡፡ በማህበረሰቡ የተገፋ አንድ ታዳጊ የኑሮ ትርጉም ሳይገባው በወንጀል ተዘፍቆና በፍቅር ተይዞ የሚዋትትበትን ሂደት የሚተርከውን ይህን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ስድስት ወራትን የፈጀ ሲሆን ተዘራ ለማ፣ የትናየት ታምራት (ሚሚ) ፋሪስብሩ፣ ሱራፌል ፀጋዬና ሌሎች አንጋፋና ወጣት ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡

Read 1749 times