“መጻሕፍት ለሁሉም ቤት” በሚል የመጻሕፍት መደብር ባለቤቶች በጋራ የሚያዘጋጁት ሁለተኛው የመጻሕፍት ኤግዚቢሽን ዛሬና ነገ ጥቁር አንበሳ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ትራኮን ታወር አንደኛ ፎቅ ላይ እንደሚቀርብ የ `እነሆ` መጻሕፍት መደብር ባለቤት አቶ ኤርሚያስ በላይነህ ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ ኤግዚቢሽኑ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን የተሳታፊዎች ቁጥር ከመጀመሪያው አውደ ርዕይ እንደጨመረ ታውቋል፡፡
ተሳታፊዎቹ “እነሆ መጻሕፍት”፣ ክብሩ መጻሐፍት፣ “ሊት-ማን መጻሐፍት፣ Book light፣ ኤዞፕ መጻሕፍት” እና ሌሎች ሲሆኑ በኤግዚቢሽኑ ላይ የታሪክ፣ ፍልስፍና፣ የልቦለድ፣ የተረቶች…እንዲሁም እምብዛም ገበያ ላይ የማይገኙ የቆዩ መጻሕፍት ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
Saturday, 05 March 2016 11:23
“መፃሕፍት ለሁሉም ቤት” ኤግዚቢሽን ዛሬና ነገ ይቀርባል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና